Jump to content

ቱድሐሊያ

ከውክፔዲያ
(ከቱዳሊያ የተዛወረ)

ቱድሐሊያ እንደሚታሠብ ምናልባት 1628-1605 ዓክልበ. አካባቢ ከዙዙ በኋላ በካነሽ ወይም በኩሻራ (በሐቲ) አገር) የገዛ ንጉሥ ነበር። ይህ ግን በሥነ ቅርስ ሊረጋገጥ አይችልም።

በዙዙ ቤተ መንግሥት ውስጥ «ዋናው ዋንጫ ተሸካሚ» የሚል ማዕረግ የነበረው ሰው ቱድሐሊያ እንደ ተባለ ሲታወቅ፣ ምናልባት የሻላቲዋራ ከተማ ንጉሥ ካሩም ካነሽን ካጠፋ በኋላ (1628 ዓክልበ ግድም) ቱድሐሊያ እንደ ተነሣ ይገመታል። ከዚህ በቀር በአንድ ኬጥኛ ሰነድ ላይ የኬጥያውያን ነገሥታት ሲዘረዝር፣ ቱድሐሊያ የንጉሥ ሕሽሚ-ሻሩማ አባት ይባላል። በታሪካዊ ሰነዶች ጉድለት ምክንያት ይህ ሁሉ ወቅት አሁን እርግጥኛ አይደለም። ቱድሐሊያ በውኑ ያንጊዜ ከነገሠ ምናልባት መጀመርያው የኬጥያውያን መንግሥት ንጉሥ ሊቆጠር ይችላል። ሕልውናው እርግጥኛ ስላልሆነ ግን በተለመደ ቁጥር ሳይሰጥ «1 ቱድሐሊያ» አይባለም፤ ዳሩ ግን በኋላ ዘመናት የነገሡት ሌሎች «ቱድሐሊያ» የተባሉት 1 ቱድሐሊያ2 ቱድሐሊያ3 ቱድሐሊያ እና 4 ቱድሐሊያ በኬጥያውያን መንግሥት ነበሩ።

ቀዳሚው
ዙዙ
ሐቲ ንጉሥ
1628-1605 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሕሽሚ-ሻሩማ ?