አል ናይት ሎንግ (አል ናይት)

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
«አል ናይት ሎንግ (አል ናይት)»
ሪቺ በ2011 እ.ኤ.አ. ዘፈነው
ላዮነል ሪቺ ዘፈን ከካንት ስሎ ዳውን አልበም
የተለቀቀው 30 August1983 እ.ኤ.አ.
የተቀዳው 1983 እ.ኤ.አ.
ስልት ዳንስ ፖፕ ሙዚቃ
ርዝመት 6:19 (አልበም) 4:20 (7")
ቋንቋ እንግሊዝኛ*
አሳታሚ ላዮነል ሪቺ፣ ጄምስ ካርማይክል
ግጥም ላዮነል ሪቺ
ቅንብር ሞታውን ሬኮርድስ


«አል ናይት ሎንግ (አል ናይት)» (All Night Long (All Night)) ከ1983 እ.ኤ.አ. (1975 ዓም) የሆነ የላዮነል ሪቺ ነጠላ ዘፈን ነው። ከሁለተኛ (ለብቻው ያለ ዘ ኮሞዶርዝ ቡድኑ) አልበሙ ካንት ስሎ ዳውን ነው፤ በብዙ አገራት በዚያው አመት እስከ #1 ሥፍራ ድረስ ፈለቀ። ዓለም ዙሪያ ተወደደና በሌሎችም ተቀርጿል። በዐረብኛም አገራት አሁንም ይወደዳል።

2013 እ.ኤ.አ. (2006 ዓም) በታተመ ቃለ መጠይቅ፣ ላዮነል ስለ ዘፈኑ የሚከተሉትን አዲስ መረጃዎች ገልጿል።

  1. በመጀመርያ ለዚህ ዜማ አርእስት አነበረውም። አርእስቱን ያገኘው እንዳጋጣሚ አንድ ጃማይካዊ ሃኪም የሆነ ጓደኛው «አል ናይት ሎንግ» ሲል ያንጊዜ ዝም ብሎ አወቀው።
  2. የ«አፍሪከኛ» ቃላቶች እንቶ ፈንቶ (ለማዝናናት) ናቸው እንጂ በውነት ቋንቋ አይደለም። የውነተኛ ቋንቋ ፈልጎ ነበር፣ ግን የሚስማማ አፍሪካዊ አረፍተ ነገሮች ለማግኘት ጊዜ አልነበረውም። ስለዚህ ከልቡ ፈጠረው።
  3. ቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ብዙ አሜሪካዊ ሙዚቃ ባይፈቅድም ይህና ሌሎች የላዮነል ሪቺ ዘፈኖች ተፈቅደዋልና እንግሊዝኛን ለማስለምድ በትምህርት ቤት እንኳ ተጠቅመዋል።
  4. ዘፈኑ ሲወጣ የ«ኤምቲቪ» ጣቢያ ገና አዲስ ነበር። ብዙ የጥቁር ዛፋኞች ሙዚቃ አናጫወትም ብለው ነበር። ሆኖም በተመልካቾቻቸው ምርጫ #1 ስለ ሆነ ሀሣባቸውን ቀየሩ።
  5. በቅርብ ያልፉት የኦፔራ ሙዚቃ አንጋፋ ዘማሪ ሉቻኖ ፓቫሮቲ ከሁሉ የሚወዱት ዘፈን ብለውታል።[1]


  1. ^ http://nypost.com/2013/09/21/five-surprising-facts-about-richies-classic-all-night-long/