Jump to content

አባል:AllThisPaperwork/ኤድዊን አቦት አቦት

ከውክፔዲያ

 ኤድዊን አቦት አቦት FBA (ታህሳስ 20 1838 - ጥቅምት 12 1926) [1] የእንግሊዛዊ መምህር እና የሃይማኖት ምሁር ነበር፣ በይበልጥ የኖቬላ ፍላት ላንድ (1884) ደራሲ በመባል ይታወቃል። ኤድዊን አቦት አቦት፤ የኤድዊን አቦት (1808 – 1882) በሜሪሌቦን የፊሎሎጂ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር እና ሚስቱ ጄን አቦት (1806 – 1882) የበኩር ልጅ ነበር። ወላጆቹ የአጎት ልጆች ነበሩ።


አቦት ትምህርታዊ መጽሃፍትን ጽፏል፣ አንደኛው ቪያ ላቲና፡ በ1880 የታተመ እና በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ በአለም ዙሪያ የተሰራጨው የመጀመሪያው የላቲን መጽሐፍ ነው።

የፍላትላንድ ርዕስ ገጽ፣ 1884

የአቦት በጣም የታወቀው ስራው በ1884 የፃፈው ልቦለድ ፍላት ላንድ፡ የብዙ ዳይሜንሽን ሮማንስ ሲሆን ባለሁለት አቅጣጫዊ አለምን የሚገልጽ እና የልኬቶችን ተፈጥሮ የሚዳስስ ነው። ምንም እንኳን በትክክል "የሂሳብ ልብ ወለድ" ተብሎ ሊጠራ ቢችልም ብዙውን ጊዜ እንደ ሳይንሳዊ ልብ ወለድ ይመደባል።

ከ1950ዎቹ ጀምሮ እስከ አሁን ያለው ዘመናዊ የሳይንስ ልብወለድ መምጣት፣ ፍላት ላንድ ታዋቂነትን ጨምሮታል፣ [2] በተለይ በሳይንስ ልብወለድ እና በሳይበርፐንክ አድናቂዎች። [3] ብዙ ስራዎች በዚህ ኖቬላ ተነሳሽነት ተጽፈዋል፣ ተከታታይ ልብ ወለዶች እና አጫጭር ፊልሞችን ጨምሮ። [3]

ዋቢ መጽሃፍት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ Thorne and Collocott 1984, p. 2.
  2. ^ Clute and Nicholls 1995, p. 1.
  3. ^ Harper 2010