አሹር-ናዲን-አፕሊ

ከውክፔዲያ
የአሹር-ናዲን-አፕሊ ስም በጡብ ላይ ተቀርጾ

አሹር-ናዲን-አፕሊ ከ1213 እስከ 1209 ዓክልበ. ግድም ድረስ የአሦር ንጉሥ ነበረ። አባቱን 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታን ገድሎ መንግስቱን ቃመበት። በአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ለ፬ (ወይም እንደ ፩ዱ ቅጂ ለ፫) ዓመታት ገዛ፤ ከዘመኑም አንድ የሊሙ አመት ስም («የኤሪብ-ሲን አመት») ከቅርሶቹ ታውቋል።