Jump to content

ቶክ ፒሲን

ከውክፔዲያ

ቶክ ፒሲን (Tok Pisin) በስሜን ፓፑዋ ኒው ግኒ የሚናገር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲቃላ ነው። ከእንግሊዝኛ ስዋሰው በጣም ተለውጧልና ዛሬ እንደ ራሱ ቋንቋ ይቆጠራል። የፓፑዋ ኒው ግኒ መደበኛ ቋንቋ ሆኖ በ120,000 ያሕል ተናጋሪዎችና በ4 ሚሊዮን እንደ 2ኛ ቋንቋ ይነገራል።

የቶክ ፒሲን አጀማመር በፓሲፊክ ውቅያኖስ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ የተላያዩም ልሣናት የሚችሉ ሰራተኞች አንድላይ ለአትክልት ስፍራዎች ሲሰሩ ነበር። ብዙ ጊዜ የእነዚህ ሰራተኞች የጋራ ቋንቋ ጥቂት ቀላል እንግሊዝኛ ቃሎች ብቻ ነበር። ስለዚህ አዲስ "የቋንቋ ዲቃላ" ተወለደ። ከእንግሊዝኛ ብቻ ሳይሆን ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከደሴተኞቹ ቋንቋዎች፣ ከጀርመንኛ፣ ወይም ከፖርቱጊዝ ነበር። ይህ ቋንቋ "ፕጅን" ተብሎ አሁን ሶስት ተወላጆች አሉት፣ እነሱም ቢስላማ (በቫኑዋቱ) ፒጂን (በሰሎሞን ደሴቶች) እና ቶክ ፒሲን ይባላሉ። ቶክ ፒሲን በአንዳንድ ትምህርት ቤት የትምህርት ቋንቋ ነው።

-im = የተሻጋሪ ግስ መነሻ።
luk (ሉክ) - መመልከት፣ lukim (ሉኪም) - ማየት
(ነገር ግን አንዳንድ ግስ ያለዚህ መነሻ ተሻጋሪ ሊሆን ይችላል፦ ካይካይ kaikai - መብላት)
ባይ bai = ወደፊት ጊዜ
ቢን bin = ያለፈ ጊዜ
ስታፕ stap = ተራማጅ ጊዜ
ኤም ባይ ካይካይ = ይበላል።
ኤም ቢን ካይካይ = በላ።
ኤም ካይካይ ስታፕ = እየበላ ነው።
ለስም ቁጥር የለም፣ ለተውላጠ ስም ግን 3 አለ።
ነጠላ ቢጥ ብዙ
1ኛ
(እኔ)
ሚቱፔላ
(ሁለታችን)
ሚፔላ
(እኛ)
2ኛ
(አንተ፣ አንቺ)
ዩቱፔላ
(ሁለታችሁ)
ዩፔላ
(እናንተ)
3ኛ ኤም
(እሱ፣ እሷ)
ቱፔላ
(ሁለታ)
ኦል
(እነሱ)
በአንዳንድ ቀበሌኛ ደግሞ "የሶስት ሰዎች ቁጥር" -tripela (-ትሪፔላ) በሚለው መነሻ ይሰራል።
ለቅጽል ሁሉ -pela (ፔላ) መነሻ ነው። ይህ ቁጥር አያመልክትም።
ለ "liklik" (ሊክሊክ = ትንሽ) ግን -pela የለም። ይህ ቃል ደግሞ እንደ ተውሳከ ግሥ ሊሆን ይችላል።
ባጋራፒም - መስበር
ባጋራፕ - ሰባራ
ካማፕ - መድረስ
ኪሲም - መያዝ
ማንጊ - ሰው
ማንሜሪ - ሕዝብ
ሜሪ - ሴት
ፒኪኒኒ - ልጅ
ፓፓ ጎድ - እግዚአብሔር
ራውስ - መውጣት፣ ራውሲም - ማውጣት
ሳቬ - ማወቅ
ታሶል - ብቻ

የአባታችን ጸሎት፦

Papa bilong mipela
Yu stap long heven.
Nem bilong yu i mas i stap holi.
Kingdom bilong yu i mas i kam.
Strongim mipela long bihainim laik bilong yu long graun,
olsem ol i bihainim long heven.
Givim mipela kaikai inap long tude.
Pogivim rong bilong mipela,
olsem mipela i pogivim ol arapela i mekim rong long mipela.
Sambai long mipela long taim bilong traim.
Na rausim olgeta samting nogut long mipela.
Kingdom na strong na glori, em i bilong yu tasol oltaim oltaim.
Tru.
ፓፓ ቢሎንግ ሚፔላ
ዩ ስታፕ ሎንግ ሄቬን
ነም ቢሎንግ ዩ ኢ ማስ ኢ ስታፕ ሆሊ
ኪንግዶም ቢሎንግ ዩ ኢ ማስ ኢ ካም
ስትሮንጊም ሚፔላ ሎንግ ቢሃይኒም ላይክ ቢሎንግ ዩ ሎንግ ግራውን
ኦልሴም ኦል ኢ ቢሃይኒም ሎንግ ሄቬን
ጊቪም ሚፔላ ካይካይ ኢናፕ ሎንግ ቱዴ
ፕኦጊቪም ሮንግ ቢሎንግ ሚፔላ
ኦልሴም ሚፔላ ኢ ፕኦጊቪም ኦል አራፔላ ኢ ሜኪም ሮንግ ሎንግ ሚፔላ
ሳምባይ ሎንግ ሚፔላ ሎንግ ታይም ቢሎንግ ትራይም
ና ራውሲም ኦልጌታ ሳምቲንግ ኖጉት ሎንግ ሚፔላ
ኪንግዶም ና ስትሮንግ ና ግሎሪ ኤም ኢ ቢሎንግ ዩ ታሶል ኦልታይም ኦልታይም
ትሩ


Wikipedia
Wikipedia