ኡራኑስ

ከውክፔዲያ

ኡራኑስ፡ (ምልክት፦⛢) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት 7ኛ ( ሰባተኛ ) ነው። ከበፊቱ ኣጣርድቬነስመሬትማርስጁፒተር እና ሳተርን የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ከበስተኋላው ደግሞ ነፕቲዩን እና ትንሹ ፕሉቶ ይገኛሉ።

ይዘት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህ ፕላኔት በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የሶስተኛነትን ደረጃ ይይዛል። ግዙፍ የ ጋዝ ክምችት እንደሆነ ይታመናል። በ ረጨቱ ውስጥ የጋዝ ክምችት የሆኑት ፕላኔቶች ጁፒተርነፕቲዩንሳተርን እና ራሱ ኡራኑስ ናቸው። በዚህም የተነሳ ጆቪያን ወይም ጁፒተርን መሳይ እየተባለ ይጠራል። በአብዛሃኛው ሃይድሮጅን እና ሂሊየም ከተባሉ ንጥረነገሮች የተሰራ ነው። በአጠቃላይ ክብደኡ ደግሞ የአራተኛነትን ደረጃ የያዘ ነው።