Jump to content

ኒቅያ ጉባኤ

ከውክፔዲያ

ጉባኤ ኒቂያ በ325 ዓ.ም በሀገረ ኒቂያ በዛሬዋ ቱርክ ኤልኩክ የተካሄደ ጉባኤ ነው ጉባኤው በዋናነት እግዚአብሔር ወልድ ፍጡር በመለኮቱ በማለት የኑፋቄ ትምህርቱን ሲያስተምር የነበረውን አርዮስን ለማውገዝ እና አምስቱን አንቀጸ ሃይማኖት ለማርቀቅ ነበር 318ቱ ሊቃውንት ተው ከስህተትህ ተመለስ ቢሉት እንደ ሳጥናኤል አሻፈረኝ ብሎ በኑፋቄው ትምህርቱ ጸንቷል ይህንንም በወቅቱ ለነበረው ሊቀ ጳጳስ ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ እግዚአብሔር በራዕይ ተገልጦ በህፃን ልጅ አምሳል የተቀደደ ልብስ ለብሶ ታየው ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስም ምነው ልብስህን ማን ቀደደብህ ሲለው እግዚአብሔርም አርዮስ ከባህርይ አባቴ ከአብ ከባህርይ ህይወቴ ከመንፈስ ቅዱስ ለየኝ ብሎ መለሰለት[1]

  1. ^ youtube.com eotcmk.org