አባል:Siltew

ከውክፔዲያ

#ሙጎ_ተራራ

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ዛሬ ወደ ስልጤ ዞን ተጉዞ በሀገራችን ረዥም ከሚባሉ ተራሮች አንዱ የሆነውን የሙጎ ተራራ ያስጎበኘናል፡፡) (ሔኖክ ስዮም በድሬትዩብ) ወራቤ ደርሰናል፡፡ ከአዲስ አበባ 173 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፤ ከጅማ የምትመጡ አልያም ወልቂጤ ያላችሁ በዚያው ከወልቂጤ ሆሳእና በሚወስደው መንገድ መምጣት ትችላላችሁ፡፡ ሙጎ እዚህ ቦታ ነው ተብሎ አይነገርም፡፡ ሙጎ ራሱ እንደተኮፈሰ አለሁ ይላልና፡፡ ወጣቷን የስልጤዎች መዲና ለቀን ወደ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ እያቀናን ነው፡፡ ደጋማው የስልጤ ምድር ከሙጎ የሚተፋ ጭጋግ ለብሷል፡፡ ከወራቤ 91 ኪሎ ሜትር ከአዲስ አበባ ደግሞ 264 ኪሎ ሜትር መጥተን ያሰብንው ጋር ደርሰናል፡፡ አናታችን ላይ ቢሆንም፤ እግሩ ስር ብንደፋም፤ ከሙጎ ተራራ ጋር እየተያየን ነው፡፡ ሙጎ እንደ ጎሚስታ ከወልቂጤ ወደ ሆሳዕና በሚወሰደው የመኪና መንገድ ጎዳናው ጥግ የቆመ ግዙፍ ተራራ ነው፡፡ አየሩ ደስ ይላል፡፡ ምናልባትም የተራራው ስነ ምህዳር የፈጠረው የአየር ንብረት ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄ ግዙፍ ተራራ ውበት ብቻ ሳይሆን የብዝሃ ህይወት ማዕከልም ነው፡፡ ርዝመቱ ከስልጤ ዞን ባለፈ በደቡብ ክልልም በቁመታቸው ከሚጠቀሱ ተራሮች ያስመድበዋል፡፡ ሙጎ የታደለ ተራራ ነው፡፡ መንገድ ዳርቻ የመኖሩን ያክል አልተራቆተም፡፡ የበርካታ ብርቅዬ አእዋፋትና የዱር እንሰሳት መኖሪያ ነው፡፡ የአካባቢው ሰው በሌላ ስያሜ ይጠራዋል፡፡ ‹‹ሚዳቻ›› የሙጎ ሌላኛ ስሙ ነው፡፡ ትርጉሙ የስልጤ ባህላዊ ምድጃ እንደማለት ነው፡፡ ይህንን ያስባለው በአካባቢው ከሚገኙት ሌሎች አነስተኛ ኮረብቶች መካከል ከፍ ብሎ የሚገኘው ገጽታው ነው፡፡ ሙጎ በከርሰ ምድር ውሃ ሀብቱ የታደለ ነው፡፡ ከስሩ በርካታ ምንጮች ይፈልቁበታል፡፡ ከባህር ጠለል በላይ 3277 ሜትር ከፍታ ካለው አናቱ ደስ የሚል ቀዝቃዛ አየርና በብርድ ወቅት የሚንደባለል ጉም ይተፋል፡፡ የተራራው ሰንሰለት ወደታች ዝቅ ብሎ ነው የሚገኘው፡፡ አናቱ ላይ ማማ ነው፡፡ እንደልብ የሚያዩበት የጉራጌ፣ የሀድያና የጊቤ ማዶ ዞኖችና የስልጤ ዞን መንደሮች ያዩበታል፡፡ አናቱ ላይ ያመሹ የአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ ማታ ማታ የጅማ ከተማ መብራት ቦግ ብሎ ይታያል ሲሉ ያዩትን ይተርካሉ፡፡ ሙጎ የተፈጥሮ ብቻ አይደለም የታሪክም መስህብ ነው፡፡ የጣሊያን ወረራ ወቅት ወራሪው ጦር የመመሸገበትና እራሱን ለመከላከል ስትራቴጂክ ቦታ በመሆኑ የመረጠው ስፍራ ነው፡፡ ተራራው አናት ላይ ቢላል የሚባል ጥንታዊ መሰጂድና አንድ ዋሻ ይገኛል፡፡ ሙጎ ተራራና አካባቢ በኢትዮጵያ ከሚገኙ 69 ዋነኛ የአዕዋፍ መገኛ ቦታዎች አንዱ ነው ይሉታል፡፡ የወፍ አጥኚዎች፤ ደግሞም ስሩ ሆነው የማያቋርጠውን የአእዋፍ ድምጽ ሲሰሙ እርስዎም እውነት ነው ይላሉ፡፡

#Siltew

ሙጎ ተራራ ማለት የሰሃባው ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ አዛን ያለው #ቢላል መስጂድ የሚገኝበት ከፍተኛ ቦታም ነው።