አር ኤን ኤ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
ኤም-አር ኤን ኤ (መልተኛ አር ኤን ኤ፡ ሐምራዊ - ካርቦን አተም፣ ነጭ - ሃይድሮጅን፣ ቀይ - ኦክስጅን፣ ቢጫ - ናይትሮጅን

አር ኤን ኤ ( RNA ) እንደ ዲ ኤን ኤ ( DNA ) ከኒክሉኢክ አሲድ ( Nucleic acid ) የተወራ ነዉ። እንደ ዲ ኤን ኤ አራት ቤዝ (base) አለዉ። እነሱም አዴናዪን ( A, adenine) ፤ዩራሲል ( U, uracil ) ( ዲ ኤን ኤ ግን በዩራሲል ፋንታ ታያሚን ( T, thymine ) ነው ያለዉ) ጓያሲን ( G, guanine ) እና ሳይቶሲን ( C, Cytosine )። ዲ ኤን ኤ ሆነ አር ኤን ኤ የተሰሩት ከኑክሌይክ አሲድ ነዉ። ኑክሌይክ አሲዶች ደጊሞ ሶስት መሰረታዊ አካላቶችች አላቸው። ቤዝ፡ ሱካሩ ( sugar group ) እና ፎስፌት ግሩፑ ( the phosphate group ) ናቸዉ። አር ኤን ኤን ከዲ ኤን ኤ የሚለየዉ ሌላው ነገር የአር ኤን ኤ ስኳር ሁለተኛ ካሪቦን ሀይድሮክሲል ( hydroxyl group (-OH )) ሲኖረዉ ዲ ኤን ኤ ግን ያለዉ ኤች ( H ) ብቻ ነዉ። ይህም አር ኤን ኤን በጣም ተለካካፊ ( reactive ) አድርጎታል።