ተኖረና ተሞተ

ከውክፔዲያ

ተኖረና ተሞተ

(69)አንዲት እድሜ ልኩዋን በድህነት የኖረች አሮጊት በነ አለቃ ገብረሀና ሰፈር ውስጥ ታርፍና ሰው ለቀብር ጉድ ጉድ ሲልና ሲሯሯጥ ሲጣደፍ አለቃ በዚያው መንገድ ሲያልፉ “ምንድን ነው እጅብ እጅቡ” ብለው ይጠይቃሉ። “እንዴ አለቃ አልሰሙም እንዴ ?”፥ “ምኑን?”፥ “ያቺ ደሀ አሮጊት መሞቷን?”። አለቃም ቀጠል ያደርጉና “አሄሄሄ ተኖረና ተሞተ?” ብለው ተናገሩ። በህይወትም እያለች የቁም ሙት ሞታለች ያም ኑሮ ሆኖ ሞት ለሷም መጣባት ወይ እንደማለት ነው።