አለባቸው ሽታ ባይነስ

ከውክፔዲያ

21ኛው የቢቡኝ ዋና አስተዳዳሪ ናቸው። በዘመነ አብይ አህመድ ጥቅምት 28 ቀን 2011 አ.ም ተሾሙ ። በአብይ ዘመን የወረዳዋ የመጀመሪያ አስተዳዳሪ ሆነዋል። በእግርጥ ከህወሃታዊ አስተሳሰብ የተላቀቅንበት ዘመን በመሆኑ እንጅ በኢህአዴግ ዘመን 7ኛው አስተዳዳሪም ጭምር ናቸው። ወረዳዋ ከተመሰረተችበት 1950ዎቹ ጀምሮ የወረዳዋ አራተኛው ትውልድ መሪ ሆነው በመመረጣቸው እድለኛ ሰው ናቸው። ..... አቶ አለባቸው ሽታ ባይነስ በቢቡኝ ወረዳ አስተዳደር ድጎ ቃንጣ ቀበሌ ልዩ ስሙ ድጎ ማርያም በተባለው ክቡር መንደር ጥቅምት 23 ቀን 1979 ዓ.ም ከአባታቸው ቄስ ሽታ ባይነስ አለምነህ ትርፌ ከእናታቸው ከወ/ሮ አዋግ መኮንን አለሙ 7ኛ ልጅ ሆነው ተወለዱ። 7ኛ ልጅ በመሆናቸውም የወረዳዋ 7ኛ መሪ በመሆን ተመርጠዋል። ........ እድሜያቸው እንደደረሰ በ1988 ዓ.ም በወረዳዋ ላይ በ1955 ዓ.ም በተመሰረተው አለማየሁ በዛብህ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት (በወረዳዋ 4ኛው መሪ ደድአዝማች ደምሴ አባት ስም በአለማየሁ በዛብህ የተሰየመ ነው። (መሪ መሪን ይወልዳል፤ መሪነት የትውልዶች የዱላ ቅብብሎሽ ነው።)) የአንደኛ ክፍል ትምህርታቸውን ጀመሩ። በ1995 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚሁ ት/ቤት በማጠናቀቅ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት አስመዝግበው ወደ 9ኛ ክፍል ተዛወሩ። ......... የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአቶ ልየው አስረስ ቤተሰቦች ትብብርና ድጋፍ በተገነባው ልየው አስረስ ዘውዴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ1996-1997 ዓ.ም ድረስ ተከታትለዋል። (ይህ ት/ቤት በወንድማማቾች በእነ ዘውዴ ልየው፣ ሽታ ልየውና ታሪኩ ልየው በጎ አድራጊነትና በአቶ አውራሪስ ተገኘ አስተባባሪነት የተገነባ ት/ቤት ነው።) የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በ1997 ዓ.ም ወስደው የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል። በወቅቱ ከ1000 በላይ አቻ ተማሪዎች ፈተና ወስደው የመሰናዶ መግቢያ ውጤት ያመጡ 280 ያህሉ ናቸው። እሳቸውም ምንም እንኳ የተሻለ ውጤት ቢያመጡም ምርጫቸውን የመምህርነት ሙያ መማር አደረጉት፤ የዲፕሎማ ትምህርታቸውን በደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከ1998-2000ዓ.ም ተምረው ሰኔ 24 ቀን 2000 ዓ.ም (በአዲሱ ሚሊኒየም) በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ በዲፕሎማ ተመረቁ። ...... ሀምሌ 01ቀን 2000 ዓ.ም በመምህርነት ሙያ በወቅቱ በዲፕሎማ መ/ር መነሻ ደመወዝ ብር 841.00 (አሁን ላይ (2011ዓ.ም ማለት ነው) 2472.00 ሆኗል።) እየተከፈላቸው እንዲሰሩ ዋበር ከተማ በሚገኘው ደድ እየሱስ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት ተቀጠሩ። በመምህርነት ሙያ ያገለገሉት ለ1 አመት ብቻ ነው። በ2002 ዓ.ም በዚሁ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ሆነው ተመድበዋል። በት/ ቤቱም ከ2002 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ለ4 አመት ያህል በርዕሰ መምህርነት አገልግለዋል። በስራ ላይ እያሉም በክረምት መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በትምህርት እቅድና ስራ አመራር ከ2002-2006 ተከታትለው ከፍተኛ ውጤት #3.80 በማስመዝገብ በ2006 መጨረሻ ላይ በከፍተኛ ማዕረግ ተመረቁ። ..... በት/ቤቱ ቆይታቸው የመማር ማስተማር ሂደቱን በውጤታማነት መርተዋል። ት/ ቤቱንም ከማህበረሰቡ ጋር በማገናኘት ስታንዳርዱን ለማሻሻል ጥረት አድርገዋል። አዳዲስ መማሪያ ክፍሎችን፣ የአስተዳደር ቢሮዎችንና ቤተ መጽሃፍት ቤት አስገንብተዋል። ት/ቤቱም በአጥር እንዲከለል አድርገዋል። ት/ ቤቱም የወረዳው ሞዴል ሆኖ ቀጥሏል። ..... አቶ አለባቸው ሽታ ባይነስ ከደድ እየሱስ ት/ቤት ቆይታ በኋላ ሀምሌ 01 ቀን 2005 ዓ.ም የቢቡኝ ወረዳ ህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ም/አማካሪ ሆነው ተሾሙ። በአማካሪነት ከ2006-2007 ዓ.ም ለ2ዓመት ያህል አገልግለዋል። ....... በመቀጠልም ጥቅምት 01/2008 ዓ.ም የቢቡኝ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። በትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊነት ከ2008-2010 ዓ.ም ድረስ መርተዋል። በቆይታቸው ወረዳዋ በትምህርት ስራ እስከ ፌዴራል ድረስ ስሟ እንዲጠራ አድርገዋል። በ2008 ስራ አፈጻጸማቸው ከአማራ ክልል ወረዳዎች ቀዳሚ በመሆን ህዳር 05-06/2009 ዓ.ም አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ላይ በተካሄደው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ተሸላሚ ሆነው ወረዳዋን የ100ሺህ ብር ተሸላሚ አድርገዋል። በ2009 ስራ አፈጻጸማቸውም ከዞኑ ቀዳሚ በመሆን የኮምፒውተር ሽልማት ለወረዳዋ አበርክተዋል። በትምህርት ስራቸውም ከቅድመ መደበኛ ትምህርት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተሳትፎን አረጋግጠዋል። በትምህርት ጥራቱም የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርከተዋል። የትምህርት ቤቶችንም ስታንዳርድ በማሻሻል ድርሻቸውን ተወጥተዋል። በትምህርት ተቋሙ ጠንካራ የስራ ባህልንና አንድነትን ፈጥረዋል። .....21ኛው የቢቡኝ ዋና አስተዳዳሪ ናቸው። በዘመነ አብይ አህመድ ጥቅምት 28 ቀን 2011 አ.ም ተሾሙ ። በአብይ ዘመን የወረዳዋ የመጀመሪያ አስተዳዳሪ ሆነዋል። በእግርጥ ከህወሃታዊ አስተሳሰብ የተላቀቅንበት ዘመን በመሆኑ እንጅ በኢህአዴግ ዘመን 7ኛው አስተዳዳሪም ጭምር ናቸው። ወረዳዋ ከተመሰረተችበት 1950ዎቹ ጀምሮ የወረዳዋ አራተኛው ትውልድ መሪ ሆነው በመመረጣቸው እድለኛ ሰው ናቸው። ..... አቶ አለባቸው ሽታ ባይነስ በቢቡኝ ወረዳ አስተዳደር ድጎ ቃንጣ ቀበሌ ልዩ ስሙ ድጎ ማርያም በተባለው ክቡር መንደር ጥቅምት 23 ቀን 1979 ዓ.ም ከአባታቸው ቄስ ሽታ ባይነስ አለምነህ ትርፌ ከእናታቸው ከወ/ሮ አዋግ መኮንን አለሙ 7ኛ ልጅ ሆነው ተወለዱ። 7ኛ ልጅ በመሆናቸውም የወረዳዋ 7ኛ መሪ በመሆን ተመርጠዋል። ........ እድሜያቸው እንደደረሰ በ1988 ዓ.ም በወረዳዋ ላይ በ1955 ዓ.ም በተመሰረተው አለማየሁ በዛብህ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት (በወረዳዋ 4ኛው መሪ ደድአዝማች ደምሴ አባት ስም በአለማየሁ በዛብህ የተሰየመ ነው። (መሪ መሪን ይወልዳል፤ መሪነት የትውልዶች የዱላ ቅብብሎሽ ነው።)) የአንደኛ ክፍል ትምህርታቸውን ጀመሩ። በ1995 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚሁ ት/ቤት በማጠናቀቅ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት አስመዝግበው ወደ 9ኛ ክፍል ተዛወሩ። ......... የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአቶ ልየው አስረስ ቤተሰቦች ትብብርና ድጋፍ በተገነባው ልየው አስረስ ዘውዴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ1996-1997 ዓ.ም ድረስ ተከታትለዋል። (ይህ ት/ቤት በወንድማማቾች በእነ ዘውዴ ልየው፣ ሽታ ልየውና ታሪኩ ልየው በጎ አድራጊነትና በአቶ አውራሪስ ተገኘ አስተባባሪነት የተገነባ ት/ቤት ነው።) የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በ1997 ዓ.ም ወስደው የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል። በወቅቱ ከ1000 በላይ አቻ ተማሪዎች ፈተና ወስደው የመሰናዶ መግቢያ ውጤት ያመጡ 280 ያህሉ ናቸው። እሳቸውም ምንም እንኳ የተሻለ ውጤት ቢያመጡም ምርጫቸውን የመምህርነት ሙያ መማር አደረጉት፤ የዲፕሎማ ትምህርታቸውን በደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከ1998-2000ዓ.ም ተምረው ሰኔ 24 ቀን 2000 ዓ.ም (በአዲሱ ሚሊኒየም) በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ በዲፕሎማ ተመረቁ። ...... ሀምሌ 01ቀን 2000 ዓ.ም በመምህርነት ሙያ በወቅቱ በዲፕሎማ መ/ር መነሻ ደመወዝ ብር 841.00 (አሁን ላይ (2011ዓ.ም ማለት ነው) 2472.00 ሆኗል።) እየተከፈላቸው እንዲሰሩ ዋበር ከተማ በሚገኘው ደድ እየሱስ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት ተቀጠሩ። በመምህርነት ሙያ ያገለገሉት ለ1 አመት ብቻ ነው። በ2002 ዓ.ም በዚሁ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ሆነው ተመድበዋል። በት/ ቤቱም ከ2002 እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ለ4 አመት ያህል በርዕሰ መምህርነት አገልግለዋል። በስራ ላይ እያሉም በክረምት መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በትምህርት እቅድና ስራ አመራር ከ2002-2006 ተከታትለው ከፍተኛ ውጤት #3.80 በማስመዝገብ በ2006 መጨረሻ ላይ በከፍተኛ ማዕረግ ተመረቁ። ..... በት/ቤቱ ቆይታቸው የመማር ማስተማር ሂደቱን በውጤታማነት መርተዋል። ት/ ቤቱንም ከማህበረሰቡ ጋር በማገናኘት ስታንዳርዱን ለማሻሻል ጥረት አድርገዋል። አዳዲስ መማሪያ ክፍሎችን፣ የአስተዳደር ቢሮዎችንና ቤተ መጽሃፍት ቤት አስገንብተዋል። ት/ቤቱም በአጥር እንዲከለል አድርገዋል። ት/ ቤቱም የወረዳው ሞዴል ሆኖ ቀጥሏል። ..... አቶ አለባቸው ሽታ ባይነስ ከደድ እየሱስ ት/ቤት ቆይታ በኋላ ሀምሌ 01 ቀን 2005 ዓ.ም የቢቡኝ ወረዳ ህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ም/አማካሪ ሆነው ተሾሙ። በአማካሪነት ከ2006-2007 ዓ.ም ለ2ዓመት ያህል አገልግለዋል። ....... በመቀጠልም ጥቅምት 01/2008 ዓ.ም የቢቡኝ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። በትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊነት ከ2008-2010 ዓ.ም ድረስ መርተዋል። በቆይታቸው ወረዳዋ በትምህርት ስራ እስከ ፌዴራል ድረስ ስሟ እንዲጠራ አድርገዋል። በ2008 ስራ አፈጻጸማቸው ከአማራ ክልል ወረዳዎች ቀዳሚ በመሆን ህዳር 05-06/2009 ዓ.ም አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ላይ በተካሄደው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ተሸላሚ ሆነው ወረዳዋን የ100ሺህ ብር ተሸላሚ አድርገዋል። በ2009 ስራ አፈጻጸማቸውም ከዞኑ ቀዳሚ በመሆን የኮምፒውተር ሽልማት ለወረዳዋ አበርክተዋል። በትምህርት ስራቸውም ከቅድመ መደበኛ ትምህርት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተሳትፎን አረጋግጠዋል። በትምህርት ጥራቱም የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርከተዋል። የትምህርት ቤቶችንም ስታንዳርድ በማሻሻል ድርሻቸውን ተወጥተዋል። በትምህርት ተቋሙ ጠንካራ የስራ ባህልንና አንድነትን ፈጥረዋል። ..... አሁን ላይ አቶ አለባቸው ሽታ እያስመዘገቡት የመጡትን ለውጥ በመገንዘብና የስራ ታታሪነታቸውን እንዲሁም ሩቅ አሳቢነታቸውንና ሰው አክባሪነታቸውን በማሰብ በወረዳው ህዝብ ግፊት የቢቡኝ አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱም ጥቅምት 28/2011ዓ.ም ተሰጣቸው። መልካም የስራ ዘመን ተመኜንላቸው!! አሁን ላይ አቶ አለባቸው ሽታ እያስመዘገቡት የመጡትን ለውጥ በመገንዘብና የስራ ታታሪነታቸውን እንዲሁም ሩቅ አሳቢነታቸውንና ሰው አክባሪነታቸውን በማሰብ በወረዳው ህዝብ ግፊት የቢቡኝ አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱም ጥቅምት 28/2011ዓ.ም ተሰጣቸው። መልካም የስራ ዘመን ተመኜንላቸው!!