Jump to content

ነጋሽ ገብረማርያም

ከውክፔዲያ

ነጋሽ ገ/ማርያም በ፲፱፲፯ ዓ.ም. በሐረርጌ ጠ/ግዛት በጨርጨር አውራጃ በሀብሮ ወረዳ ልዩ ስሟ መቻራ በምትባል አካባቢ ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢያቸው የባህላዊ ትምህርት ተከታትለዋል።


ከጣሊያን ወረራ በኋላ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ጎልቶ መታየት በመጀመሩ ጣሊያኖችን በብዙ ነገሮች ማውገዝና መቃወም ተጀመረ፡፡ እነሱም እንደ ሲጋራ ማጨስ፣ ሴተኛ አዳሪነትንና የመሳሰሉት ነበሩ፡፡ ነጋሽ ይህን በተመለከተ ሴተኛ አዳሪነትና ምንም እንኳን በጣሊያኖች ጊዜ ይፋ በሆነ መንገድ ቢታይም ከዚያ በፊት እንደነበረም “ሴተኛ አዳሪ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ገልጸውታል፡፡


ነጋሽ ገ/ማርያም ችሎታቸውን ያሳዩት “ሴተኛ አዳሪ” የተሰኘ ልብወለድ መጽሐፋቸውን በጻፉበት ጊዜ ነበር፡፡ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ድራማዎች ውስጥ “የአዛውንቶች ክበብ” እና “የድል አጥቢያ አርበኞች” ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የደራሲው ሥራዎች
 ሴተኛ አዳሪዋ(ልብወለድ)
 FE(ልብወለድ)
 የአዛውንቶች ክበብ(ተውኔት)
 የድል አጥቢያ አርበኞች(ተውኔት)

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።

http://www.ethioreaders.com/authorbook.php?fl=228&lg=A