ኩሻራ
Appearance
ኩሻራ በጥንታዊ ሐቲ (አናቶሊያ፣ አሁንም ቱርክ አገር) የተገኘ ከተማ-አገር ነበረ። ሥፍራው በእርግጥ አይታወቅም።
በአንድ ጽላት ዘንድ፣ የአካድ ንጉሥ ናራም-ሲን (2035 ዓክልበ. ግድም) የኩሻራን ንጉሥ ትሽቢንኪ ከሐቲ ንጉሥ ፓምባና ከ፲ ሌሎች ጋራ አሸነፋቸው።
የኩሻራ ንጉሥ ፒጣና ካነሽን በ1662 ዓክልበ. ግድም እንደ ያዘ ይታወቃል። ከዚያ ልጁ አኒታ በዘመቻ ዛልፓን፣ ሐቱሳሽን፣ ቡሩሻንዳንና ሌሎችን ከተሞች አሸነፈ። በኋላ የኬጥያውያን መንግሥት ንጉሥ 1 ሐቱሺሊ መነሻው በኩሻራ እንደ ነበር አመለከተ። ስለዚህ የኩሻራ ቋንቋ የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች አባል የሆነ ኬጥኛ ይሆናል።