Jump to content

ታሪክ ዘኦሮሞ

ከውክፔዲያ

'ታሪክ ዘኦሮሞ ወይንም ታሪክ ዘጋላ የኦሮሞን ህዝብ አመጣጥ እና መስፋፋት የሚዘግብ ጽሑፍ ነው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተደረሰው ይሄ መጽሐፍ የዓፄ ልብነ ድንግልን ስርአተ ነገስት በመዳሰስ በርሳቸው ዘመን አገሪቱ ለመጥፋት መድረሷን ሲዘግብ ከአባ ባህረይ በተቃራኒ መልኩ የዚህን ጥፋት ምክንያት በልብነ ድንግል ሃጥያት ያሳብባል። በንጉሱ መታበይ፣ ሲጃራ ማጨስ መፍቀድን፣ የፈርስ ጉግስ መፍቀዱንና ሌሎች የአህዛብ ስራ ናቸው ተብለው ይሚገመቱ ስራዎችን በመስራቱ ሕዝቡ በእግዚአብሐር እንደተቀጣ ያትታል። መጽሐፉ በርግጥም እርስ በርሱ የሚጋጭ ሃሳብም ያቀርባል። በመጀመሪያ ደረጃ ልብነ ድንግል ለሃጢያት የበቃው የኦሮሞዎችን ባህል ስለሚኮርጅ እንደነበር ሲናገር በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ኦሮሞዎች ከግራኝ ወረራ በኋላ እንደመጡ ይናገራል። ስለሆነም የጊዜ ስሌት ግጭት ይታይበታል።

የመጽሐፉን ገጾች በፈረንሳይኛ እና አማርኛ ለማንበብ ምስሉን ይጫኑ