ጨረር

ከውክፔዲያ
(ከቬክተር የተዛወረ)
ቬክተር
ከነጥብ A ወደ B የሚሄድ ቬክተር

ጨረር (ቬክተር) ማለት በሂሳብና የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት፣ አቅጣጫመጠን ያለው ማንኛውም መለኪያ ማለት ነው። ይህም ምንነታቸውን ለመገንዘብ መጠናቸው ብቻ አስፈላጊ ከሆኑ መለኪያወች ይለያል። ለምሳሌ በአንድ ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪወችን ብዛት ለማወቅ አቅጣጫ አያስፈልግም። ስለዚህ ይህን ጉዳይ የምንለካበት መለኪያ ነጠላ ቁጥር ( ስኬላር) ይባላል። በተቃራኒ አንድ መኪና ወደየት እንደተጓዘ እንደሆነ ለማወቅ መጀመሪያ ከኛ ያለውን ርቀት (መጠን) እና ቀጥሎ አቅጣጫውን ማወቅ ግድ ይላል። ርቀቱን ብቻ ማወቅ መኪናው ወዴት እየተጓዘ እንደሆን ለማወቅ አይረዳም።

ደግሞ ይዩ፡ የጨረር ስሌት