ቱሉዝ
Appearance
(ከቱሉስ የተዛወረ)
ቱሉዝ Toulouse | |
ክፍለ ሃገር | ኦት-ጋሮን |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 439,553 |
ቱሉዝ (Toulouse) በደቡብ ምዕራብ የምትገኝ የፈረንሳይበስፋትዋ አራተኛ ከተማ ስትሆን አብዛኛዎቹ ህንፃዎችዋ የተሰሩት ከሸክላ በመሆኑ «ፅጌረዳማ ቀለሟ ከተማ» የሚለውን የቅፅል ስም እንድታገኝ አድርጓታል። ቱሉዝ በተማሪ ብዛትዋ በዩንቨርስቲዎችዋ በወይን–ጠጅ በሚመስለው አበባዋ፣የኤይር ባስ (Air bus) ዋና መቀመጫ በመሆንዋ ከምትታወቅባቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው። በ1998 የነዋርዎችዋ ብዛት 437 715 ሲደርስ በዙሪያዋ ያሉት ነዋርዎችዋ ሲጨመሩ 819 000 ይደርስ ነበር።
ቱሉዝ የሚለው ቃል ከየት እንደመጣ እርግጠኛበ ባይሆንም ቶሎዛ (Tolosa) ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ነው በሚለው ሀሳብ ብዙዎች ይስማማሉ። ከቶሎዛ ወደ (Tholose) ከዛም፡ በኦክሲታንኛ፡ (Occitanie) የአነጋገር ዘይቤ ምክንያት ቱሉዝ እንደተባለች ይገመታል።
ቱሉስ፡ በአመት፡ ውስጥ፡ አብዛናዎን፡ ገዛ፡ ፀሐያማ፡ ስትሆን፣ በየፈረንሳይ፡ ሞቃታማ፡ ከሚባሉት፡ ከተማዎች፡ ውስጥ፡ ትመደባለች፡፡ ከፍተኛ፡ ሙቀትዋ፡ ከ28°c እስከ 33°c ሲሆን፣ (እስከ 44°c የደረስበት፡ አመታት፡ ተመዝግበዋል) ዝቅተኛው፡ 0°c እስከ 3°c፡ ይደርሳል ። ጸደይ- ዝናባማና፡ መብረቅ፡ የበዛበት። በጋ- ደረቅና፡ ሞቃታማ። ክረምት- እርጦብና፡ ቀዝቃዛ፡ (በብዛት፡ ካለ፡ በረዶ)።