Jump to content

ታርጫ

ከውክፔዲያ
ታርጫ
ከተማ
አገር  ኢትዮጵያ
ክልል  ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት
ዞን ዳውሮ
ካንቲባ አስናቀ አበበ
ታርጫ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ታርጫ
የታርጫ አቀማመጥ በኢትዮጵያ ውስጥ

7°9′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°10′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ታርጫ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ከተማ እና በራሱ እንደ ወረዳ የተለየ ከተማ ነው። ታርጫ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የዳውሮ ዞን መቀመጫ ሆኖ የሚያገለግል ነው። [1] ታርጫ ከአዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ በ507 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እና እንዲሁም በአቅራቢያው ከሚገኘው ወላይታ ሶዶ በ169 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። [2]

መሠረተ ልማቶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ታርጫ 24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ አንድ የመንግስት ሆስፒታል፣ አንድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እንዲሁም የዳውሮ ታርጫ ካምፓስ የሚባል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም አለ፤ ይህም ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፎች አንዱ ነው።