አባል:የሱፍ አህመድ

ከውክፔዲያ
                 የሳት እራት

ምድርን ያለ ካስማ ያቆመ ፈጣሪ ለታረዘ አልባሽ ላጣ ተቆርቋሪ

  ለተራበ አጉራሽ አጀጋኝ ለፈሪ
  ራቂን የሚናፍቅ ና ብሎ ተጣሪ

ለኩነኔ ቀራን ፅድቅን አስተማሪ

                   አይ ፈጣሪ፣

እንዲህ ብለህ ፅፈህ በመለኮት መፅሀፍ ላንተ የወገነ ከድሜው ሰጥቶህ ምእራፍ በቃልህ ላበለ ሽመል መዞ ዘራፍ በአይነ ህሊና ከኤደን ገነት በራፍ፣

  እራስ ወዳድ ፃድቅ ራሱን አላዋቂ
  ባይነት የተጧፈ ጣል አርጎ ብጫቂ

ፈጣሪ ከፃፈው አንድ እንኳ ሳይደርሰው በልብሱ ቀዳዳ ብርድ አየጠበሰው

  አፉን ሚያርስበት ሳይኖረው ጠብታ

አንኳን የሚቀምሰው

  ላመል ስሙ ጠፍቶት እሚሉት ገበታ፣
እንዲህም ሆኖ

ቃሉ ለኔ ብቻ ላንተ የለም እያለ ከትንቢቱ ግርጌ ቁልል ስሙ እንዳለ ስንት ጊዜ አሰቦ ስንት ጊዜ ማለ፣

  ርስት ይመስል ገነት ከገዥ ላልጋ ወራሽ
  ሁሉን በጠቀሰ ለኔ ይላል ጭራሽ፣

ፈጣሪም

  ይህን ቃል መስጠቱ ከመፅሀፉ ላይ
  እንደ ሰምና ወርቅ ሊለይ ብሎ ነው
                      የዋህና አስተዋይ፣ 

ጮማ ቀርቦ ሳለ ሆዱን ፊጥኝ አስሮ ከሰል መሳይ አሹቅ ላንጀቱ ወርውሮ ድሀ ወይን ይጠጣ ይርሳ ድህነቱን ምትለውን ሀረግ ዘንግቶ የጠቢቡን

      አልያ ከሰለሞን እኔ እሻል ብሎ
      ፃድቅ ነኝ ባይ ፃድቅ ፅድቅናን አጉድሎ
      የወይኑን አጸድ በቀጋ ከልሎ
      ባቄላን ምጣድ ላይ ሰርክ አንከባሎ
 አሹቅን ከኑሮው እያመሳሰለ

ድህነት ፅድቅ ነው

 ስለዚህም ድሀ ከቶም ድህነቱን እንዳይረሳው አለ?

ነኝ ባዩ ግን

  ቃሉ ለታረዘ ገነት ለተራበ
  በመሠለው ብቻ መስሎት የቀረበ

ስንት ጊዜ አስቦ ስንት ጊዜ ማለ ቃሉ ለኔ ብቻ ላንተ የለም እያለ አቻ ለአቻ አረገው እግዜሩ ለሁሉም በቂ ሆኖ ሳለ፣

    ሌላው ሁሉ ይቅርና

ፊት ቃል አለኝ ብሎ ለሚመፃደቀው እንደ ጥያቄ አይቶ መልሱን ቢመልሰው፣

    አስኪ ልጠይቀው ሽው ካለው ድንገት
    ለሰውም አይደለ ለራሱ ሰውነት
    ካለው ትርፍ እራፊ ዝናብ ለጣለ ለት።
                             #