አሚ-ሳዱቃ

ከውክፔዲያ
(ከአሚሳዱቃ የተዛወረ)
የአሚ-ሳዱቃ ዘሃራ ጽላት

አሚ-ሳዱቃ ከ1559 እስከ 1538 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን ንጉሥ ነበረ። አባቱን አሚ-ዲታናን ተከተለው።

ለአሚ-ሳዱቃ ዘመን 21 የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል። እነዚህ የዓመት ስሞች ባብዛኛው ስለ አረመኔ መቅደስና ሥርዓት የሚነኩ ናቸው። ምንም ዘመቻ ስለማይጠቅሱ ስላማዊ ዘመን እንደ ሆነ ይመስላል። በ2ኛውና እንደገና በ10ኛው ዓመት የሕዝብ ዕዳዎች እንደ ሠረዘ ይላሉ። ለዚሁም የአዋጅ ሰነዱ ታውቆ የአሞራውያንአካዳውያን ወገኖች እኩልነት እንዳረጋገጠ ታውቋል።

በንጉሥ አሚ-ሳዱቃ ዘመን በ8ኛው ዓመት የዘሃራ ሁኔታና አቀማመጥ «የአሚ-ሳዱቃ ዘሃራ ጽላት» በተባለው ሰነድ በደንብ ስለ ተመዘገበ፣ ይህ የታሪክ ሊቃውንት ዘመኑን ለመወሰን ረድቷል። ስለዚሁ የሥነ ፈለክ ቁጠራ፣ የአሚ-ሳዱቃ 8ኛው አመት ወይም በ1702፣ በ1646፣ በ1582፣ ወይም በ1550 ዓክልበ. እንደ ተከሠተ ታወቀ። ዛሬ የአንዳንድ አገራት ታሪክ ሊቃውንት «መካከለኛ አቆጣጠር» የተባለውን ሲቀበሉ፣ የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1646 እና የባቢሎን ውድቀት በ1603 ዓክልበ. የሚወስኑት ናቸው። አለዚያ «አጭር አቆጣጠር» ተከትለው የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1582፣ የባቢሎንም ውድቀት በ1539 ዓክልበ. ያደርጉታል።

ባለፈው ቅርብ ጊዜ ግን በሥነ ቅርስ እርምጃ ሳቢያ የአሦር ነገሥታት ዘመናት ቁጥር ለማወቅ ስለ ተቻለ፣ የፈረንሳይ ሊቅ ዤራርድ ዠርቱ «ከሁሉ አጭሩ» ('ኡልትራ አጭር' ወይም 'አብልጦ አጭር') አቆጣጠር በትክክል እንደሚስማማው አስረድቷል።[1] የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1550፣ የባቢሎንም ውድቀት በ1507 ዓክልበ. ሆነ (ወይም ክ.በ. በ1499 እንደ ኤውሮጳውያን አቆጣጠር) ለማለት እንችላለን ማለት ነው።


የአሚ-ሳዱቃ ተከታይ ልጁ ሳምሱ-ዲታና ነበረ።

ቀዳሚው
አሚ-ዲታና
ባቢሎን ንጉሥ
1559-1538 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሳምሱ-ዲታና

የውጭ መያያዣ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ http://chronosynchro.net/base.php?page=accueil (ፈረንሳይኛ)