አል ናይት ሎንግ (አል ናይት)
Appearance
«አል ናይት ሎንግ (አል ናይት)» | |
---|---|
የላዮነል ሪቺ ዘፈን ከካንት ስሎ ዳውን አልበም | |
የተለቀቀው | 30 August፣ 1983 እ.ኤ.አ. |
የተቀዳው | 1983 እ.ኤ.አ. |
ስልት | ዳንስ ፖፕ ሙዚቃ |
ርዝመት | 6:19 (አልበም) 4:20 (7") |
ቋንቋ | እንግሊዝኛ* |
አሳታሚ | ላዮነል ሪቺ፣ ጄምስ ካርማይክል |
ግጥም | ላዮነል ሪቺ |
ቅንብር | ሞታውን ሬኮርድስ |
«አል ናይት ሎንግ (አል ናይት)» (All Night Long (All Night)) ከ1983 እ.ኤ.አ. (1975 ዓም) የሆነ የላዮነል ሪቺ ነጠላ ዘፈን ነው። ከሁለተኛ (ለብቻው ያለ ዘ ኮሞዶርዝ ቡድኑ) አልበሙ ካንት ስሎ ዳውን ነው፤ በብዙ አገራት በዚያው አመት እስከ #1 ሥፍራ ድረስ ፈለቀ። ዓለም ዙሪያ ተወደደና በሌሎችም ተቀርጿል። በዐረብኛም አገራት አሁንም ይወደዳል።
በ2013 እ.ኤ.አ. (2006 ዓም) በታተመ ቃለ መጠይቅ፣ ላዮነል ስለ ዘፈኑ የሚከተሉትን አዲስ መረጃዎች ገልጿል።
- በመጀመርያ ለዚህ ዜማ አርእስት አነበረውም። አርእስቱን ያገኘው እንዳጋጣሚ አንድ ጃማይካዊ ሃኪም የሆነ ጓደኛው «አል ናይት ሎንግ» ሲል ያንጊዜ ዝም ብሎ አወቀው።
- የ«አፍሪከኛ» ቃላቶች እንቶ ፈንቶ (ለማዝናናት) ናቸው እንጂ በውነት ቋንቋ አይደለም። የውነተኛ ቋንቋ ፈልጎ ነበር፣ ግን የሚስማማ አፍሪካዊ አረፍተ ነገሮች ለማግኘት ጊዜ አልነበረውም። ስለዚህ ከልቡ ፈጠረው።
- በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ብዙ አሜሪካዊ ሙዚቃ ባይፈቅድም ይህና ሌሎች የላዮነል ሪቺ ዘፈኖች ተፈቅደዋልና እንግሊዝኛን ለማስለምድ በትምህርት ቤት እንኳ ተጠቅመዋል።
- ዘፈኑ ሲወጣ የ«ኤምቲቪ» ጣቢያ ገና አዲስ ነበር። ብዙ የጥቁር ዛፋኞች ሙዚቃ አናጫወትም ብለው ነበር። ሆኖም በተመልካቾቻቸው ምርጫ #1 ስለ ሆነ ሀሣባቸውን ቀየሩ።
- በቅርብ ያልፉት የኦፔራ ሙዚቃ አንጋፋ ዘማሪ ሉቻኖ ፓቫሮቲ ከሁሉ የሚወዱት ዘፈን ብለውታል።[1]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |