አማርኛ ተረት ምሳሌዎች

ከውክፔዲያ

እውቀት

አስመሣይ "ሁለት ጊዜ በላህ ተፋህ ሁለት ጊዜ ተናገርህ ከፋህ"

ሁለት ጊዜ ነው የዶሮ ልደት አንዱ በእንቁላል አንዱ በጫጩት

ሁለት ጊዜ ይፈርዱ ጉድ ይወልዱ

ሁለት ጥፉ ካገር ይጥፉ

ሁሉ ሄደ ተበተነ እህና እኔ ቀረነ አለ ያዘነ

ሁሉ ሆነ ቃልቻ ማን ይሸከም ስልቻ

ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ

ሁሉ ቢናገር ማን ይሰማል

ሁሉ አማረሽን ዲስኮ (disco) አታውጧት ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት ሁሉ አማረኝን ገበያ አታውጣት

ሁሉ አረሰ ማን ይሸምት

ሁሉ የሚገኝ ከእሱ የሚገኝ የለም ያለእርሱ

ሁሉ ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል

ሁሉ ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል

ሁሉም ሰው መምሰሉ ባይታይ አመሉ

ሁሉም ሸክሙን ፍቅርም ያዥውን

ሁሉም በየዘመድህ ቢሉት አክንባሎ ጋጥ ገባ ሁሉም በየዘርህ ቢሉት አከንባሎ ጋጣ ገባ

ሁሉም አካል ነው ግን እንደአይን አይሆንም

ሁሉም ከልኩ አያልፍም ሁሉም ከኋላው ያገኘዋል እንደስራው ሁሉም ወንፈሉን ፈታይም ድውሩን ሁሉም ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል ሁሉም ያልፋል የሚኮርጅም ቢሆን ሁሉም ያልፋል ግን እስኪያልፍ ያለፋል ሁሉን ለእኔ አትበል ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል ሁሉን አውቆ አሳውን እሾህ ከስጋው ለይቶ ሁል ጊዜ ባሬራ ትበያለሽ ወይ አንዳንድ ጊዜ እንኳ ወጥ አትይሞይ ሁል ጊዜ ከመደንገጥ አንድ ጊዜ መሸጥ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሂዳ ጉበት ቢነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች ሂዳ ጉበት የነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች ሂዳ ጉበት ይነሷታል ታናሽ ታላቅ ላኩልኝ አለች ሂድ አትበለው እንደሚሄድ አርገው ሂድ አትበለው እንዲሄድ አድርገው ሂድ ካገር ኑር ካገር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም ህልም አለ ተብሎ ሳይተኛ አይታደርም ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በሰጠኝ ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በተወኝ ህመሙን የሸሸገ መድሀኒት የለውም ህመሙን የደበቀ መድሀኒቱም አልታወቀ ህመሙን የደበቀ መድሀኒት የለውም ህያዋን ለነገስታት ሙታን ለካህናት ይገብራሉ ህዳር መማረሪያ ሰኔ መቃጠሪያ ህግ ይኖራል ተተክሎ ስርአት ይኖራል ተዛውሮ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሆሆሆ ስቄ ልሙት አለ ሰውየው ሆቴል ቢያብር ገንዘብ ያስገኛል ሆደ ሰፊ ነገር አሳላፊ ሆደ ሰፊ ይሻላል ከአኩራፊ ሆዱ ሲሞላ ፍቅሩ ሌላ ሆዱ ሲጎድል ሰው ያጋድል ሆዱ ናረት ሙያው ከጅረት ሆዱ ወድዶ አፉ ክዶ ክፉ ለምዶ ሆዱ ፈሪ እግሩ ዳተኛ አዳም ሲዋጋ እርሱ ይተኛ ሆዱን የወደደ ማእረጉን የጠላ ሆዱን የወደደ ማእረጉን ይጠላል ሆዱን ያለ ሆዱን ተወጋ ሆዳም ሰው እንብርት የለውም ሆዳም ቢሸከም የበላ ይመስለዋል ሆዳም ቢፈተፍት የጠገበ ይመስለዋል ሆዳም ፍቅር አያውቅም ሆዴ ሆዴ የሚለውን ጌታ ያየዋል አይኔ አይኔ የሚለውን ሰው ያየዋል ሆዴ በጀርባዬ ቢሆን ገፍቶ ገደል በጣለኝ ሆዴ ኑር በዘዴ ሆዴ አታጣላኝ ከዘመዴ ሆዴን በልቶኝ ጎኔን ቢያኩኝ አይገባኝ ሆድ ሆዴን የምትል ወፍ አለች ምናለች ሆድ ለማታ በልቶ ለጠዋት ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው ሆድ ለባሰው ቢላዋ አታውሰው ሆድ ለተተባሰው ማጭድ አታውሰው ሆድ ሲሞላ ራስ ባዶ ይቀራል ሆድ ሲያር ጥርስ ይስቃል ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ጠዋት ሆድ ባዶ ይጠላል ሆድ ባዶን ይጠላል ሆድ እንዳሳዩት ነው ሆድ ከሁዳድ ይስፋል ሆድ ካገር ይስፋል ሆድ ወዶ አፍ ክዶ ክፉ ለምዶ ሆድ ዘመድ ሳይወድ አፍ እህል ሳይለምድ ሆድ የሸሸገውን ብቅል ያወጣዋል ሆድ የኔ ነው ሲሉት ቁርጠት ሆኖ ይገድላል ሆድ ያበላውን ያመሰገናል ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል ሆድህን ጎመን ሙላው ጀርባህን ለጠላት አታሳየው ሆድና ግንባር አይሸሸጉም ሆድና ግንባር አይሸሸግም ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ለሀምሳ ጋን አንድ አሎሎ ይበቃል ለሀብት መትጋት ሰውነትን ያከሳል ገንዘብን ማሰብ እንቅልፍ ይነሳል ለሀጥአን የወረደ ለጻድቃን ይተርፋል ለሁሉም ጊዜ አለው ለሂያጅ የለውም ወዳጅ ለህልም ምሳሌ የለውም ለሆዳም ሰው ማብላት ውቅያኖስን ለመደልደል መቃጣት ለሆዳም በሬ ገለባ ያዝለታል ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል ለሆዳም በሬ ቫት ተከፈለ ለሆዳም በቅሎ ጭድ ያዝለታል ለሆዴ ጠግቤ በልብሴ አንግቤ ለሆድ ቁርጠት ብላበት ለራስ ምታት ጩህበት ለላሙ መንጃ ለሸማው መቅደጃ ለላሙ መንጃ ለሸማው መከንጃ ለላም ቀንዷ አይከብዳትም ለላም ከጥጃዋና ከአላቢዋ ማን ይቀርባታል ለላም የሳር ለምለም ለላም ጥጃዋ ለአህያ ውርንጭላዋ ለሌለው ምን ትለው ለሌባ ቅሌት ልብሱ ነው ለልደት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ለልጅ ሲሉ ይበሉ ለወዳጅ ሲሉ ይጠሉ ለልጅ ሲሉ ይበሉ ለወገን ሲሉ ይጠሉ ለልጅ አይስቁለትም ለውሻ አይሮጡለትም ለልጅ ከሳቁለት ለውሻ ከሮጡለት ለልጅ ጥርስህን ለዝንብ ቁስልህን ለልጅ ጨዋታ ለባለጌ ቧልታ ለሎሌው ምን ትለው ለመሀን እምዬ ለአገልጋይ እትዬ ብርቋ ነው ለመሄድና ለመላወስ አዛዥ ራስ ለመሄድና ለመመለስ አዛዥ ራስ ለመሆኑ ሳይሆን እንዴት ይሆናል ቢሆን ለመማር ክፍል መግባት ለመኮረጅ ካሮት መብላት ለመማር ክፍል መግባት ለማለፍ ካሮት መብላት ለመስማት የፈጠንህ ለመናገርና ለቁጣ የዘገየህ ሁን ለመስማት የፈጠንህ ለመናገር የዘገየህ ሁን ለመስራት የሚያፍር መብላት አይደፍርም ለመስራት ያፈረ ለመብላት ደፈረ ለመስጠት አለመቸኮል ከሰጡም ወዲያ አለመጸጸት ለመነኩሴ መልካም ሎሌ ለመታማት መፍራት ለመከራ ያለው መነኩሴ ዳዊቱን ሸጦ አህያ ይገዛል ለመከራ የጣፈው ቢነግድ አይተርፈው ለሙት የለው መብት ለሚመለከት ለሚያየው ሞት ቅርብ ነው ለሚስት ያጎርሷል ለተመታ ይክሷል ለማረም ማን ብሎት ሲሰራው ግን ግድፈት ለማን አለው ፈጣሪ አለው ጠጅ ለሌለው ውሀ አለው ለማን ይፈርዱ ለወደዱ አይደለም ለወለዱ ለማኝ ቢያብድ ስልቻውን አይጥልም ለማኝ አያማርጥም ማር አይኮመጥጥም ለማየት የፈለገ አይኑን ይገልጣል ለማያቅህ ታጠን ብሎሀል ሀሰን ለማያውቅ ፎገራ ዱሩ ነው ለማያውቁሽ ታጠኚ ለማያውቁሽ ታጥበሽ ቅረቢ ለማይሞት መድሀኒት አለው ለማይሰጥ ሰው ስጡኝ ማለትን ማን አስተማረው ለማይሰጥ ሰው ስጡኝን ማን አስተማረው ለማእበል ወደብ ለነፋስ ገደብ የለውም ለምሽት መብራት ለመከራ ጊዜ ብልሀት ለምክንያት ምክንያት አለው ለምን ላለው ፈጣሪ አለው ጠጅ ለሌለው ውሃ አለው ለምን ሰርግ ይሄዳል ሰርግ አለ በቤቱ ለምን ተክዤ አምላክን ይዤ ለምን ያለው ስልቻውን ጫን ያለው ኮርቻውን ለምን ያለው ስልቻውን ጫን ያለው ኮርቻውን አያጣም ለምን ጊዜው ነቀዝሽ ለምኖ ለማኝ ቆቤን ቀማኝ ለሞኝ ሰኔ በጋው መስከረም ክረምቱ ለሞኝ ንገረው ምን ይሰማ ብዬ ለብልህ ንገረው ምን ይሳተው ብዬ ለሞኝ ከሳቁለት ለውሻ ከሮጡለት ለሞኝ ጉድጓድ አያሳዩትም ቤት ነው ብሎ ይገባበታል ለሞፈር ቆራጭ እርፍ አይታየውም በግላጭ ለረዥም ሰው ልብ እና ልብስ ያጥረዋል ለረዥም መንገድ አትሩጥበት ለረዥም ነገር አትቸኩልበት ለራሱ አያውቅ ነዳይ ቅቤ ለመነ ላዋይ ለራሱ አያውቅ ጠንቋይ መድሀኒቱ ላዋይ ለራሱ ጥላ ለእግሩ ከለላ ለራሱ የማይረባ ለሌላም አይረባ ለራሱ የማይረባ ለሰውም አይረባ ለራስ ምታት ጩህበት ለሆድ ቁርጠት ብላበት ለራሱ አያውቅ ሰው አይጠይቅ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ለራስ ቢያወሩ ለቅንቅን ይዘሩ ለራስ ቢያወሩ ለቅንቅን ይዘሩ አለች ዶሮ ለራስ ከበጁ አይታጡ ደጁ ለራበው ሰው ቆሎ ለቁልቁለት በቅሎ ለራበው ባዶ መሶብ ማቅረብ ለራት የማይተርፍ ዳረጎት ለርስት ሴቶች ስንኳ ይሞቱበታል ለሰማይ ምሰሶ የለው ለባእድ ስር የለው ለሰለባ የመጣ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስ ለሰለባ የመጣ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስም ለሰበበኛ ቂጥ መረቅ አታብዛበት ለሰባቂ ጆሮህን አትስጠው ለሰው ልጅ ሲያበሉ ለውሻ ልጅ ያብሉ ለሰው ልጅ ከሚያበሉ ለውሻ ልጅ ያብሉ ለሰው ልጅ ከማብላት ለውሻ ልጅ ማብላት ለሰው ልጅ እውቀት ለጦጣ ብልጠት ለሰው ሞት አነሰው ለሰው ሞት አነሰው ውሻውንስ ፈሴ መለሰው አለች ቀበሮ ለሰው ቢነግሩት ለሰው ለሰው ቢናገሩ መልሶ ለሰው ጫር ጫር አድርጌ አፈር ላልብሰው ለሰው ብሎ መሞት አምላክነት ያሻል ለሰው ብሎ ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ ለሰው ብትል ትጠፋለህ ለእግዜር ብትል ትለማለህ ለሰው እንግዳ ላገሩ ባዳ ለሰው እንዴት F አነሰው ለሰው ከበሬታው ሰው ለወጥ ማጣፈጫው ጨው ለሰው ጠላቱ ይወጣል ከቤቱ ለሰው የማይል ሰው ሞትም ሲያንሰው ለሰው ብሎ ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ ለሴትና ለጉም አይዘነጉም ለሰይጣን አትስጠው ስልጣን ለእሳት ውሀ ለጸጉር ቡሀ ለሴት ልጅ እስከአርባ ቀን ሞቷን ከዚያ ወዲያ ሀብቷን ለሴት ምስጢር ማውራት በወንፊት መቅዳት ለሴት ምክር አይገባትም ለሴትና ለጉም አይዘነጉም ለሴት ጠላ ለፈረስ ቆላ ለስሟ መጠሪያ ቁና ሰፋች ለስሱ ፍትፍት አሳይቶ እበት ያጎርሷል ለሸማኔ ማገጃ ስለት ማረጃ ለሹመት ካልመከሩለት ለጥርስ ካልነከሩለት ለሹመት ካልመከሩለት ለጥርስ ካልከደኑለት ለሹመት ያደለው የለማኝ አለቃ ይሆናል ለሺ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ ለቀላል ምስጢር መንገር በቀዳዳ ጤፍ መቋጠር ለቀላል ሰው ምስጢር መንገር በቀዳዳ ጤፍ መቋጠር ለቀላል ሰው ምስጢር መንገር በቀዳዳ አቁማዳ ጤፍ መቋጠር ለቀማኛ የለውም እጅ ለበቅሎ የለውም ልጅ ለቀበጠች አማት ሲሶ በትር አላት ለቀባሪው አረዱት ለቀን ቀጠሮ ለሴት ወይዘሮ ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው ቀንዱ ይከልክለው ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው ቀንዱ ይከለክለዋል ለቁንጫ ለምጽ ያወጣል ለቁንጫ መላላጫ ለቂጡ ጨርቅ የለው ቆንጆ ያባብላል ለቅልብልብ አማት ሲሶ በትር አላት ለቅሶ ሳለ ከቤት ይሄዳል ጎረቤት ለቅናት የለውም ጥናት ለቅዘን እግር አንስተውለት ለውሻ ሮጠውለት ለቆመ ሰማይ ቅርቡ ነው ለቆማጣ አንድ ጣት ብርቁ ናት ለበራ ወለባ ለውሻ ገለባ ለበጋ ጥጃ ውስ አነሰው ወይ ለበግ ደጋ ለምቾት አልጋ ለቡናሽ ቁርስ የለሽ ለነገርሽ ለዛ የለሽ ለባለጌ ገድሉ ውርደቱ ለቤት ሳማ ለውጭ ቄጤማ ለቤት ሳንቃ ለሰው አለቃ ለቤት ሳንቃ ለነገር ጠበቃ ለቤት ባላ ለችግር ነጠላ ለብልህ ንገረው ምን ይስተው ብዬ ለሞኝ ንገረው ምን ይገባው ብዬ ለብልህ አይነግሩ ለድመት አያበሩ ለብልህ አይነግሩ ላንበሳ አይመትሩ ለብልህ አይነግሩ ለንጉስ አይመክሩ ለብልህ አይነግሩም ለንጉስ አይመክሩም ለብልህ አይነግሩ ካልጠየቀ በስተቀር ለተማሪ ቆሎ ለወታደር በቅሎ ለተሟጋች መዘዘኛ የዳኛ ትእግስተኛ ለተረታው ያበደረ እሳት ጨመረ ለተራበ ግብር ለተበደለ ነገር ለተራበ በግብር ለተበደለ በነገር ለተራበ ቂጣ ለተጠማ ዋንጫ ለተሸሸገ ምግብ የተሸሸገ ሆድ አይጠፋለትም ለተሾመ ይሟገቱለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል ለተሾመው ይመሰክሩለታል ለተሻረው ይመሰክሩበታል ለተሾመ ይመሰክሩለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው ለተባባሰው ማጭድ አታውሰው ለተንኮለኛ ሲሉ ይሰበስባሉ ለቅን ይፈርዳሉ ለተወገረ የማያዝን እንብርት የለውም ለትኋን ልጓም ማጉረስ ላፈኛ ሰው መመለስ ለትኋን ልጓም ማጉረስ ላፈኛ ሰው መመለስ አይቻልም ለቸኮለ ሰው ዋንጫ አስጨብጠው ለችግር የፈጠረው ቢነግድ አይተርፈው ለነገረኛ ሰው ጀርባህን ስጠው ለነገረኛ ነገር ተውለት ለሆዳም እህል አቅርብለት ለኔ ነግ በኔ ለንጉስ የማይገዛ ለእግዚአብሄር አይገዛ ለንጉስ ያልረዳ ከባህር የማይቀዳ ለንጉስ ያልረዳ ከባህር ያልቀዳ ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበዋል ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበው ለአህያ ማር አይጥማትም ለአምላክ ልንገረው ለማያስቀረው ለአበባ የለው ገለባ ለአቤቱታ የለው ይሉኝታ ለአንበሳ አታበድር ካበደርክ አትጠይቅ ለአንተ ያለውን እንጀራ ይሻግታል እንጂ ማንም አይበላውም ለአኩራፊ ምሳው እራት ይሆነዋል ለአይነ ስውር መስተዋት ለአይንና ለወዳጅ ጥቂት ይበቃል ለአይን የሚከፋ ለአፍንጫ ይከረፋ ለአዋጅ ነጋሪት ለጥጥ ልቃቂት ለአገሩ እንግዳ ለሰው ባዳ ለአፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል ለአፉ ለከት የለውም ለአፍታ የለውም ፋታ ለአፍ ዳገት የለውም ለእሳት እንጨት ካልነሱት አይጠፋም ለእሳት እንጨት ካልነፈጉት አይጠፋም ለእሳት ውሀ ለጸጉር ቡሀ ለእሳት ፍላት ለጮማ ስባት ለእበጥ ፍላት ለእንጨት እሳት ለእባብ እግር የለው ለሞኝ መላ የለው ለእብለት ስር የለው ለእባብ እግር የለው ለእብለት ስር የለውም ለእባብ እግር የለውም ለእበጥ ፍላት ለእንጨት እሳት ለእኔ እናት ምን ደላት ያም አፈር ያም ድንጋይ ጫነባት ለእውር ዝማሜ ለመላጣ ጋሜ ለእጅ ርቆ ለአይን ጠልቆ ለእግሩ የተጠየፈ ለቂጡ አተረፈ ለእግር የፈሩት ለቂጥ ይተርፋል ለእግዚአብሄር የቀነቀነ ለጽድቅ ለጌታ የቀነቀነ ለወርቅ ለእውነት ማማ ለውሸት ጨለማ ለከለላ ጥላ ቢርብህ ብላ ለከሳሽ የለው መላሽ ለካህን ጥምቀት ለገበሬ ግንቦት ለክፋት ያደለው አሳዳጊ የበደለው ለኮ መሳቢያ ወፍጮ ማላሚያ ለወሬ ሞትሁ ለወሬ ሞትሁ ለእህል ሰለፍኩ ለወሬ ወዳጁ ወሬ ለመነኩሴ ጥሬ ለወሬ የለው ፍሬ ለወሬ የለው ፍሬ ለአበባ የለው ገለባ ለወሬ የቸኮለ እናቱን በመንገድ ይረዳል ለወርቅ ያሉት አንገት ላሽክት ለወታደር ሰፊ መንደር ለወዲላ መልካም ዱላ ለወይዘሮ መልካም ዶሮ ለወደላ መልካም ዱላ ለወዳጅ የማር ወለላ ለጠላት አሜኬላ ለወዳጅና ለአይን ትንሽ ይበቃዋል ለወጡም እዘኑለት ከእንጀራውም ጉረሱለት ለወጡ ጊዜስ ከደረቁም ለወጡም እዘኑለት ከደረቁም ብሉለት ለወጥ የሚሻል ቅልውጥ ለዋንጫ ቡሽ ለውሀ ጉሽ የለውም ለዋስ አፍ የለው ለጉንዳን ደም የለው ለውሻ ምሳ የለው ራት ብቻ ለውሻ ሞት ፊት አይነጩለትም ለውሻዬ ያልሁትን ልጄ ቢበላብኝ አልወድም ለውሽማ ሞት ፊት አይነጩለትም ለውጡኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ ለዘመዴ ያዝናል ሆዴ ለዚህ ሆዴ ጠላኝ ዘመዴ ለዝናም ጌታ ውሀ ነሱ ለዝናም ጌታ ውሀ ነሱት ለዝንብ ከትላንት ወዲያም ድሮ ነው ለይቶ እንደፈፋ አንጓሎ እንዳረፋ ለይቶት አባ ንጉሷ ለደህና ሰው ዋጋ አነሰው ለደህና ሰው ውሸት ለጅብ እሸት ለደብተራ መቋሚያና ጭራ ለደደብ ማስረዳት ድንጋይ ቅቤ መቀባት ለደግ ንጉስ እለት እለት ማልቀስ ለዳርቻው ሲሳሱ መካከሉን ተነሱ ለዳርቻው ሲሳሱ ከነመሀሉም ተነሱ ለዳባ ለባሽ ነገርህን አታበላሽ ለዳኛ አመልክት እንዲሆን መሰረት ለዳኛ የነገሩት በርጥብ ያቃጠሉት ለዳኛ ዳኛ አለው ለአንበሳ ተኩላ አለው ለድሀ ማን ሰጠው ውሀ ለድህነት የፈጠረው ቢነግድ አይተርፈው ለድህነት የፈጠረው ቢነግድ አያተርፍም ለድሪ ያሉት አንገት ለአሸንክታብ ለድሪ ያሉት አንገት ላሽክት ለድካም የጣፈኝ ብነግድ አይተርፈኝ ለዶሮ ሲነገሩ ምጥማጥ ይሰማል ለጆሮ ጥርስ ለሆዳም ስስ ለገላጋይ ደም የለውም ለገበሬ መልካም በሬ ለገቢህ ተንገብገብ ለገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ ለገደለ ጎፈሬ ላረጋገጠ ወሬ ለገዳም የረዳ አይጎዳ ለጉንዳን ደም የለው ለዝንብ ቤት የለው ለጉንዳን ደም የለው ለገንዘብ ቤት የለው ለጋስ ቢለግስ አበደረ እንጂ አልሰጠም ለጋስ ቢለግስ አበደረ እንጂ እንዲያው አልሰጠም ለእግዜር የተቀናቀነ ጽድቅ ለንጉስ የተቀናቀነ ወርቅ ለጎበዝ ስጠው ሰንጋ ፈረስ ለጠላትህ እንደ ዳቦ እስኪገምጥህ አትመቸው ለጠቢብ አንድ ቃል ይበቃል ለጠጪ ሰው የመጠጥ ወሬ አውራው ለጥልና ለዳኛ ያለው ገንዘብ አፋፍ ይቆያል ለጥርጣሬ ምንጣሬ ለጥቅም ሲታጠቁ ከጎን ይጠንቀቁ ለጥቅምት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ለውጠኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ ለጨለማ ጊዜ መብራት ለመከራ ጊዜ ብልሀት ለጨቅጫቃ ሰው ከማበደር ይሻላል በጄ ማደር ለጭሰኛ መሬት ለሳር ቤት ክብሪት ለጾም ግድፈት ለበአል ሽረት ለጾም ግድፈት ለባል ሽረት ለፈረስህ አንገት ለጋሻህ እንብርት ለፈሪና ለንፉግ እያደር ይቆጨዋል ለፈሪ ሜዳ አይነሱም ለፈሪ ምድር አይበቃውም ለፈሪ ይበቃል ፍርፋሪ ለፈሪ ስጠው ፍርፋሪ ለፋሲካ የተዳረች ሁል ጊዜ የፋሲካ ይመስላታል ለፍቅር ብተኛት ለጠብ አረገዘች ለፍቅር የለውም ድውር ለፍየል ቆላ ለሙክት ባቄላ ለፍየል ህመም በሬ ማረድ ለፍየል ስም አውጣ ቢለው ሞት አይደርስ አለው ሊበሉዋት ያሰብዋትን አሞራ ይሏታል ጂግራ ሊወጋ የመጣ ጌታዬ ቢሉት አይመለስም ሊያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ ሊያስቡት አይገድም ሊጣላ የመጣ ሰብብ አያጣም ላህያ ፈስ አፍንጫ አይዙለትም ላህያ ማር አይጥማት ላህያ ያልከበደው ለመጫኛ ከበደው ላለው ቅንጭብ ያረግዳል ላለው ይጨመርለታል ላለፈ አይጸጸቱም ለሚመጣው አይበለጡም ላለፈው አይጸጸቱም ለሚመጣው አይበለጡም ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራለትም ላለፈው ክረምት ውሀ ማቆር አይቻልም ላለፈው ጸሎት ከንቱ ጩኸት ላሊበላ ሄደሽ ከህንጻው ብትሰፍሪ አይገኝም ጽድቅ አለ ባህሪ ላሊበላ አደራውን አይበላ ላሊበላ የቃሉን አይበላ ላሊበላን ካላጠገቡት ይጮሀል ሎሌም ካልሰጡት ይከዳል ላላየ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው ላላየው የሚያስገርም ለሰማው የሚያስደንቅ ላላዩ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው ላላወቀው ፎገራ ዱር ነው ላመት ልብስ ለእለት ጉርስ ላሜ ቦራ የልጆቼን ነገር አደራ ላም ሲበዘበዝ ጭራዋን ያዝ ላም ቀንዷ አይከብዳትም ላም በረቱን የሰው ልጅ አባቱን አይረሳም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ላም አለኝ በሰማይ ወተትዋንም አላይ ላም አለኝ በሰማይ ገመድ እፈልጋለሁ ላም እሳት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወውም ልጅ ሆነባት ላም ከወንዝ ልጅ ከቦዝ ላንተ መምከር ጥቁር ድንጋይ ላይ ውሀ ማፍሰስ ነው ላንቺ ቁምነገርሽ በሶብላ ወጥሽ ላንቺ ብርቅሽ በሶቢላ ወጥሽ ላያዘልቅ ጸሎት ለቅስፈት ላይቀርልኝ እዳ በጊዜ ልሰናዳ ሌባ ላመሉ ቅድመ እውቅና አገኘ ሌባ ላመሉ ንግድ ይላል ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል ሌባ እናት ልጇን አታምንም ሌባን ሌባ ቢሰርቀው እንዴት ይደንቀው ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት ልብስህን በውሀ ገንዘብህን በድሀ ልብ ካላየ አይን አያይም ልብ ካላየ አይን አይፈርድም ልትደርቅ የደረሰች ምንጭ ጭልጭል ትላለች ልትሰራ ሂዳ ተላጭታ መጣች ልጅም ከሆነ ይገፋል ድንችም ከሆነ ይጠፋል ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች ልጅ ምን ቢሮጥ አባቱን አይቀድምም ልጅ ሳለህ አጊጥ ሞል ሳይዘጋ ሸምት ልጅ ቢያኮርፍ ቁርሱ እራት ይሆናል ልጅና እሳት ባለቤቱ ያጠፋዋል ልጅን አሳዳጊ እሳትን ውሀ ያጠፋዋል ልጅና ወረቀት የያዘውን አይለቅም ልጅና ጦጣ ውሀ ይጠጣ ልጅ ያቦካው ለእራት አይሆንም ልጅ ይወለዳል ከቦዝ ላም ይገዛል ከወንዝ ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ ልግመኛ ባሪያ መጇን ትደብቃለች ልግመኛ አጋዥ ብታገኝ መጅ ደበቀች ልግመኛን መምከር ውሀ በወንፊት ማኖር ልፋት ቢያምርህ መሬት ግዛ ችግር ቢያምርህ ልጅ አብዛ ልፋ ያለው ሊስትሮ እግር ስር ይውላል ልፋ ያለው ምረጡኝ አለ ልፋ ያለው በህልሙ ሲሸከም ያድራል ልፋ ያለው አንድ እንጨት ያስራል ልፋ ያለው በሬ ቆዳው ለከበሮ ልፋ ያለው ቢን ላደንን ይፈልጋል ልፋ ያለው አንድ እንጨት ያስራል ሎሌ ለስህተት ጌታ ለምህረት ሎሌ ሲከብር ጌታውን ይከሳል ሙክት ሲሰባ ሾተሉን ይልሳል ሎሌ ያገለገለውን ይቆጥራል ጌታ ያስቀየመውን ያስባል ሎሌና አሞሌ ካዘዙት ይውላል ሎሚ ካልመጠጡት እምቧይ ነው ሎሚ ካልመጠጡት እምቧይ ዳቦ ካልገመጡት ድንጋይ ሎሚና ትርንጎ ሞልቶልህ ባገር እንቧይ ታሸታለህ የድሀ ነገር ሎሚና ትርንጎ ሞልቶ ባገር እንቧይ ያሸታል አወይ የድሀ ነገር ሎሚ ቢያብብ ቢኖርና መልካም ሽታ ቢሰጥ መኮምጠጡን አይተውም


[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መሄድ በጋ ነው መቀመጥ ክረምት ነው መሄጃ የሌለው መውጫውን ያበስራል መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ መልከ ጥፏ ቆንጆዋን አስናቀች መልካም ባል መጥፎ ሴት ይገራል መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል መልካም አባት ለልጆቹ እጁን ኪሱ ይከታል መልካም ባል መጥፎ ሴት ይገራል መልኳ ባያምር አመሏ ይመር መልክ ታጥቦ አይጠጣ ወይ አይበላ መልክ ስጠኝ እንጂ ሙያ ከጎረቤቴ እማራለሁ መመራመር ያገባል ከባህር መሞት የፈለገ ግልገል ቀበሮ ቤት ሄዶ ይጨፍራል መራጭ ይወድቃል ከምራጭ መቀመጥ በአልጋ ታላቅ ደጋ መቅረቧን ሳታውቅ እጇን ታጠበች መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች መተው ነገሬን ከተተው መቼ መጣሽ ሙሽራ መቸ ቆረጠምሽ ሽንብራ መካር የሌለው ንጉስ አለ አንድ አመት አይነግስ መንገድ ካገር ልጅ ምክር ከጨዋ ልጅ መወለድ ቋንቋ ነው ሚስቱ ክፉ ባቄላ እራቱ ብሳና እንጨቱ ሀዘን ነው እቤቱ ሚስቱ ደግ ስንዴ እራቱ ወይራ እንጨቱ ደስታ ነው እቤቱ ሚስቱን ጠልቶ ካማቱ ልጁን ከሶ ካባቱ ሚስቱን ገድሎ አማቱ ቤት ተሽሽገ ሚስት ባታብል ባሏን ትወልዳለች ሚስት ከፈቷት ባዳ ማሽላ ከተቆረጠ አገዳ ሚስትህ አመዳም ጎራዴህ ጎመዳም ሚስትህ አረገዘች ወይ ቢለው ማንን ወንድ ብላ አለው ሚስትህን ስደድ በሬህን እረድ ይላል የባለጌ ዘመድ ሚስትና ዳዊት ከብብት ሚስት ፈትቶ ካማት መቀለብ በእንፉቅቅ መሄድ ሙቅ ውሀና የሰው ገንዘብ አይጠቅምም ሚስጥርህን ለባእድ ለምን አዋየኸው ወንፊት ወሀ ይዞ የት ሲደርስ አየኸው ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ ማር በበላሁበት በጣፈጠው አፌ ጎመን ጎረስኩበት አይ አለማረፌ ማሽላ ሲያር ይስቃል ማሽላ እየፈካ ያራል?? ማቅ ይሞቃል ጋቢ ይደምቃል ገቢውን ባለቤት ያውቃል??? ማን ሙሽራ ሊልሽ ትኳያለሽ ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ ማእድ ጠፋና አንድ ላይ በላን ማግባቱ ቀርቶብኝ በታጨሁ ማጣት ከሰማይ ይርቃል ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡ ውሀ ቢያንቅ በምን ይውጡ ምን ያመጣ ድሀ ምን ያገሳ ውሀ ምን ቢያርሱ እንደጎመን አይጎርሱ ምንም ቢጠም መንገድ ምንም ቢከፋ ዘመድ ምን ቢፋቀሩ አብረው አይቀበሩ ምከረው ምከረው እንቢ ካለ መከራ ይምከረው ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላል ሞት የሰጠው ቀባሪ አያሳጣውም ሞኝ ሲስቁበት የሳቁለት ይመስለዋል ሞኝ እከኩን እያየች ስትስቅበት ወደደችኝ ብሎ ይፈነድቃል ሞኝና ወረቀት ሊደራደሩ ነው ሞኝና ወረቅት የያዘውን አይለቅም ሞኝ ውሀ ሲወስደው ይስቃል ሞኝ ዘመድ ከልጅህ እኩል አድርገኝ ይላል

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሬሳ በምኑ ይከበራል በዝምታው ራስ ሳይጠና ጉተና ራስ ተላጭቶ ወለባ ልባልባ ታጥቆ አዛባ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሰለሞን ሳባን ውሀ ባያስጠማት ኖሮ የሱ ጥም ባልበረደ ነበር ሰውን ፈላጊ በምርጫ ይሽነፋል ሰማይ አትረስ ንጉስ አትክሰስ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ሰባት አመት ባይማሩ ሰባ አመት ይደንቁሩ ሰነፍ ሴት ያገባ በሬው በሰኔ ገደል የገባ ሰነፍ በዓል ያበዛል ሰነፍ ቢመክሩት ውሀ ቢወቅጡት ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል ሰነፍ ገበሬ ክረምት በጋው በጋው ክረምቱ ሰኔ መቃጠሪያ ህዳር መገናኛ ሰኔ ሰላሳ የለውም ካሳ ሰኔና ሰኞ ሰኔን በዘራዘር ሃምሌን በጎመን ዘር ሰካራም ቤት አይሰራም ሰካራም ዋስ አያጣም ሰው መሳይ በሸንጎ ሰው በዋለበት ውሀ በወረደበት ሰው ቢማር ቄስ እንጂ መላክ አይሆንም ሰው ባለው ይሰለፋል ሰውን ማመን ቀብድ ተቀብሎ ነው ሰውን ሰው ናቀው የራሱን ሳያውቀው ሰውን ሰው ያሰኘው እቁብ ነው ሰውን ሲወዱ ከነንፍጡ እና ልጋጉ ሰውን ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ ሰው አለብልሀቱ ገደል መግባቱ አለጉልበቱ ውሀ መግባቱ ሰው አለወንዙ ብዙ ነው መዘዙ ሰው እንደ እውቀቱ ነው ሰው ከሞተ የለ ንስሀ ከፈሰሰ አይታፈስ ውሀ ሰውየው ውሀ ሲወስደው እኔም ወደ ቆላ እወርዳለሁ ብዬ ነበር አለ ሰው ያመነ ውሀ የዘገነ ሰው ያስገድላል አባይ ውሀ ያስጮሀል ድንጋይ ሰው ያለስራው የተሰረቀ አህያ ይነዳል ሰው ጥራ ቢሉት መራራን ጠራት ሰው ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ ሰዶ ማሳደድ ቢሻህ ዶሮህን ለቆቅ ለውጥ ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ ሲሉ ስምታ ዶሮ ሞተች ዋና ገብታ ሲመክሩት ያልሰማ ሲያጮሉት ይሰማ ሲመች ያማት ተዝካር ይወጣል ሳይመች ያባት ይቀራል ሲሞቱ ብታይ አንቀላፋች ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል ሲሮጡ የፈቱት ሲቀመጡ ለማስተካከል ቀላል ነው ሲሮጥ የመጣን አህያ አጥብቀህ ጫነው ሲሰርቀኝ ያየሁትን ቢጨምርልኝ አላምነውም ሲስሟት ትታ ሲስቧት ሲስሟት እንቢ ብላ ሲጎትቷት ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል ሲበሉ አድርሰኝ ሲጣሉ አርቀኝ ሲበሉ አድርሱኝ ሲጣሉ መልሱኝ ሲቃ የቀስቀስው ነቅቶ አይተኛም ሲታጠቡ እስከ ክንድ ሲታረቁ ከሆድ ሲቸኩሉ የታጠቁት ለወሲብ አይመችም ሲቸግር ጤፍ ብድር ሲያውቀኝ ናቀኝ ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል ሲያደርጉ አይታ ዶሮም ጡት መያዣ ገዛች ሲጠሩት ወዴት ሲልኩት አቤት ሲጠባ ያደገ ጥጃ ቢይዙት ያጓራል ሲገደገድ ያልበጀው ሲወቀር እሳት ፈጀው ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት ሳትወልድ ብላ ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ ሲስል ያድራል ሳያውቁ የቆረጡት አበባ የፈለጉት ቀን ይደርቃል ሳያጣሩ ወሬ ሳይገሉ ጎፈሬ ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በቅርቡ ሳይሰሙ ወሬ ሳይገሉ ጎፈሬ ሳይቃጠል በቅጠል ሳይተርፋት አበድራ ሳትቀበል ሞተች ሳይቸግር ጤፍ ብድር ሳይቸግር ጤፍ ብድር መከበር በከንፈር ሳይቸግር ጤፍ ብድር በስተርጅና ሙሽርና ሳይከካ ተቦካ ሳይደግስ አይጣላም ሳይጠሩት አቤት የሰይጣን ጎረቤት ሳይጠሩት ወይ ባይ ሳይሰጡት ተቀባይ ሴቱ ሲበዛ ጎመን ጠነዛ ሴትና ዶሮ ዱር ከሄዱ ቤታቸውን ይክዳሉ ሴት ከወንድ እህል ከሆድ ሴት ለቤት ወፍጮ ለዱቄት ሴትና መሬት የማይችሉት የለም ሴት ማገዶ ሲቸግራት ምሰሶ ትነቅላለች ሴት ሲበዛ ልማት ይፋጠናል ሴት ሲበዛ ወንዶች ይፈራሉ ሴት በማጀት ወንድ በችሎት ሴት በጳጳስ ኳደሬ በንጉስ ሴት ብታውቅ በወንድ ያልቅ ሴት ሲያፏጩላት ያረሱላት ይመስላታል ሴት ታውቅ በወንድ ያልቅ ሴት አማት የመረዘው ኮሶ ያነዘዘው ሴት አግብተው ሴት ቢወልዱ የት አለ ንግዱ ሴት ከወንድ እህል ከሆድ ሴት ከጠላች በቅሎ ከበላች አመል አወጣች ሴት ካላበለች ባልዋን ትወልዳለች ሴት ካልወለደች ቋንጣ አትጠብስም ሴት ካልዋሸች ባልዋን ትወዳለች ሴትና መሬት የማይችሉት የለም ሴት የወደደ ጉም የዘገነ ሴት ያመጣው ጠብ አይበርድም ሴት ይወዷል ማጀት ያንጎዳጉዷል ሴትና ቄስ ቀስ ሴትና በቅሎ እንደገሪዋ ነው ሴትና አህያ በዱላ ሴትና አህያ ዱላ ይወዳል ሴትና ድመት ወደ ሞቀበት ሴትና ዶሮ ሳይጣላ አይውልም ሴትና ድስት ወደ ማጀት ሴትና ዶሮ ሳያብድ አይውልም ሴትና ፈረስ እንደኩሬ ውሀ እያደር ማነስ ሴትና ፈረስ የስጡትን ይቀምስ ሴትን ያመነ ጉም የዘገነ ሴት የላከው ምልክቱን አይረሳም ሴት የላከው ሞት አስፈራራው ሴት የላከው ሞት አይፈራም ሴት የላከው በር አያንኳኳም ሴት የላከው አልቃይዳን አይፈራም ሴት የላከው ጅብ አይፈራም ሴት የላከው ፓርላማ ይገባል ሴትየዋ እንደፈራሁት ተቀደደብኝ አለች ስለ ጨሰ አይነድም ስለዳመነ አይዘንብም ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎም ስልቻ ስምህ ማነው ላገር አይመች ማን አወጣልህ ጎረቤቶች ስምሽ ማነው ሲሏት ቂጤ ትልቅ ነው አለች ስምን መላክ ያወጣዋል ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል ስም ያለው ሞኝ ነው ስም ይወጣል ከቤት ይሄዳል ጎረቤት ስም ይወጣል ከቤት ይከተላል ጎረቤት ስራ ለሰሪው ምርጫ ለመራጭ ስራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው ስራ ከመፍታት ምርጫ መወዳደር ስራ ከምፈታ ልጄን ላፋታ ስራ ያጣ መለኩሴ አደገኛ ቦዘኔ ተባለ ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል ስራ ያጣ መነኩሴ “አደገኛ ቦዘኔ” ተብሎ ታሰረ ስራ ያጣ መነኩሴ የምርጫ ቅስቀሳ ጀመረ ስራ ያጣ ቄስ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል ስብ ሊያርዱ ጉፋያ ይነዱ ስትወልድ የምትበላውን በርግዝናዋ ጨረስችው ስትግደረደሪ ጾምሽን እንዳታድሪ ስደትና አግዳሚ ሁሉንም እኩል ያረጋል ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ ስጋው ያሳማ እንኳን ለበላው ለሰማው ገማ ስጋው ያሳማ ከበላው የሰማው ገማ ሶስቴ ከመፍሳት አንዴ መቅዘን

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሸማ ለብሶ ስልቻ በቅሎ ጭኖ ለብቻ ሸማ ማዋስ ለባላገር በቅሎ ማዋስ ለወታደር ሸማ በውሀ ሰው በንስሀ ሸማን በውሀ ሰውነትን በንስሀ ሸማ በየፈርጁ ይለበሳል ሸማና ምስጥ ወደ ውስጥ ሸማኔ በመኑ ጠይብ በከሰሉ ሸማኔ በድሩ ጠይብ በመንደሩ ሸማኔ ድውሩን ባለስልጣን ክብሩን ሸማን ጠምዞ ያሰጧል እህልን አላምጦ ይበሏል ሸምበቆ በመርዘሙ አይሆንም ምሰሶ ሸምበቆ በመርዘሙ ምሰሶ አይሆንም ሸርሙጣ ስታረጅ አቃጣሪ ትሆናለች ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ አበደ ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ ያበደ ሸኚና ጥላ ቤት አይገባም ሸኚ ቤት አያደርስም ሸኝ ቤት አይገባም ሸክላ ቢጥሉት ገለባ ሹመት ላወቀው ይከብደዋል ላላወቀው ያሳብደዋል ሹመት ሲገኝ ዘመድ አይገድም ሹመት ሺህ ሞት ሹመት በተርታ ስጋ በገበታ ሹመት የለመደ ወንዝ ዳር ይወርዳል ሹመትና ቁመት ከልኩ አያልፍም ሹመትና ቁመት አይገኝም በምኞት ሹም ለመነ አዘዘ ሹም ለሹም ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል ሹም ለሹም ይጎራረሳል ድሀ ለድሀ ይለቃቀሳል ሹም መክሰስ ወጀድ ማረስ አይቸግርም ሹም ሲቆጣ ማር ይዞ እደጁ ደስ ሲለው ማር ይዞ እደጁ ሹም ቢሞት ሀምሳ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ሀምሳ ሹም ቢሞት ቀባሪው ሀምሳ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ሀምሳ ሹም ያዛል ቄስ ይናዝዛል ሹምና ማር እያደር ይከብዳል ሹምና የጋማ ከብት በጊዜ ይከተት ሹምና ጥጥ እያደር ይከብዳል ሹምና ጥጥ እያደር ይከዳል ሹሩባ ትሰራ ሄዳ ጠጉሩዋን ተላጭታ መጣች ሹክሹክታ የጠብ ወለምታ ሺ መት ሺ ሞት ሺም ታለበ አንድ ያው በገሌ ሺ በመከረ አንድ በወረወረ ሺ በመከር አንድ በወረወር ሺ አውል ሲሞት ሺህ ይሙት ሺ አውል ከሚሞት ሺ ይሙት ሺ አውል ኪሞት ሺ ይሙት ሺ ይሙቱ ሺ አውል አይሙት ሺ ዝንብ መሶብ አይከፍትም ሺህ ቢታለብ አንድ በገሌ አለች ድመት ሺ ቢታለቡ ከገሌ አላልፍም አለች ድመት ሺ ቢያጩሽ አንድ ያገባሽ ሺ ያጭሽ አንድ ያገባሽ ሻማ ራሱ ነዶ ራሱ ብርሀን ይሰጣል ሻሽ ይደምቃል ማቅ ይሞቃል የሚበጀውን ባለቤቱ ያውቃል ሻጭ ገዥ ሆኖ ይገምታል ሽልም እንደሆን ይገፋል ቂጥም እንደሆን ይጠፋል ሽል ከሆነ ይገፋል ቂጣም ከሆነ ይጠፋል ሽል እንደሆን ይገፋል ቂጣም እንደሆን ይጠፋል ሽመልና ዘንግ ቂልና በግ ሽማግሌ ሳለ ምክር አይጠፋም ጎልማሳ ሳለ ላም አይነዳም ሽማግሌ በምክሩ አርበኛ በሰናድሩ ሽማግሌ ካለበት ነገር አይናቅበት ሽማግሌ ካለበት ነገር አይሰረቅ ጎበዝ ካለበት በትር አይነጠቅ ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልመረተ ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልሸተ ሽማግሌ ይገላግላል የተጠቃ አቤት ይላል ሽማግሌና ስልቻ ሳይሞሉ አይቆሙም ሽማግሌና ጅብ በላላባት ይገባል ሽማግሌን ከምክር ከመለየት ከምግብ መለየት ሽሮን ሲሸውዷት ፕሮቲን ነሽ አሏት ሽሽት ከኡኡታ በፊት ሽበት ምን ታረግ መጣህ ቢሉት እኖር ብዬ አለ ሽበት እኖር ብዬ መጥቻለሁ አለ ሽታና ግማት ላልሰማ ማውራት ሽንብራ መኖር በመከራ ሽንኩርት አንድም በሉት ገማ ደገሙትም ገማ ሽንኩርት የባህሪውን ይሸታል ሾላ በድፍን ሾተልን ወደ ሰገባህ ቁጣህን ወደ ትእግስት ሾተልን ወደ አራዊት ቁጣህን ወደ ትእግስት ሾተልን ወደ አፎት ቁጣን ወደ ትእግስት ሽሮ ቢደነፋ እንጀራ እስኪቀርብ ነው

    ==ቀ==

ቀለም ሲበጠበጥ ብርእ ሲቀረጥ ቀለም በቀንድ ውስጥ ጨለማ ነው ሲፃፍ ግን ብርሃን ነው ቀለም ሲበጠበጥ ብርእ ቅረጹልኝ ቀለበት ለቆማጣ ሚዶ ለመላጣ ቀሊል አማት ሲሶ በትር አላት ቀላጅ የሰይጣን ወዳጅ ቀላዋጭ ወጥ ያውቃል ቀልብ የሌለው ውሻ ጠዲቅ አምጡልኝ ይላል ቀልድና ቅዘን ቤት ያጠፋል ቀልደኛ አልቅሶ ካልተናገረ የሚያምነው የለም ቀልደኛ ገበሬ ሲያስቀን አደረ ቀልደኛ ገበሬ ናይት ክለብ ከፈተ ቀልደኛ ጎረምሳ እያራ ያፏጫል ቀልድና ቅዘን ቤት ያበላሻል ቀሙን ላይቀር ከነጫማቸው ቀማኛና ሽፍታ ጭለማና ማታ ቀርቀሬ ወርጄ ማር ስልስ ማር ልከፍል ቀስ በመቀስ አንቁላል በአግሩይሂዳል ቀስ እንዳይደፈረስ ቀስ እንዳይፈስ ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል ቀስ በቀስ አባይም ዝናብ ይሆናል ቀበሮ ናት የገጠሩዋ ሚዳቋ ናት የሰፈሩዋ ቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለች ቀበቶ ለማፈኛ ሰንሰለት ለማቆራኛ ቀበኛ ማሰሪያውን በልቶ ያሳጥራል ቀበኛ ከብት ዋጋውን ያደርስ ቀባሪ በፈጣሪ ቀብረው ሲመለሱ እግዜር ይማርዎ ቀብሮ የሚመለስ የሚመለስ አይመስለውም ቀኑ የጨለመበት መንገዱ ዘንግ ነው ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ ቀና ቢታጣ ይመለመላል ጎባጣ ቀናውን ብነግራት ውልግድግዱን አለች ቀን ስው መስሎ ማታ ጅራት አብቅሎ ቀን ሲከፋ በግ ይነክሳል ቀን ሲጥለው ሁሉ ይጠላው ቀን ሲገለበጥ ውሀ ወደ ላይ ይፈሳል ቀን ሲደርስ አምባ ይፈርስ ቀን ሳይቆጥሩ ውሻ ሳይጠሩ ደረሰ በእግሩ ቀንበር ታርቆ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል ቀንበር ታንቆ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል ቀን በበቅሎ ማታ በቆሎ ቀን በቅሎ ማታ ቆሎ ቀን ቢረዝም ልብ ያደክም ቀን ቢረዝም ልብ ይደክም ቀን ቢቆጥሩ ውሻ ቢጠሩ ደረሰ በእግሩ ቀን ቢቆጥሩ ውሻ ቢጠሩ ይደርሳል በእግሩ ቀን ባጀብ ሌት በዘብ ቀን አይጥለው የቀለም ሰረገላ አያሰናክለው ቀን አይጥለው ጠጅ አያስክረው ቀን አይጥለው ጠጅ አያሰክረው የለም ቀን እስኪወጣ ያባቴ ገበሬ ያግባኝ ቀን እስኪያልፍልሽ ያባትሽ ሎሌ ያግባሽ ቀን እስኪያልፍ ያለፋል ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ያግባኝ ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ይግዛኝ ቀን እንደተራዳ ሌት እንደ ግርግዳ ቀን ከህዝብ ሌት ከጅብ ቀን ከጣለው ሁሉ ይጥለው ቀን ካልለቀሙ ሌት አይቅሙ ቀን ካለቀሙ ሌት አይቅሙ ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ቀን የጎደለበት ጠገራ አይጥ ይበላዋል ቀን ይነዳ እንደ ፍሪዳ ቀንና ጨርቅ እንደምንም ያልቅ ቀንና ጨርቅ ያልቃል ብልህ ያውቃል ቀንዳምን በሬ ቀንድ ቀንዱን ቀንዱ ሰማይ ጠቀስ ጭራው ምድር አበስ ቀንድ ካላት ላም ጎዳ ትከፋለች ቀንድና ጅራት ለዋንጫ አለፉ ቀንድ እገባበት ጅራት አይቀርም ቀንድ ውስጥ ገብቶ ጅራት አይቀርም ቀኝም ሰገሩ ግራም ሰገሩ መገናኛው ኮሩ ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ ቀድሞ ነበር እንጂ ተራምዶ ማለፍ አሁን ምን ይሆናል ተይዞ መለፍለፍ ቀይ ምላሱ ጥቁር እራሱ ቀይ ሰው መልክ አይፈጅም ቀይ እንደበርበሬ ጥሩ እንደ ብርሌ ቀዳዳ ያፈሳል ግቢ ያፈርሳል ቀድሞ ሰኞን አለመሆን ነው ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የሚናገረውን ሰው ይጠላዋል ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የተናገረውን ሰው ይጠላዋል ቀዶ ያለበሰ ቆርሶ ያጎረሰ ቀጥኜ ቢያየኝ ጅማት ለመነኝ ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ ቀጥኜ ቢያዩኝ ሞዴል ነሽ አሉኝ ቁልቢጥ የላት ቁና አማራት ቁልቢጥ የላት ድርጎ አማራት ቁመህ ተከራከር ዙረህ ተመካከር ቁመህ ተናገር ዙረህ ተመካከር ቁመቷ ቢያጥር እንደ ድምብላል ውዷ ክፉ ነው ይደበልላል ቁም እንደአላማ ቁረጥ እንደጫማ ቁም እንዳላማ ጥልቅ እንደጫማ ቁም ነገረኛ መምሰል የተለመደ አመል ቁም ነገር ይዞ ተረት ቂም ይዞ ጸሎት ቁራ ሲነጣ አህያ ቀንድ ያወጣ ቁራ ስሙን የጠራ ቁርበት ምን ያንቋቋሀል ቢሉት ባያድለኝ ነው እንጂ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ ቁርበት ምን ያንጓጓሀል ቢሉት ባያድለኝ ነው እንጂ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ ቁርጥማት ቢያብር አልጋ ላይ ያማቅቃል ቁርጥ ያጠግባል ተስፋ ያታልላል ቁቅም ከፈስ ተቆጠረች ቁና ለመስፈሪያ ብርብራ ለማስከሪያ ቁንጥጫ ይሻላል ከግልምጫ ቁንጫ ለትልቅ ሰው ይበረታል ይባላል ቁንጫ መሄድ ሳትማር መዝለል ትማራለች ቁንጫ ሞኝ ናት ቀን ትበራለች ተለቃቅማ ታልቃለች ቁንጫ ውሀ ወረጅ ቢሏት ስፈናጠር የሰው ዶጮ እሰብር አለች ቁጥቋጦም ሲያድግ ዛፍ ይሆናል ቁጥቋጦ ሲያድግ ዛፍ ይሆናል ቁጥቋጦ ያለዛፍ አይሆንም ቁጩና ብስጩ አልማችሁ ፍጩ ቁጭትና መረቅ ለጊዜው ይጣፍጣል ቁጭትና መጠጥ ለጊዜው ይጣፍጥ ቁፍ ቁፍ አሰኘሽ እንደቄብ ዶሮ ለመከራ ላሳርሽ ኖሮ ቂል ሲረግሙት የመረቁት ይመስለዋል ቂል አይሙት እንዲያጫውት ቂልን ለብቻው ስደበው ራሱን ባደባባይ እንዲሰደብ ቂልን አንድ ጊዜ ስደበው ሲሰደብ ይኖራል ቂልን ድንጋይ ተማትቶ ጌታና ሎሌ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ ቂል ከጠገበበት አይወጣም ቂል ያገኘው ፈሊጥ ውሻ የደፋው ሊጥ ቂምህን አትርሳ የወደቀን አንሳ ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት ጭድ አዝሎ ወዘት ቂጡን የተወጋ ውሻ እንደልቡ አይጮህም ቂጡ የቆሰለ ውሻ እንደልቡ አይጮህም ቂጥ ቢወድል ፈስ አያድን ቂጥ ቢያብጥ ልብ አይሆንም ቂጥኛም ከውርዴ ይማከራል ቂጥኛም ከውርዴ ይውላል ቂጥ ገልቦ ክንብንብ ቂም ቂም ያሰኘሽ እንደዶሮ ለካስ ለመከራሽ ላሳርሽ ኖሮ ቂፍ ቂፍ ያሰኘሽ እንደ ቄብ ዶሮ ለመከራሽ ላሳርሽ ኖሮ ቃልህ ሳይዘጋ እግርህ ሳይዘረጋ ቄሱም ዝም መጽሀፉም ዝም ቄስ ለኑዛዜ ፍቅር ለሚዜ ቄስ ምን ይሻል ጠላ ነገር ምን ይሻል ችላ ቄስ ኤርክሶን መምህሩ እናት አያስቀብሩ ቄስ እበር አረመኔ ከማህበር ቄስ ካናዘዘው እድሜ ያናዘዘው ቄስ ካፈረሰ ዲያቆን ከረከሰ ቄስና ንብ እያዩ እሳት ይገባሉ ቄስና ንብ እያየ እሳት ይገባል ቄስ ያዘዘህን አድርግ እንጂ ቄስ ያደረገውን አታድርግ ቅል ባገሩ ድንጋይ ይሰብራል ቅል ባገሩ ደንጊያን ይሰብራል ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ሎሌና ጌታ ተሟግቶ ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ሎሌና ጌታ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ጌታና ሎሌ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ ቅልውጥ አሳስቦ ይጥላል ዘመቻ ቅምሙ የበዛበት ወጥ አይፋጅ አይኮመጥጥ ቅማል እንኳን ካቅሟ ጥብጣብ ታስፈታለች ቅማል ውሀ ውረጅ ቢሏት ስንዳሰስ ለመቼ ልደርስ ቁንጫ ውሀ ውረጅ ቢሏት ስፈናጠር የሰው ዶጮ እሰብር አሉ ቅማል በጥፍር ቢድጧት ራስ ደህና አለች ቅማል ከአካላት ምስጢር ከቤት ቋንጣና ባለሟል ሳያር አይቀርም ቅዝምዝም ወዲያ ፍየል ወዲህ ቅርብ ያለ ጠበል ልጥ ይነከርበታል ቅርናታም ለቅርናታም ሰንቡሌ ሰንቡሌ ይባባላል ቅርንጫፉ እንደዛፉ ቅቤ መዛኝ ድርቅ ያወራል ቅቤ ሲለግም ወስፌ አይበሳውም ቅቤ ተነጥሮ ለመብላት ያባት የናት ቅቤና ቅልጥም ወዴት ግጥምጥም ቅቤ ይፍሰስ ከገንፎ አይተርፍ ቅቤ ይፍሰስ ከገንፎ አይለፍ ቅብጥና ቅልጥ አንድ ላይ ሲሄዱ ቅልጥ ብላ ቀረች ሶራስ ክመንገዱ ቅል በአገሩ ድንጋይ ይሰብራል ቅናት ያደርሳል ከሞት ቅናት ጥናት አያገናኝ ካባት ከናት ቅናት ጥናት አይገኝም ከናት ካባት ቅና ያለው በአባቱ ከረባት ይቀናል ቅና ያለው በናቱ ብልት ይቀናል ቅን በቅን ከማገልገል ፊት ለፊት ማውደልደል ቅንቡርስ የት ትሄዳለህ መተማ ትደርሳለህ ልብማ ቅንነት ለነፍስ መድሀኒት ቅንድብ ለአይን ጥቅሻ አስተማረች ቅዝምዝም ሲወረወር ጎንበስ ብለህ አሳልፈው ቅዠት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም ቆላና ደጋ እመቤትና አልጋ ቆሎ ለዘር እንዶድ ለድግር አይሆንም ቆሎን ቢቆረጥሙት እንጂ ቢያሹት አያልቅም ቆመው የሰቀሉትን ቁጭ ብለው ለማውረድ ይቸግራል ቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ናት ቆማጣ ብለው ያው ቁምጥና ነው ሌላ ምን ይመጣል አለ ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል ቆሩ መቀበሪያው ያው ፈሩ ቆሩ በማን ምድር ትለፋ ቆርሶ ያላጎረሱትን ቀዶ ያላለበሱትን ብላቴና ማዘዝ አይገባም ቆቅ ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ቆንጆና እሸት አይታለፍም ቆዳ ማንጓጓቱን ስሱ መጓጓቱን ቆዳ ማንጓጓቱን ስሱ መጓጓቱን አይተውም ቆዳ ሲወደድ በሬህን እረድ ቆጥሮ የማይሰጥ ሌባ ቆጥሮ የማይቀበል ሌባ </poem>