ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ኃይሌ ፡ ገብረ ፡ ሥላሴ
አምስተርዳም ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (1997) ዓ.ም.

.

ኃይሌ ፡ ገብረ ፡ ሥላሴ ፡ በ ሚያዝያ ፲ ፡ ቀን ፡ ፲ ፱ ፻ ፷ ፭ (1965) ዓ.ም. ፡ በአሰላ ፡ ከተማ ፣ አርሲ ፡ ክፍለ ፡ ሀገር ፡ የተወለደ ፡ አቻ ፡ ያልተገኘለት ፡ ድንቅ ፡ የረጅም ፡ ርቀት ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ሯጭ ፡ ነው። ኃይሌ ፡ በሩጫ ፡ ዘመኑ ፡ በ ፲ ሺህ ፣ በ ፭ ሺህ ፣ በግማሽ ፡ ማራቶን ፣ በማራቶንና ፡ እንዲሁም ፡ በሌሎቹ ፡ የሩጫ ፡ ዓይነቶች ፡ ከ ፲ ፩ ፡ በላይ ፡ የዓለም ፡ ክብረ-ወሰን ፡ ሰብሯል። ኃይሌ ፡ በሩጫ ፡ ችሎታው ፡ ጠንካራ ፡ የሆነበት ፡ ምናልባትም ፡ ከመንደሩ ፡ ከባሕር ፡ ጠለል ፡ በላይ ፡ ከፍታ ፡ ነው ፡ ተብሎ ፡ ቢታመንም ፡ የተፈጥሮ ፡ ጥንካሬው ፡ ዓለምን ፡ ያስደነቀ ፡ ብርቅዬ ፡ ኢትዮጵያዊ ፡ ነው። ኃይሌ ፡ 2 ፡ ጊዜ ፡ የኦሊምፒክ ፡ ወርቅ ፡ ሜዳሊያ ፡ ተሸላሚ ፡ ከመሆኑም ፡ በላይ ፡ በ፴፫ ፡ ዓመት ፡ ዕድሜው ፡ ፪ ፡ ሰዓት ፡ ከ፬ ፡ ደቂቃ ፡ በሆነ ፡ ጊዜ ፡ በመግባት ፡ የዓለምን ፡ ማራቶን ፡ ክብረ-ወሰን ፡ ሊሰብር ፡ ችሏል። ኃይሌ ፡ ገብረ ፡ ሥላሴ ፡ እስካሁን ፡ ድረስ ፡ ፳፮ ፡ የዓለም ፡ ክብረ-ወሰኖችን ፡ ሰብሯል። ሯጭ ፡ ኃይሌ ፡ ገብረ ፡ ሥላሴ ፡ በሲድኒ ፡ እና ፡ በአትላንታ ፡ ኦሊምፒኮች ፡ በ፲ ሺህ ፡ ሜትር ፡ ሩጫዎች ፡ ወርቅ ፡ አስመዝግቧል።

፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም. "ኤንዱራንስ (Endurance)" ፡ የተባለ ፡ ስለ ፡ እራሱ ፡ የእሩጫ ፡ ድል ፡ ፊልም ፡ ተሠርቷል።

እ.ኤ.አ ህዳር 2021 ኃይሌ ገብረስላሴ ከትግራይ አማፂያን ጋር በጦርነት ግንባር ላይ እየተዋጋ ነው።


[[መደብ: የኢትዮጵያ አት ሌቶች]]