አስራት ወልደየስ

ከውክፔዲያ

ፕሮፈሰር አስራት ወልደየስ አዲስ አበባ ተወልደው ድሬዳዋ ያደጉ ሲሆኑ፣ ለመጀመርያ ጊዜ ፕሮፌስናል ስልጠና ያገኙ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ቀዶ ጠጋኝ ነበሩ።

ፕሮፌሰር አስራት ወያኔ ስልጣን በያዘ ጊዜ የወያኔ ተቃዋሚ በመሆን መአሀድ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት መስራችና ዋና ሊቀመንብር በመሆን ታላቅ የወያኔ ተቃዋሚ ሲሆኑ ወያኔም በፍረሀት ወደ እስርቤት ካስገባቸው በሗላ በሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን፣ ጅሩ እነዋሪ፣ መንዝ፣ ተጉለትና ቡልጋ፣ አውራጃ ውስጥ እንዲሁም በመላው የአማራ ክልል የፕሮፌሰር አስራት ተከታዮች በማለት በጣም ብዙ ሕዝብ ጨፍጭፏል። በአሁን ሰዓትም የአማራ ብሔርተኝነት በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የመንፈስ ልጅነት እየተመራ ይገኛል፡፡

በመጀመሪያ ትክክል ነበሩ በኇላ አበላሹት::

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እና የአማራ ህዝብ ትግል!!!!! " አንደበት ላጣ ህዝብ ካልተናገሩለት ወንጀል አይሆንም ወይ ወገኑ ነኝ ማለት" ሀይሉ( ገሞራው) ማሳሰቢያ


ይህ ፅሁፍ ከተፃፈ አራት አመት አልፎታል ፡፡ ነገር ግን በየአመቱ የጓደኞቼ ብዛት ስለሚጨምር ለአዲሶቹ አባላት የተወሰነ ስለ አባታችን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ መረጃ ለመስጠት ያህል ሲሆን በዛውም የሙት አመታቸውን ለማስታወስ ያህል ነው፡፡ ሌላው ፅሁፉን ምስጋናው አንዷለም ( መለክ ሀራ) እኔን አስፈቅዶ << ግዮናዊነት>> የሚለው መፅሀፉ ውስጥ አካቶታል፡፡ ግዮናዊነት ሊወጣ ሲል ምስገጋናው ፅሁፉን በደንብ አጎልብተው እያለኝ እኔም በግሌ ከ 9- 12 ክፍል የሂሳብ መርጃ መፅሀፍ ( mathematics reference book) እየፃፍኩ በነበረበት ሰአት ስለነበረ ተደራረበብኝና ትንሽ ተዘናጋሁ መፅሀፉ ሲወጣ ግን ህዝቡም ሲወደው የተሻለ ባበረክት ኑሮ ብዬ ተቆጨሁ፡፡ ነገሩን ነው እንጂ አሁን ላይ በጋሻው መርሻ የተፃፈ << አንፀባራቂው ኮከብ>> የተባለ የፕሮፌሰር አስራትን ትግል የሚዳስስ መፅሀፍ ስላለ አንባቢዎች በጥልቀት ያንን ቢያነቡ ስል እመክራለሁ፡፡ 1. ግለ ታሪክ ________ እውቁ የቀዶ ጥገና መምህር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሀምሌ 11 1920ዓ.ም በአዲስ አበባ የተወለዱ ሲሆን፤ በሶስት አመታቸው ቤተሰቡ በሙሉ ወደ ድሬደዋ በመዛወሩ እድገታቸው ድሬደዋ ሊሆን ችሏል፡፡ ጣልያን ኢትዮጲያን ሲወር ገና የ8 አመት ልጅ ቢሆኑም የወረራው ወቅት ግን ለብላቴናው አስራት መጥፎ ትዝታን ጥሎ ያለፈ ነበር:: ገና በመጀመሪያ አመት ላይ ፋሽስት ጣሊያን አያታቸውን ቀኝ አዝማች ፅጌ ወረደን ወደ ጣልያን በምርኮ የወሰዳቸው ሲሆን፣ የ1932ቱን የግራዚያኒ ግድያ ሙከራ ተከትሎ ከ30,000 በላይ ኢትዮጲያዊ ሲያልቁ አባታቸው አቶ ወልደየስ አጥላየ አንዱ መስዋዕት ሆኑ፡፡ ይህንን ተከትሎም በባላቸው ሀዘን ከፍተኛ ህመም ላይ የወደቁት እናታቸው ወዲያውኑ ሞቱባቸው፡፡


በ1933ዓ.ም ኢትዮጲያ ከጣሊያን ነፃ ስትወጣ ወደ አዲስ አበባ የመጡት አስራት ወልደየስ በሚቀጥለው አመት ማለትም በ1934ዓ.ም በተፈሪ መኮንን ት.ቤት ዘመናዊ የቀለም ትምህርት ጀምረዋል፡፡ በትምህርት ላይ ጥሩ አቀባበል የነበበራቸው ይህ ምሁር በ1935ዓ.ም የፎቶ ካሜራ ተሸልመዋል፡፡ በኀላም ከ42ቱ ምርጥ ተማሪዎች አንዱ ሆነው የውጭ የመማር እድል አግኝተዋል፡፡ በግብፅ አሌክሳንደሪያ ቪክቶሪያ ኮሌጅ በ1948ዓ.ም በቀዶ ጥገና ሙያ በጥሩ ነጥብ ተመርቀው የወጡት ፕሮፌሰር አስራት ወደ ሌላ ለገር ለመሄድ ወለም ዘለም ሳይሉ ደሀውን ወገናቸውን ሊያገለግሉ ወደ ሀገራቸው መጥተዋል፡፡ ለተከታታይ አምስት አመታት ህዝቡን ሲያገለግሉ ቆይተው ወደ እስኮትላንዱ Edinburgh University specialized ለማድረግ ተመልሰው ሄደዋል፡፡ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ሀገር ቤት ከረጅም ግዜ ልፋት በኀላ የሙያ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን የመጀመሪያውን የህክምና ት.ቤት አቋቁመዋል፡፡ በሙያቸው መምህር፣ ሀኪምና የት.ቤቱ ዲን ሆነው ደሀውን ህዝባቸውን አገልግለዋል፡፡ ለዚህም እስከ ንጉሱ የግል ሀኪምነት ድረስ ደርሰዋል፡፡ 2. በወታደራዊው ደርግ ዘመን _____________________ ወታደራዊው መንግስት ስልጣን እንደያዘ ንጉሱን ገሎ ለህዝብ የሰጠውን መግለጫ professor John H. spencer ' Ethiopia at bay' በሚል መፅለፋቸው ሁኔታውን ሲገልፁት፦ " The Dergue announced that Haile selassie has been found dead in bed and that it had immediately summoned the former Emperor's physician Dr. Asrat woldeyes with considerable courage, the doctor publicly denied any such summons. He has been at home all day and no such call ever reach him." ይህም ማለት በግርድፉ (ደርግ ንጉሱን ገሎ ለህዝብ በሰጠው መግለጫ << ሲታመሙብን የግል ሀኪማቸውን እሰጠርቸን ነበር ግን ቤታቸው አልነበሩም>> ሲል ፕሮፌሰሩ ግን << በሰአቱ ቤቴ ነበርኩ መንም የጠራኝ የለም >> ሲሉ ንግግሩን ተቃውመዋል)


በዚህ የተጀመረው ግንኙነት በኀላም የደርግ ካድሬዎች የህክምና ት.ቤቱ ላይ ሊያሳርፉት በሚሞክሩት የሶሻሊስት ፅንሰ ሀሳብ በተደጋጋሚ ፕሮፌሰሩ ጋር ሳያስማማቸው ኖሯል፡፡ ይህም ሆኖ ግን በ1970ወቹ መጀመሪያ አካባቢ ከሰሜን ተገንጣዮች ጋር ያደርገው የነበረው ፍልሚያ ላይ ፕሮፌሰር አሰራት ሙያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ወደ ቦታው አቅንተው ነበር፡፡ 3. በኢህአዴግ ዘመን ________________ ምሁር በአይኔ አልይ የሚለው ይህ መንግስት ገና ከጅማሮው ነበር ፕሮፌሰሩሠ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ የጀመረው፡፡ በወቅቱ በመንግስት ቁጥጥር ስር ይታተሙ በነበሩ ጋዜጦች( እፎይታ፣ ማለዳ፣ አዲስ ዘመን፣ አቢዮታዊ ዲሞክራሲ...) ፕሮፌሰሩ ከደርግ ጋር ሆነው እንደወጉት አድርገው መፃፍ ጀመሩ፤ በወቅቱ ፕሮፌሰሩ ሲጠየቁ ግን፦ " እኔ የህዝብ ልጅ ነኝ በሙያየ ከንጉሱ እስከ መንግስቱ ሀ/ ማርያም ቤተቦች፤ ከድሀ ገበሬ አስከ ወታደር የሙያው ስነምግባር በሚጠብቅ ሁኔታ አገልግያለሁ። እነሱ እንደሚሉትም ሳይሆን ምፅዋ ላይ የኢትዮጲያ ወታደር ወይም የተገንጣይ ሳንል አክመናል፡፡ አሁንም ቢሆን እርዳታየ ካስፈለጋቸው ለእነሱም ለማገልገል ችግር የለብኝም፡፡" ነበር ያሉት፡፡


ፕሮፌሰር አስራትን ለየት የሚያደርጋቸው ስብእና በሙያው እንዳሉ ሌሎች አጋሮቻቸው፤ የራሳቸው የግል ህክምና ተቋም ገንብተው ገንዘብ ለመሰብሰብ አንድም ቀን ያልሞከሩ ሲሆን፤ ህይወታቸውን በሙሉ ለህዝብ ችግር አሳልፈው የሰጡ ነበሩ፡፡ 4. የፖለቲካ ህይወት _______________ እዚሀህ ላይ ብዙዎች የሚጠይቁት ጥያቄ ዋናው ይህ ትልቅ ምሁር እንዴት ወደ ዘር ፖለቲካ ሊገቡ ቻሉ? የሚለው ነው። ለዚህም ራሳቸውን ጨምሮ ብዙ ፀሀፊዎች እንደሚያስቀምጡት የተለያዩ ምክንያተቶች አሉ ከእነሱም ውስጥ፦


ሀ. በሰኔ መጨረሻ 1983ዓ.ም በአውሮፓውያን እና አሜሪካ አቀናባሪነት የተደረገው "national peace conference" ፕሮፌሰሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ወክሎ የታደመው ቡድን አባል ሆነው ተሰብስበው ነበር፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ዘሮችን የወከሉ ቡድኖች ሲኖሩ በህዝብብዛቱ ሁለተኛ የሆነውን አማራን የወከለው ቡድን የለም ነበር፡፡ የስብሰባው ዋነኛ አጀንዳም 'ስለተጨቆኑ ብሄር ብሄረሰቦች ...ምናምን ' ሲሆን ጨቋኝ ሆኖ የቀረበው ቡድን ደግሞ አማራው ነበር፡፡ ይህ ነገር መንግስት በሚቆጣጠራቸው ሚዲያ ሳይቀር አማራው ደርግና የአፄው ስርአት ላጠፉት ጥፋቶች ሁሉ እንደ ዋና ባለቤት ተደርጎ ተወሰደ፤ ቋንቋው ቆሻሻ ቋንቋ/ dirty language/ ወይም እንደ ኦነግ አጠራር ( Afan Ajawa) ተብሎ ይጠራ ጀመር፡፡ በግልፅም የመንግስት አካል የነበረው የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ታምራት ላይኔ ሳይቀር ኤርትራ ሄዶ በአማራው ስም "በነፍጠኛው ስርአት ለተደረጉ ማንኛውም ግፍ እና በደል እኔ በአማራው ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ" የሚል ሰንፋጭ ንግግር አድርጎ መጣ፡፡ ይህ ሁሉ በሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳ ፍሬ አፍርቶ ወደ ተግባር ተለወጠ፡፡


ለ. ይህንን የቃላት ጦርነት ወደ ተግባር ለመለወጥ ሁለም ታጣቂ ሀይሎች ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ኦነግ፣ ኦህዲድ/ ኢህአዲግ/... በበደኖ 154 ሰው፣ ጊራዋ፣ ኩርፋ ጨሌ፣ ለንጋ፣ ኬርሳ፣ ሶካ፣ ደደር፣ ሂርና፣ ቁኒ፣ መስላ፣ ጋሊቲ፣ ደባ የቸባሉ አካባቢዎች ከ 1000 ሰው በላይ፤ አርባ ጉጉ ላይ ከሞተው ውጭ ከ32,000 በላይ ሰው ከመኖሪያው ተፈናቅሏል ፡፡ አርሲ ነገሌ 60 ሰው፣ ወለጋ ከ200 ሰው በላይ እንደ ዱር እንስሳ ታድነው ተገለዋል፡፡ ይህ ከብዘ በጥቂቱ ነው፡፡ ሴቶችን መድፈር፣ ፅንሳቸውንን በጩቤ እያወጡ ማሳየት ዋና መዝናኛቸው ነበር፡፡ ይህ ሁላ ሲሆን ወያኔ/ህወሀት/ ዳር ቆሞ ለኦነግ እና ሌሎቸች መሳሪያ እያስታጠቀ ያልታጠቁ ንፁህ ገበሬ አማሮችን አስጨፈጨፈ። የሚገርመው በቀደመ ስሙ ኢህዲን የጥምቀት ስሙ ብአዲን የሚባለው ድኩማን ድርጅት ይህ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲካሄድ አንድም ተቃውሞ አላደረገም፡፡ ከበአዲን ይልቅ # የኢሳ_ ሶማሌ_ጎሳዎች ለመንግስት ባስገቡት ደብዳቤ እንደገለፁት "ይህ በኦነግ እና ኦህዲድ አማካኝነት የሚደረግ ንፁሀን ጭፍጨፋ ማስቆም ካልቻላችሁ እኛ ጣልቃ ገብተን እናስቆማለን" የሚል የወንድማዊ እና ታሪክ የማይረሳው ስራ ሰርተውልናል፡፡


እንግዲህ ከላይ የጠቀስናቸው ምክንያቶች እና ሌሎችም ተጨምረው ናቸው ፕሮፌሰሩን መአህድን ጥር ወር 1984ዓ.ም ሊያቋቁሙ ያስቻላቸው፡፡ መአህድ ( መላው አማራ ህዝባዊ ድርጅት) ገና ከጅማሮው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ፅህፈት ቤት የከፈተ ሲሆን፡፡ በተለያየ መንገድ ተፅዕኖ ማድረግ ጀመረ፡፡ በህዳር ወር 1985ዓ.ም ደብረ ብርሃን ላይ ያደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ድርጅቱን በመንግስት ደህንነቶች ክትትል ስር እንዳይወጣ አደረገው፡፡ መአህድን እንደፈሩት የሚያስታውቀው በወቅቱ የመከላከያ ሚኒስተር የነበሩት አቶ ስየ አብርሃ የድርጅታቸው ስብሰባ ላይ፦ " forget colonel Goshu Wolde, forget all those who make war declaration from abroad. Concentrat on the biggest challenge at home i.e Professor Asrat. If we under the dergue had got the chance which Professor Asrat enjoys today in organizing and mobilizing his AAPO( መአህድ ) followers, it would not have take us 17 years long to topple the Mengistu regime" ....ይህ የሚያመለክተው ወያኔ መአህድን ምን ያህል ፈርቶት እንደነበረ ነው፡፡ ከመስከረም እስከ ሀምሌ 1985ዓ.ም ብቻ ከ40 በላይ የመአህድ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ታስረዋል፡፡


ፕሮፌሰር አስራት ከአርባ አንዱ የዩኒቨርስቲ መምህሮች ጋር 'በአቅም ማነስ' በሚል ፖለቲካዊ ስም ማጥፋት ታርጋ በገነት ዘውዴ በሚመራው ትምህርት ሚኒስተር ተባረዋል፡፡ ይህ እንግዲህ የሚሆነው ከ Edinburgh university የተመረቁትን ምሁር በደደቢት በረሀ ምሩቃን መሆኑ ነው፡፡


በ1986ዓ.ም መንግስታዊው ጁንታ እውቁን ምሁር ደብረ ብርሃን ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር አማካኝነት " መንግስትን በሀይል ለመገልበጥ አሲረዋል" ሲል ሁለት አመት ፈረደባቸው፡፡ እዛው እስር ላይ እያሉ በ1988ዓ.ም እንደገና በሌላ ክስ ሶስት አመት ጨመረባቸው፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ከ65 አመት በላይ የነበሩ አዛውንት ላይ ነበር፡፡ ፕሮፌሰር ከዚህ አመት በኀላ ግን ጤና አጡ በተከታታይም ሀኪሞች የውጭ ህክምና ያስፈልጋቸዋል ቢባልም መንግስት ሊቀበል አልቻለም፡፡ በመጨረሻ ከተዳከሙ በኀላ በታህሳስ ወር 1991ዓ.ም ወደ ውጭ እንዲሄዱ ቢፈቀድም በጣም ተዳክመው ስለነበር ከ5 ወር በኀላ ግንቦት 6 1991ዓ.ም በPhiladelphia ሊያርፉ ችለዋል፡፡


የዚህ ፅሁፍ ባለቤት ከተለያየ ቦታ የጨመቀውን ይችን ፅሁፍ የፃፈው አንድም ታላቁን መምህር ለማስታወስ ነው፡፡ ሌላው የአሁኑ ትውልድ ከዚህ ምን ይማራል? የሚለውን ሁሉም በየቤቱ እንዲያስብበት ነው ፡፡ በተጨማሪም

  1. የአማራው_መደራጀት ግድ መሆኑን ለማስመር ነው፡፡ በመጨረሻ ስለ

አማራዊነት ማሰብ ተመርጦ የሚገባበት ጉዳይ ሳይሆን ከመገፋት፣ ከጭቆና የሚመጣ መሆኑን ለማጠየቅ ነው፡፡ reference


1. ነፀብራቅ 2. ዶ.ር አሰፋ ነጋሽ " reflection on the work of professor Asrat: 1997" 3. Amnesty international press release on July 1, 1994