Jump to content

ተሾመ ቶጋ

ከውክፔዲያ

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ፡ በ1954ደቡብ ኢትዮጵያወላይታ ተወለዱ። እ. ኤ አ. በ2009 የ46 ዓመቱ ጎልማሳ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን እንደ ተቆጣጠረ ተቀማጭነታቸው በግብጽ ሆኖ ለ 3 የአረብ አገሮች አምባሰደር ሆኑ። ከዚያም በስፖርት ሚንስትርነት ካገለገሉ በኋላ በ1997 ውዝግብ ያስነሳው የጠቅላላ ምርጫ ሲደረግ ለፓርላማአፈ ጉባኤነት ኢሕአዴግ በበላይነት በተቆጣጠረበት ፓርላማ ተመረጡ። ጥሩ የመናገር ችሎታ አላቸው የሚባልላቸው አቶ ተሾመ በተለይ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ከኬኒያዓለም ጋዜጠኞች የሚሰጡት ቃለ ምልልስ በወቅቱ ታዋቂ አርጎአቸው ነበር። ይሁን እንጂ በፓርላማ ተናጋሪነት ዘመናቸው የወከሉትን ፓርቲ ወግነው የተቃዋሚዎችን መብት በተደጋጋሚ ሲጫኑ ስለተስተዋሉ ብዙ ነቄፌታ አትርፈዋል።