ናርሲሲሳዊ ወላጅ
ናርሲሲሳዊ ወላጅ ማለት በናርሲሲስም (ናርሲሳዊ የስነልቦና ቀውስ ) የተጠቃ ወላጅ ማለት ነው በአብዛኛው ናርሲሲስቲክ ወላጆች ብቻቸውንና በትልቅ ስስት ለልጆቻቸው ቅርበት ያሳያሉ ይልቁንም በልጆቻቸው እያደጉ ሲሄዱ በሚያሳዩት ነጻ የመሆን ስሜት ስጋት ያድርባቸዋል የመቅናት ስሜትም ሊያድርባቸው ይችላል ከዚህም የተነሳ በወላጅና በልጅ መካከል ያለው ግንኙነት ናርሲሲሳዊ ትስስር የሚባለውን መልክ ይይዛል ይህም ማለት በናርሲሲሳዊ ወላጅ አይን የልጁ ህልውና ብቸኛ አላማ የወላጅን ስነልቦናዊ ፍላጎት ማሟላት ነው የበታችነት የሚሰማቸው ናርሲሲሳዊ ወላጆች ሌሎች ሰዎች ስለነሱ ያላቸውን አመለካከት መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ ይሰማቸዋል ይህንንም የሚያደርጉበት ምክንያት በጥፋተኛነት እንዳይከሰሱና መገለል እንዳይደርስባቸው እንዲሁም ድክመቶቻቸው እንዳይጋለጡባቸው ነው እነዚህ ሰዎች በራሳቸው የተጠመዱ ሲሆኑ የራሳቸውን ገጽታ በመካብ ብዙ ጊዜ ያጠፋሉ አንዳንዶቹም እራሳቸውን እንደታላቅ ሰው ይመለከታሉ እነዚህ ሰዎች ግትሮች ሲሆኑ ልጅን ለማሳደግ አስፈላጊ የሆነው ራስን በሰው ቦታ አድርጎ የማሰብ ስሜት(ኤምፓቲ)የላቸውም መገለጫዎች
ናርሲሲስም ትውልድ ተሻጋሪ ስነልቦናዊ ቀውሶችን የማስከተል አዝማሚያ አለው ይህም ማለት ናርሲሲሳዊ ወላጆች በተራቸው አንድም ናርሲሲሳዊ የስነልቦና ቀውስ ያለባቸው ልጆች አልያም ደግሞ የተደጋጋፊ ጥገኝነት የስነልቦና ቀውስ ያለባቸው ልጆች ይኖራቸዋል በራስ የሚተማመነው ወላጅ (መጠነኛ ስራ በቂ ነው የሚል ወላጅ)ልጁ በተወሰነ ነጻነት እንዲያድግ ሲፈቅድ ናርሲሲሳዊ ወላጅ ግን ልጁን የራሱን ገጽታ ማሳያ አድርጎ ያየዋል እንዲሁም ይጠቀምበታል የራሱን ገጽታ በመገንባት የተጠመደው ወላጅ ልጁ የራሱን ማንነት ማሳያ እንዲሆን እንዲሁም ልጅየው የወላጁ አድናቂ እንዲሆንለት ይጠብቃል በዚህም ሂደት ልጅየው የወላጁ ስነልቦናዊና ትምህርታዊ ፍላጎት አስፈጻሚ የመሆን ስሜት ያድርበታል ናርሲሲሳዊ ወላጆች ለራሳቸው ያላቸውን ግምት ለመጠበቅና በቀላሉ የሚጠቃውን ማንነታቸውን ለመከላከል የቅርብ ሰዎችን በተለይም ደግሞ እንደራሳቸው ቅጥያ የሚያዩዎቸውን ልጆች ባህሪይ ለመቆጣጠር ይታገላሉ