አለቃ ገብረ ሃና ሞቱ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

አለቃ ገብረ ሃና ሞቱ

(9)አለቃ በጣም ቸገራቸውና ልጃቸውን ሂድና ንጉስ ሚኒሊክን አባቴ ሞቶ ግን ተስካሩን የማወጣበት ገንዘብ የለኝም ብለህ ገንዘብ ተቀብለህ ና ብለው ላኩት። ልጅም እንደተባለው ወደ ቤተመንግስት ሂዶ ያባቱን ከዚህ አለም በሞት መለየት ነግሮ እንደተባለው ገንዘቡን ይጠይቃል። ምኒሊክም እጅግ በጣም አዝነውና አልቅሰው ገንዘቡን ሰጥተው ይልኩታል። አለቃም ችግራቸውን ከተወጡ በኋላ ምኒሊክን ሊያዪ ጉዞ ወደ አ.አ. ያቀናሉ። በቤተመንግስቱም ያያቸው በመገረም እን...ዴ? አለቃ ሞተው አልነበር በማለት እየተገረሙ ለምኒሊክ ሊነግሩ ተጣደፉ። ሚኒሊክም ሲያዩአቸው ገብረሀና ሞተህም አልነበር? ቢሏቸው አለቃም ከሄድኩበት አገር እንደርሶ የሚስማማኝ ንጉስ ባጣ ተመልሼ መጣሁ ብለው ንጉሱን አሳቋቸው አሉ።