Jump to content

ዘሃራ

ከውክፔዲያ
(ከቬኑስ የተዛወረ)

ዘሃራ ወይም ቬነስ፡ (ምልክት፦♀) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት ሁለተኛ ቅርቡ (2ኛው) ነው። ከበስተኋላው ሰባቱ ፈለኮች ማለትም መሬትማርስጁፒተርሳተርን ኡራኑስነፕቲዩን እና ፕሉቶ ይገኛሉ። ከፊቱ የምትገኘው ብቸኛዋ ፈለክ ኣጣርድ ናት።


ዘሃራ የሚለው ስም ከአረብኛ «ዙህራ» ሲሆን ይህ ማለት ቁንጅና ወይም አበባ ነው። በአንድ ጥንታዊ የአረብ ትውፊት ዘንድ ዙህራ የተባለች ሴት በተዓምር ፈለክ ሆነች። አረቦች ይህን ትውፊት ከአይሁዶች፣ አይሁዶችም ከባቢሎን ሰዎች እንደ በደሩት ይታመናል። በአረመኔ እምነቶች ፈለኩ በፍቅር ጣዖት ስም ይባል ነበር፤ በእንግሊዝኛ ቬነስ የሚለው ስም ከሮማይስጥ የጣዖት ስም ነው።

እብራይስጥ ደግሞ ለዚሁ ፈለክ ያለው ስም «ኖጋህ» ሲሆን ይህ በአማርኛ ማለት «ንጋት» ነው (የንጋት ኮከብ)። በአፋን ኦሮሞ «በከልቸ» ይባላል። በሶማለኛ ደግሞ «ወሀርሂር» ይባላል።

ይህ ፈለክ በመሬት ሰማይ ላይ ከሚታዩ አካላት እንደ ጨረቃ ሁሉ ግዙፉ አካል ነው። ይህን ፈለክ ለማየት ጥሩ ጊዜ የሚሆነው ጠዋት ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት እንዲሁም ማታ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው። ፈለኩ በነዚህ ሁለት ጊዜያት በደማቅ ቀይ ብርሃኑ ተለይቶ ይታወቃል። የተሰራው ከ መሬት ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ቋጥኝ ከበዛበት አካል ነው። ይህም ባህሪው ከ ሶስቱ ፈለኮች ማለትም ከ ሜርኩሪ፣ መሬት እና ማርስ ጋር ተመሳሳይ ባህሪ እንዲኖረው ያደርገዋል። እነዚህ በአንድነት በ ኢንግሊዝኛው ተሬስትሪያል ፈለኮች.በመባል ይታወቃሉ።

ቬነስ ላይ ባረፉ የሶቭየት ህብረት ሮቦቶች የተነሳው የቬነስ ምድር ፎቶ