አሬን ስበላ ከረምሁ (1)(2)

ከውክፔዲያ

አሬን ስበላ ከረምሁ (1)

(10)አለቃ የሚኖሩበት አካባቢ ድርቅ ጠንቶ ሁሉም ስደት ገባ።አለቃም ሲጓዙ ውለው ጥሩ አካባቢ ይደርሱና የግዜር መንገደኛ ነኝ ብለው አንዷን ባልቴት ለምነው ሊያድሩ ይፈቀድላቸዋል። ሌሊት ላይ ከመደባቸው ይነሱና ባልቴቱዋ ምኝታ ጋ ሄደው አይነ ምድራቸውን ተወጥተው ምኝታቸው ተመልሰው ባልቴቱዋን መጣራት ይጀምራሉ። ሴትየዋም «ምነው? ምን ሆኑ?» ስትላቸው ቤቱ አይነምድር አይነምድር ይሸታል እና መተኛት አቃተኝ ይላሉ። ሴትየዋም ኩራዟን ትለኩስና ፍለጋ ይጀመራል። አለቃም ተነስተው ወደ ባልቴቲቱ ምኝታ አካባቢ ሄደው እዚህ ነው እዚህ ነው ብለው ይጮሃሉ። «ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ እንዴት ቤት ውስጥ ትጸዳጃለሽ ባይሆን እኔ አለሁ አይደል እንውጣ አትይኝም» ብለው ድምፃቸውን የበለጠ ከፍ ያደርጋሉ። ሴትየዋም ጎረቤት እንዳይሰማባት ብላ አለቃን ትለምናቸዋለች። ከዚያም ትንሽ አጉረምርመው አክርሚኝ ይላሉ። በዚህ ተስማምተው፤ አለቃም ከርመው ያ የድርቅ ወቅት ያልፍና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚያውቃቸው ሰው አግኝቷቸው «እንዴት ከረሙ?» ይላቸዋል።አለቃም «አሬን ስበላ ከረምኩ» ብለው መለሱ አሉ።

አሬን ስበላ ከረምሁ (2)

(11)አለቃ ገ /ሀና ከጎንደር አዱ ገነት አፄ ምኒልክ መናገሻ ለደጅ ጥናት ሰንቀው በወረሀው ፆም አካባቢ ይጓዛሉ። ጥኌት ወደ ቤተ መንግስት የወጡ ማታ ወደ ማደሪያቸው እየተመላለሱ የወረሀውን ፆም ጨርሰው ፍስክ ሲገባ ወደ ጠጅ ቤቶች ጎራ እያሉ መልከስከስ ይጀምራሉ። የያዙት ደረቅ ስንቅ አልቆ ወደ ማርትሬዛቸው ምንዘራ ጀምረዋል። ወርሀ ግንቦት ገብቶ ክረምቱ ሊጀምር ሲል ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረባቸው --ደጅ ጥናቱን ትተው ወደ ጎንደር ማቅናት ወይም እየተሟጠጠች ያለችውን ኪሳቸውን የሚያደልቡበት መንገድ መፈለግና ክረምቱን አራዳ ማሳለፍ፤ ደጅ ጥናቱንም መቀጠል። ታዲያ አንዷን የጠጅ ኮማሪት መሳም ከጀመሩ ቀኖች ተቆጥረዋል። አንድ ምሽት ግን ተንኮል አዘጋጅተው ኖሮ እሆን ብለው እዳሪያቸውን ሳይወጡ አብረው ይተኛሉ። ከሥራ በኌላ (ከመሳሳም በኌላ) እንቅልፍ መጥቶ የምኝታ ጓደኛቸውን እየረፈረፈ ሳለ፤ አለቃ ቀ .. ሰ . ስ ብለው ከጠፍር አልጋው እራቅ ብለው ይኮሱና ይዘውት ወደ አልጋው ቀ --ሰ --ስ ብለው ይጋደማሉ። ከዚያ የምኝታ ጓደኛቸውን (የጠጅ ቤቱን) ባለቤት መቀመጫ አካባቢ አብሰው የቀረውን ባካባቢው ያልከሰክሱታል። ሊቆዩ አስበው ሽታው ስላስቸገራቸው ሴትዮዋን መቀስቀስ ይገባሉ። ምነው ብለው ሲነቁ ሽታው እያድቀሰቀሰ የሚያመራው ወደሳቸው ጉያ መሆኑን የተገነዘቡ ኮማሪት። አለቃን። ስለፈጠረዎ በማሪያም ይዠወታለሁ። የሚፈልጉትን ሁሉ አደርጋለሁ። ከመሀላችን እንዳይወጣ ማለት። ደጅ ጥናቱንም ቢሆን እስከሚሳካልዎ እዚሁ ከኔ ጋር መቆየት ይችላሉ አሏቸው። አለቃም አይዞሽ ምንም ችግር የለም ያለ ነው። አትሰቀቂ ብለው ያረጋጓታል። በዚህ አስባብ አለቃ ወደ ጎንደር ሳይዘልቁ ክረምቱን ያለምንም ችግር ያሳልፋሉ።በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ደጅ ጠኙ ሁሉ ምኒልክ ግብር ሲገባ እሳቸውም ይገኛሉ። በመገኘታቸው የተገረሙ አፄ ምኒልክም «እንዴ አለቃ እዚህ ምን ስትበላ ከረምህ?» ብለው ሲጠይቋቸው ህ ..ም ብለው «አሬን ስበላ ከረምሁ።» ብለው መመለሳቸውን ሰምቻለሁ።