አባል:Codex Sinaiticus

  ከውክፔዲያ

  አስራት ባንጫ ከአባታቸው ከአቶ ባንጫ ፊጋ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዳቂቴ ዱካሞ በ1968 ዓ,ም በድሮ ስዳሞ ክ/ሀገር ወላይታ አውራጃ በአሁኑ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ሞኮኒሳ ወይጌ ቀበሌ ተወለዱ፡፡

  ትምህርታቸውን አንደኛ ደረጃ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በተወለዱበት ቀበለ የተከታተሉ ሲሆን 7ኛንና 8ኛ ክፍልን በአቅራቢያቸው በሚገኘው ወረዳ በኤዶ ድጉና ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በወረደቸው በሚገኘው በቦዲቲ መሰናዶና 2ኛ ደረጃ አጠናቅቀው ወደ ዪኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት በማምጣት በ1998ዓ,ም ወደ ዲላ ዪኒቨርስቲ ገብተዋል፡፡
  
  ከ1998ዓ,ም እስከ 2000 ድረስ በመቀጠል ከሦሥት አመት ቆይታ በኀላ በአማርኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግርያቸውን ከዲላ ዪኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡
  

  በመቀጠልም ትምህርትን ለመማር ካላቸው ፅኑ ፍላጎት የተነሣ በከረምት ፕሮግራም ከ2008ዓ,ም እስከ 2011ዓ,ም ድረስ ትምህርታቸውን ተከታትለው ሁለተኛ ዲግርያቸውን በ2011ዓ,ም ከደብረብርሃን ዪኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡

  ሥራን በሚመለከት በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁበት ጊዜ ጀምረው ይህ ጽሁፍ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በተከታተሉበት በቦዲቲ መሰናዶና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሙያ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡