Jump to content

አባል:Zebegna Sefer Addis Ababa

ከውክፔዲያ

የዘበኛ ሰፈር አዲስ አባባ ዛሬ ሒልተን ሆቴል ካለበት ከበስተኋላው የሚገኝ ሲሆን፣ ከገብርዔል መሳለሚያ ጀምሮ የስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በኩል በማርሻል ቲቶ ቤት ዞሮ ወደ ኢዮቤልዩ ቤተ መንግስት አስከ ሂልተን ከዘያም የሰማንያ ሁለት አፓርትሜንት የሚገጥም ነው።በዚህ ሰፈር ውስጥ እንደሌላው አካባቢ ሁሉ የወጣቶች መረዳጃ ማህበር ነበር።ይህ የወጣቶች ማህበር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አከናውኗል።ሰፈሩ ውስጥ ለቤተስብም ሆነ ለሌሎች በመላላክ አግልግሎት፣ በክረምት ጎርፍ ሲመጣ ጎርፉ የሚሄድበትን በማምቻቸት፣ ድንጋይ አንጥፎ መንገድ ሰፈሩ ውስጥ በመስራት፣ በዓመት አንድ ጊዜ በድንኳን ውስጥ የተለያዩ ግጥሞችንና ቲያትሮችን ዘፈኖችን በማዘጋጀት ወላጆችን በማዝናናት፣ ለቅሶ ላይ ሶስት ቀናት ሃዘን ቤት በመገኘት ሃዘንተኛውን ማስተዛዘንና የሃዙኑ ተካፋይ እንግዶችን እጅ በማስታጥብ፣ ምግብ በማቅረብና በማንሳት፣ ቡናን ሻይ በማፍላት፣ ወዘተ አግልግሎት ሰጥቷል።ሰርግና ማህበር በሚሆንበት ግዜ በጭፈራ፣ በማስተናገድ ዳቦ ሰብሮ በመሻማት ባሁሉን ተግባራዊ አድርጓል።ከዚህ በተጨማሪ በእግር ኳስ አስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በወቅቱ ይደረግ በነበረው ውድድሮች ቋሚ ተሳታፊና ጥሩም ውጤት አስመይግቧል።

ስዕል:ዘበኛ ሰፈር