Jump to content

ኆኅተ እና

ከውክፔዲያ
ዲጂታል ዑደት
ዲጂታል ዑደት · ኆኅተ አመክንዮ · ዕልፍ ኩነት ማሽን
ግቤት ውጤት
ግቤት A ግቤት B A እና B
0 0 0
0 1 0
1 0 0
1 1 1

ኆኅተ እና መሰረታዊ ከሆኑት ኆኅተ አመክንዮዎች አንዱ ሲሆን ተግባሩም የአመክንዮ እናን ተግባር በተጨባጭ ቁስ መፈጸም ነው። ምንም እንኳ ኆኅተ አመክንዮዎች በተለያዩ ቁሶች ሊሰሩ ቢችሉም፣ በአሁኑ ዘመን እነዚህ ኆኅቶች የሚሰሩት ከኤሌክትሪክ አካላት ስለሆነ አስራሩ ከዚህ አኳያ ይመረምራል። ኆኅተ እና አምክንዮ-እናን በቁስ እንደመግልጹ፣ የዚህ ኆኅት ውጤት ከፍተኛ ቮልቴጅ (1) እሚሆነው ሁለቱም ግቤትዎቹ ከፍተኛ (1) ሲሆኑ ብቻ ነው። ከሁለቱ አንዱ ውይንም ሁለቱም ግቤቶች ትንሽ(0) ከሆኑ የ እና ውጤት 0 ይሆናል ማለት ነው። ይህ ጸባይ ከጎን በሚታየው የዕውነታ ሠንጠረዥ ተብራርቶ ይታያል።

ከሠንጠረዡ እንደምንረዳ፣ የእና-ኆኅት ከሚቀርቡለት ሁለቱ ወይም ከዚያ በላይ ግቤቶች ትንሹን ይከተላል።


የ እና-አመክንዮ ምልክቶች: ሀ) በማብሪያ ማጥፊያ, ለ) አይኢሲ ምልክት ሐ)ብዙ ጊዜ የሚታይምልክት

A እና B ግቤቶች ሲሆኑ ውጤት ሲሆን በአጠቃላይ ይህ ኆኅት የሚተገብረው አመክንዮ ነው ማለት ነው። የመጀመሪያው ምልክት እሚያሳየው ሁለት ማብሪያ ማጥፊያዎችን ሲሆን፣ ሁለቱም ማብሪያ ማጥፊያወች አንድ ላይ ካልበሩ ኤሌክትሪክ እንደምያስተላልፉ መገንዘቡ ይህ ዑደት የአምክንዮ-እናን እንደሚተገበር ያስረዳል።

የ እና-ሆኅት ከኆኅተ ኢእና ወይም ከኆኅተ ኢወይም ሊሰራ ይችላል። ለምሳሌ ከኢ-እና እንዲህ ይሰራል፦

ተፈላጊው ኆኅት ኆኅተ ኢእና የእና ኆኅት መሰራቱ

ቁሳዊ አሰራሩ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
NMOS የሚሰራ እና-ኆኅት
CMOS የሚሰራ እና-ኆኅት

የእና ኆኅት ብዙ ጊዜ የሚሰራው ከ N-channel ወይም or P-channel MOSFETች ነው።