Jump to content

አምክንዩ ምክነት

ከውክፔዲያ

አምክንዮ ማለት አንድን እውነት ከሌላ እውነት ጋር የሚያያይዝ መሳሪያ ማለት ነው ። ይህ የሚያሳየው የአምክንዮ ተፈጥሮ እውነትን ማግኘት ሳይሆን፣ እውነትን ማስተሳሰር ነው። በዚህ ትስስር ላይ ግን ፣ ብዙ ስህተቶች ይፈጠራሉ ( የማይያዙ እዉነታወችን ማያያዝ ፣ ያልተያያዙ እውነታወችን የተያያዙ ማስመሰል ፣ ወዘተ .. )። እነዚህን ስህተቶች የፍልስፍናና ሒሳብ ተማሪወች የአምክንዮ -ምክነት logical fallacy በማለት ሰብስበዋቸዋል ።

1. adhominem እሱኮ ፦

ምሳሌ ፦

አበበ ፦ መንገዶች እየተጣበቡ ስለሆነ ሌሎች መንግዶች መሰራት አለባቸው ።
መሰረት ፦ አንተኮ ታክስ እንኳ አልከፈልክም ፣ ስለመንገድ እና ስለ መንግስት ስራ አታውቅም።

እዚህ ላይ ፣ መሰረት የሰራችው ስራ adhominem/እሱኮ ይባላል ምክንያቱም አበበ ያነሳውን ጥሩ ነጥብ ከመወያየት ይልቅ ከነጥቡ ጋር ጭራሽ ግንኙነት የሌለ ነገር አንስታ ውይይቱን ዘጋች ።

2. appeal to force/ ዋ !

ምሳሌ ፦

አበበ ፦ መቸ ነው የሀገራችን ህዝብ ከርሀብ የሚዎጣው ?
ማሞ ፦ አሜሪካ ገብተህ ዝም ብለህ ትዘባርቃለህ ።

ማሞ እንግዲህ ለማለት የፈለገው አሜሪካ ባትገባ ኑሮ ይህን ነጥብ አታነሳም ነበር ። የማያነሳበት ምክንያት ፣ ምግብ ስለተትረፈረፍ ሳይሆን ፣ ይህን ነጥብ ቢያነሳ ሚደርስበት ነገር ስላለ ነው ። ይህ ዋ ! የሚባለው ምክነት ነው ።

3.red herring/ሸወዳ

አበበ ፦ ትላንትና ባክሽ የትራፊክ ትኬት አገኘሁ
መሰረት ፦ እንዳትከፍል ! ስንት ሰው ገዳይ ወንጀለኛ እያለ አንት እምትቀጣበት ምንም ምክንያት የለም ።

ይህ እንግዲህ ያልተገናኝቶ-ገብያ ዋና መሰረት ነው። አንድ ሰው የሚናገረው ነጥብ ደስ ሳይለን ሲቀር ፣ ሌላ የማይገኛኝ ነገር አንስተን በመሸወድ ሀሳቡን እንዳይጨርስ ስናደርግ ሽወዳ red herring ይባላል ።

ሌላ ምሳሌ ፦

እናት ለአስተማሪ ፦ ልጀ ፈተና ላይ ኮርጃለች ብለህ ታምን ይሆናል ፣ ነገር ግን ይችን ትንሽ ምስኪን ልጅ እንደገና ፈተና እንድትወስድ ስታደርግ ለህሊናህ አይከብደህም