Jump to content

ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ

ከውክፔዲያ

ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ15ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ በእንግሊዝኛ አጠራር ላይ የደረሰ የድምጽ ለውጥ ነበር።

በዚህ ለውጥ ሳቢያ የእንግሊዝኛ ረጅም አናባቢዎች አጠራር ከሌሎች ልሳናት (እንደ እጣልኛፈረንሳይኛ ወዘተ) እጅግ ይለያል።

ስለዚህ፦

  • 'time' (ጊዜ) የሚለው ቃል ከ1400 ዓ.ም. በፊት «ቲም» ሆኖ ቢያሰማ፤ ዛሬ ግን «ታይም» ያሰማል።
  • 'see' (ማየት) '' '' '' '' '' '' «ሴ» '' '' '' '' '' «ሲ» '' '' ።
  • 'name' (ስም) '' '' '' '' '' '' «ናም» '' '' '' '' '' «ኔይም» '' '' ።
  • 'house' (ቤት) '' '' '' '' '' '' «ሁስ» '' '' '' '' '' «ሃውስ» '' '' ።
  • 'moon' (ጨረቃ) '' '' '' '' '' '' «ሞን» '' '' '' '' '' «ሙን» '' '' ።

ከዚህ ዋና ለውጦች ጭምር አንዳንድ ሌሎች ትንንሽ የድምጽ ለውጦች ደረሱ። እንዲሁም ዘመናዊ እንግሊዝኛ 'more' /ሞር/ («ተጨማሪ») ከ6 መቶ አመታት በፊት 'māra' /ማረ/ እንደ ነበር እርግጥኛ ነው።

ከለውጡ በፊት የላቲን ፊደል ዋና ዋና አናባቢዎች (a, e, i, o, u) እንደ ላቲን፣ እንደ ጣልኛ፣ እንደ ሌሎቹም ልሳናት «ኣ፣ ኤ፣ ኢ፣ ኦ፣ ኡ» ይሰሙ ነበር። ከለውጡ በኋላ እነኚህ ድምጾች ረጅም ሲሆኑ ወደ «ኤ፣ ኢ፣ አይ፣ ኡ (oo)፣ አው (ou)» ተሻገሩ። ለውጡ የደረሰበት ምክንያት በ1400-1500 ዓ.ም. ግድም በእንግሊዝ የተነሣው ትውልድ ከወላጆቻቸው አነጋገር ለመለየት አዲስ ቄንጥ ስለ ፈለጉ ነው።