አበጋዝ ክብረዎርቅ
አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉ ሙዚቃ አቀናባሪዎችና ኪቦርድ ተጫዋጮች አንዱ ነው።
{ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችን ሰርቷል።
- አበጋዝ_ክብረወርቅ_ሺኦታ
የሙዚቃው ኢንጅነር . ሙዚቃ ፕሮዲውሰር፣ አቀናባሪ፣ መምህር እንዲሁም ሙዚቀኛ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሺኦታ ;የሙዚቃ አቀናባሪዎች አንድን ግጥምና ዜማ አቀናብረው፣ ለጆሮ ለየት የሚሉና ልብን የሚማርኩ፣ ሰዎችን በተመስጦ ወደ ሌላ ቦታ የሚወስዱ ዘፈኖችን መፍጠር ይችላሉ፡፡ ለሙዚቃ ፕሮዲውሰር፣ አቀናባሪ፣ መምህር እንዲሁም ሙዚቀኛ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሺኦታ እውነተኛ ሙዚቃ ጆሮን ኮርኩሮ ልብን የሚመስጥ እንዲሁም የነፍስ ምግብ የሚሆን ነው፡፡ ዘመን ከማይሽራቸው ዜማዎች ጀርባ ያለው አበጋዝ ነው፡፡ በሙዚቃው የተለያየ ትውልድን ማገናኘት ችሏል፡፡ ለሀገራችን ሙዚቃ የተሰጠ ልዩ አአቀናባሪ መሆኑን ብዙዎች ይመሰክሩለታል።ብዙ ጊዜውን የሚያሳልፈው ስቱዲዮው ነው፡፡ ስለ ውልደቱ ግማሽ ኢትዮጲያዊ ግማሽ ጃፓናዊ ነው የተወለደው ጃፓን ሲሆን ቀኑም እ.ኤ.አ ሰኔ 14;1976 ነው። ያደገው በኢትዮጲያ ሲሆን ገና የአንድ ዓመት ልጅ እያለ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን በቅዱስ ዮሴፍ እና በሊሴ ገ/ማርያም ት/ቤት ተምሯል፡፡ የመጀመሪያ የተጫወተበት ፕሮፌሽናል ባንድ ዳህላክ ነበር፡፡ ከዛም በኢትዮ-ስታር፡ በዋቢሸበሌ ባንድ ተጫውቷል፡፡ ከሀገር ከወጣ በኋላ ከሙሉቀን መለሰ ጋር ለኹለት ዓመታት ተጫውቷል፡፡የሙዚቃ ትምህርትን በበርክሌ ዩኒቨርሲቲ ሙዚቃ ተምሯል፡፡ …….. ትህትናው፡ ብሔራዊ ስሜቱና ለሌሎች ያለውን አድናቆት ብዙዎች ያወሱለታል፡፡ በዚኽም ያከብሩታል፡፡ ከ100 በላይ አልበሞችን አቀናብሯል ጥላሁን ገሰሰ፣ማህሙድ አህመድ፣አስቴር አወቀ፣አሊ ቢራ፣ቴዋድሮስ ታደሰ፣ኤፍሬም ታምሩ፣ንዋይ ደበበ፣ፀሀዬ ዮሀንስ፣አረጋኝ ወራሽ፣ሀመልማል አባተ፣ኩኩ ሰብስቤ፣ነፃነት መለሰ。。。 ከአሁኑ ድምፃውያን ደግሞ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ጎሳዬ ተስፋዬ፣ህብስት ጥሩነህ፣ሚካሄል በላይነህ፣ታምራት ደስታ፣ዳዊት መለሰ፣ግርማ ተፈራ፣ሀይልዬ ታደሰ፣ሸዋንዳኝ ሀይሉ፣ሄለን በርሄ፣የኛ。。。እሱ ከሰራላቸው ሙዚቀኞች ውስጥ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ በፊልም የተሳተፈበት ቀሚስ የለበስኩለት ፊልም በ2ተኛው ጉማ አዋርድ ምርጥ ስኮር አሸናፊ ነበር አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ። @ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ተመኘውልህ ምንጭ:-ከተለያዩ