Jump to content

አስከናዝ

ከውክፔዲያ

አስከናዝኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 መሠረት የጋሜር (ያፌት) ልጅ ነው። በትንቢተ ኤርምያስ 51፡27 ደግሞ ከአራራትና ከሚኒ መንግሥታት ጋር የአስከናዝ መንግሥት በባቢሎን ላይ እግዚአብሔር ይጠራል።

በአውሮፓና በአይሁዶች አፈ ታሪክ ዘንድ፣ አስከናዝ (ወይም አስካኔስ) የእስኩቴስና የጥንታዊ ጀርመን አገሮች አባት እንደ ነበር ይቆጠራል። እስኩቴስ ወይም የሳካ ሕዝብ በአሦርኛ መዝገቦች «አሽኩዝ» ይባል ነበር።

Royal Genealogies (1724 ዓ.ም. ታተመ)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጄምስ አንደርሶን በ1724 ዓ.ም. የተጻፈው መጽሐፍ Royal Genealogies (ንጉሣዊ የዘር ሐረጎች) ስለ አስከናዝ የሆኑትን ልማዶች ተርኮ የጥንታዊ ጀርመን አገር መጀመርያው ንጉሥ እንደ ነበረ ይላል፦

አስከናዝ፣ ወይም አስካኔስ፣ በአቬንቲኑስ ዘንድ ታላቁ ቱዊስኮ፣ በሌሎችም ቱዊስቶ ወይም ቱዊዞ ተብሎ (አቬንቲኑስ የኖህ 4ኛው ልጅ ያደገዋል፣ ግን ያለ ታማኝነት) ከማየ አይኅ 131 አመታት በኋላ በኖኅ ወደ አውሮጳ ተላከ፤ ከ20 ሻለቆች ጋራ ሂዶ በታናይስ ዙሪያ በጥቁር ባሕር ምዕራብ ዳርቻ ላይ ሠፈረ (ይህም ባሐር ባንዳንዶች ከእርሱ «አስከን» ይባላል)። በዚያ የጀርመንና የሳርማትያ ሰዎች መንግሥት መሠረተ።... ይህ የአስከናዝ ዕድሜ 24 አመት ሲሆን ነበር፤ እርሱ ከ200 ዓመታት በላይ ኖረና፣ ለ176ም ነገሠ።