ታሚልኛ

ከውክፔዲያ
ድራቪዲያን ቋንቋዎች ከነታሚልኛ የሚናገሩበት ዙርያ

ታሚልኛ (தமிழ் /ታሚል/) በደቡብ ሕንድና በስሪ ላንካ የሚናገር ቋንቋ ነው። የድራቪዲያን ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው። 70 ሚሊዮን ተናጋሪዎች ሲኖረው ከሕንድ አገር 23 ይፋዊ ቋንቋዎች አንዱ ነው። እንዲሁም በስሪ ላንካና በሲንጋፖር ይፋዊ ኹኔታ አለው።