አባል ውይይት:አስረኛው ሰው

Page contents not supported in other languages.
ከውክፔዲያ

ሰርቫይቫል

የሰውን ልጅ ህልውና ወደሚፈታተኑ ሁኔታዎች በተለያዩ ምክንያቶች ባልጠበቅነውና ባላሰብነው ሰዓት ልንገባ እንችላለን፤ ለምሳሌ በአውዳሚነታቸው የሚታወቁት ተፈጥሮ የምታስከትላቸው ጥፋቶች ማለትም መሬት መንቀጥቀጥ፣ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ፣ ሱናሚ፣ አውሎ ንፋስ፣ የመሬት መንሸራተት፣ ድርቅ፣ የተለያዩ የበሽታ ወረርሽኖች፣ በጎርፍ መጥለቅለቅ እና ሌሎችም ፍፁም ባላሰብነው እና ባልገመትነው ሰዓት ተከስተው፣ ቤትና ንብረታችንን አውድመው ሜዳ ላይ ሊያስቀሩን ይችላሉ፡፡ ጦርነት፣ የአካባቢ ብክለት፣ የእሳት አደጋዎች እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች በሰው ሰራሽ ጥፋቶች ውስጥ ሊከሰቱ ይችላሉ፤ በተጫማሪም በግጭቶች አማካኝነት ዓለም ወደ ባዮሎጂካል፣ ኬሚካልና ኒዩክለር ጦርነቶች ሊገባ ይችላል፡፡ ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎች ተጨማሪ ጥፋቶች ምክንያት ህልውናችን አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ለስደት፣ ለበሽታ፣ ለጉስቁልና፣ ለረሃብና ለሌሎች ጠንቆች ልንዳረግ እንችላለን፤ በርግጥ ሌሎች የተለያዩ ምክንያቶችንም መግለፅ ይቻላል፡፡ በመሆኑም መፅሃፉን ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት ራሳችንን ችግር ውስጥ እንደወደቀ አንድ አልሞት ባይ መመልከት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡


ሰርቫይቫል[ኮድ አርም]

[[1]]