ቺኑዋ አቼቤ

ከውክፔዲያ

በሙሉ ስሙ ሲጠራ አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ይሰኛል። ምናልባትም ናይጄሪያ ካሉዋት ምርጥ ፀሃፍት ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የሚሰለፍ ሳይሆን አይቀርም። በ1930 እ.ኤ.አ. ኦጊዲ በተባለች የናይጄሪያ ግዛት ከአዜያህ ኦካፎ እና ከጃኔት አቼቤ ተወለድ። በ1953 እ.ኤ.አ. ከለንደን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።

ለአቼቤ ድንቅ ሥራ የተባለለት "Things Fall Apart" 50 ወደሚሆኑ የአለም ቁዋንቁዋዎች የተተርጎመ ሲሆን ወደ 10,000,000 ቅጂዎች እንደተሸጡለት ይነገራል። አቼቤ ከአፍሪካ ፀሃፍት ሁሉ ሥራው በበዙ ቁዋንቁዋዎች በመተርጎም ክብረ ወሰኑን እንደያዘ ነው። ብዙዎችም ይኸው ድርሰቱ በአለም እስከዛሬ ከተደረሱ ምርጥ ልበ-ወለዶች መካከል እንደሆነ ይስማማሉ። አቼቤ ከ30 ከሚበልጡ ዩኒበርስቲዎች የክብር ዶክትሬት የተቀበለ ሲሆን ብዙ ሽልማቶችንም ከተለያዩ ድርጅቶች አግኝቷል። ይሁንና እስከ አሁን ድረስ የኖቤል ሽልማት ለማግኘት አልታደለም። ይኸውም በብዙው ጽሁፉ የመራቡን አለም ዘረኛነት የሚተች በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል።

በ1990 ዓ.ም በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ከወገቡ በታች መንቀሳቀስ የተሳነው ሲሆን ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኘው የባርድ ኮሌጅ የቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ፕሮፌሰር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።

ድርሰቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ልብ-ወለድ ድርሰቶች

አጫጭር ታሪኮች

የግጥም መድብል

መጣጥፎች፣ ሂስ እና ፖለቲካዊ አስተያየቶች

የህጻናት መጻህፍት