Jump to content

አባል ውይይት:ክንፈሚካኤል

Page contents not supported in other languages.
ከውክፔዲያ

የሰማዕቱ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ወደ ነበረበት አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓመተ ምሕረት በታላቅ የሕዝብ አጀብ ተመልሷል።

[ኮድ አርም]

በፋሽስጥ ኢጣልያ በግፍ ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ከረፋዱ በ፭ ሰዓት ከ፲፭ ደቂቃ ላይ በ፲፩ ጥይጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ሰማዕትነት የተቀበሉት የሰማዕተ ጽድቅ የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት በግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ዘመነ መንግሥት በ፲፱፻፴፰ ዓመተ ምሕረት የተሠራ ሲሆን፤ በልማት ምክንያት ተነስቶ ከቆየበት ወደ ነበረበት አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓመተ ምሕረት በታላቅ የሕዝብ አጀብ ተመልሷል። በዕለቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴያስን ጨምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የሃይማኖት ተቋማት ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን አሰር በተባለ ተቋራጭ የተሠራው የሐውልቱ ማኖሪያ ላይ ሐውልቱ በታላቅ ክብር እንዲቀመጥ ተደርጓል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተለይም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች በስፍራው ከማለዳው ጀምረው የታደሙ ሲሆን በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት በቦታው ላይ ሲኖር ፤ ከረፋዱ ፭፣፲፭ ጀምሮ ሥነሥርዓቱ ጀምሮ ልዩ ልዩ መርኃ ግብሮች እና "ጴጥሮስ በዚያች ሰዓት" የተሰኘው የሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን መሳጭ ተውኔት በመነባንብ መልክ ቀርቧል። የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ፣ የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊዎችም ንግግር አድርገዋል። ሐውልቱ በ፳፻፭ ዓ.ም ለቀላል ባቡር መስመር ዝርጋታ ያለ ሕዝብ ይሁንታ የተነሣና በብሔራዊ ሙዚየም የተቀመጠ በመሆኑ ብዙውን ሕዝብ ያስደነገጠ እና ያስቆጣ ሲሆን አሁን ወደ ስፍራው በመመለሱ በርካቶችን አስደስቷል።

[ኮድ አርም]