አባል:ኑሩ ሙሃመድ

ከውክፔዲያ

አብሽ እና ጥቅሙ

1.አብሽ የኮሌስትሮልና የደም ውስጥ የስኳር መጠንን ከመቀነስ ባሻገር ሌሎች የጤና ችግሮችን ለማከም ይጠቅማል፡፡

2.የአብሽ ፍሬና ቅጠሉ ምግብን ለማጣፈጥና ለቅመምነት ይውላል፡፡ምግብን ከማጣፈጥ በተጨማሪ በግብፅ፣ጣሊያን ፣እና ግሪክ ሀገራት የተለያዩ በሽታዎችን ለማከም ይጠቀሙበታል፡፡

3.ኮሌስትሮል መቀነስ ከፍተኛ መጠን ያለው የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስና ጤነኛ ሆነን እንድንቆይ ያስችላል ፡፡ጥናቶች እንደሚያሳዩት አብሽ በተለይም መጥፎ የተባለው ኮሌስትሮል እንዳይፈጠር በማስረግ (absorbtion) ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

4.ለልብ ጤንነት አብሽን አብዝቶ መጠቀም የልብን ጤንነት እንደተጠበቀ እንዲቆይ ያደርጋል፡፡

5.ለስኳር ህመም የስኳር በሽተኛ ከሆኑ እንዲሁም ምልክቶቹ የሚታዩ ከሆነ በቋሚነት አብሽን መጠቀም ይኖርብዎታል፡፡”ካላክቶማንናን ” የተባለ ሟሚ ፋይበር ሰውነታችን የሚወስደውን የስኳር መጠን ዝግያለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡እንዲሁም ኢንሱሊንን የማነቃቃት ተፈጥሮአዊ ባህሪ አለው፡፡

6.ለምግብ ማስተላለፊያ ቧንቧ የምግብ ልመትን ያፋጥናል፣መርዝ ከሰውነት እንዲወገድ ይረዳል፡፡ በተለይም በሻይ መልክ ከተጠቀምነው የጨጓራ ህመምን ያስታግሳል፡፡

7.ቃርን ለማስታገስ ተደጋጋሚ የቃር ችግር ካለብዎት በሚበሉት ምግብ ውስጥ አንድ ማንኪያ የራስ አብሽ በመጨመር የጨጓራና የአንጀት ግድግዳን እንዲለሰልስ በማድረግ ቃርን ያስታግሳል፡፡

8.ክብደትን ለመቀነስ ክብደትዎን ለመቀነስ ካሰቡ የራሱ የአብሽ ፍሬዎችን በባዶ ሆድ መውሰድ አላስፈላጊ የሆኑ ስቦችን ለማስወገድ ይጠቅማል ፡፡