ታቦር እየሱስ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ታቦር እየሱስ

አጼ ሰይፈ አርድ (1344-1372) በደብረ ታቦር ተራራ (እየሱስ ተራራ) ላይ የእየሱስ ቤክርስቲያንን መሰረተ[1][2]። ይህ ቤ/ክርስቲያን አሁን ድረስ ከዚህ ዘመን የመነጩ ቅርጻቅርጾች ሲኖሩት በኋላ በ18ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ራስ ጉግሳ ሙርሳ በቤተክርስቲያኑ አጠቃላይ ለውጥ አድርጓል። ስለዚህም አሁን በቤ/ክርስቲያኑ የሚገኙ ስዕሎች ባብዛኛው ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ዋዜማ የሚመነጩ ናቸው። በ1500 ወቹ ይህ የደብረታቦር ስም በአጼ ልብነ ድንግል ዜና መዋዕል ላይ ሰፈረ።


ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Éthiopie By Luigi Cantamessa, Marc Aubert ገጽ 181
  2. ^ Friedrich Heyer, Die Kirche in Dabra Tabor, Erlangen 1981 (Oikonomia 13)