ቭሮጽወፍ

ከውክፔዲያ

ቭሮጽወፍ (ፖሎኛ፦ Wrocław) የፖላንድ ከተማ ነው።

የሕዝቡ ቁጥር 635,759 ያህል ሰዎች ነው።

ገላውዲዎስ በጥሊሞስ ካርታ (130-140 ዓም ግድም) «ቡዶሪጉም» የተባለ መንደር በአካባቢው ይታያል። ቭሮጽወፍ የተመሠረተው በ10ኛው ክፍለ ዘመን ዓም በገዢው ቭራቲስላቭ ስም ሲሆን፤ በመጀመርያ «ቭራቲስላቪያ» ተባለ።