Jump to content

አረንጓዴ ዛጎል አሳ

ከውክፔዲያ
አረንጓዴ ዛጎል አሣ

አረንጓዴ ዛጎል አሳ (ሮማይስጥPerna canaliculus) 2 ክፍት-ክድን ባለ ዛጎል ውስጥ ከሚኖሩት አሶች አንድ ዝርያ ነው። ዝርያው የሚገኘው በኒው ዚላንድ ጠረፍ አጠገብ ነው። ለኒው ዚላንድ ምጣኔ ሀብት እርግጥኛ ሚና አለው።

ይኸ የዛጎል አሣ ዝርያ በተለይ ለአንጓ ብግነት (ሪህቁርጥማት) የሚያስታግስ ልዩ መድኃኒት በውስጡ ይሠራል። በዚህ ምክንያት በኒው ዚላንድ የሚበሉት ማዖሪ ኗሪዎች ከአንጓ ብግነት እምባዛም አይቸገሩም፤ ከአሳው የወጣው መድኃኒት ደግሞ በሌላ አገር በሚኖሩት የቁርጥማትና የሪህ ህመምተኞች ይፈለጋል።