ወህኒ
Appearance
(ከአምባ ወህኒ የተዛወረ)
ወህኒ | |
አምባ ወህኒ (ከሩቁ) በ1851 ዓ.ም. | |
የወህኒ ተራራ በስሜን ጎንደር የሚገኝ ሲሆን በአጼፋሲለደስ ዘመን ለመጀምሪያ ጊዜ ለተገዳዳሪ የነገስታት ወንድ ዘሮች እንደ እስር ቤት አገልግሏል። ይህም እርስ በርስ ጦርነትን ከወደፊቱ ለማስቆም ነበር።
ፋሲል ልጁ ዳዊት ሲያምጽ ለመጀመሪያ ጊዜ በእስር ወደዚህ ተራራ ልኮታል። የዚህ ስርዓት ምንጭ ቀደምቱ የደብረ ዳሞ እና ግሸን አምባ ዘይቤ ነበር። አጼ ፋሲል ይህን ተራራ ለእስር ቤት ከተጠቀሙበት ጀመሮ እስከ ዘመነ መሳፍንት (በተለይ 1790) ድረስ አምባው በዚህ መልኩ አገልግሏል። በአሁኑ ዘመን የተለያዩ ሰወች ተራራውን ለመውጣት ሞክረው ከአንድ ሰው በስተቀር አልቻሉም ፤ በድሮው ዘመን ግን ቤ/ክርስቲያን እና ቤተ መንግስት በተራራው ላይ ተሰርቶ ነበር። ፍርስራሾቹም አሁን ድረስ በምኩራቡ ይገኛሉ።
-
አምባ ወህኒ ላይ ተሰርቶ የነበረው ቤ/ክርስቲያን ፍርስራሽ በ1950ወቹ በሄሊኮፕተር ፎቶ እንደተነሳ
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |