አባል ውይይት:Gize mag

Page contents not supported in other languages.
ከውክፔዲያ

እጀ-መንገድ እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

ኮምጣጤ ቀማሾቹ

ጥንታዊ ቻይናዎች የኛ ታሪክ 10ሺ አመት ታሪክ ነው ይላሉ። የነሱ የ10ሺ አመት ታሪክ ከኛ ከ3ሺ መኩሪያችን ጋር ሲነፃፀር አቤት የኛ ማነሷ! እኛ ደግሞ በሉሲ ሚሊዮን ጊዜ እናስከነዳቸዋለን።

እያንዳንዱ የቻይና ገበሬ ቻይና ባትኖር የአለም ስልጣኔ ከጦርና ከፍላፃ አያልፍም ብሎ ያስባል። መድኃኒትን፣ የእርሻ መገልገያን፣ ሥነ-ፅሑፍን ፣ስነ-ሥዕልን፣ ፍልስፍናን፣ ወረቀት ፣ ህትመት ፣ባሩድ ፣ኮምፓስ ... ለአለም ያበረከትን እኛ ነን  ይላሉ። እውነትም እኒህ ቻይናዎች ብዙ ነገር ሰርተዋልና!  እሱን ለሌላ ጊዜ ላቆየውና  አሁን ወደ ኮምጣጤ ቀማሾቹ...

በቻይና ትላልቅ ከተማዎች በሚገኙ ጠባባብ መንገዶች ያሉት ሱቆች አንድ ስዕል ይሸጣሉ ወይንም ይሰቅሉታል። ማስተር ኮፒው ከቻይና ሀብቶች አንዱ ሆኖ በፔኪንግ ሙዚየም የሚገኝ ሀብት ሲሆን ቅጂዉን ግን ብዙ ሠዎች ሠርተዉታል። 

እንግዲህ እኔና እናንተ ወደዛ  ቻይና መንደር እንሂድ።ለቻይና እኛ ቱሪስት ልንሆን አንችልም። ቻይናውያን ምግብ ያልበላ ሠው ከቤቱ መውጣት የለበትም ይላሉ። እኛ ደግሞ ረሐባችን ፀሐይ የሞቀው ነው።ስለዚህ አንዱ ቻይናዊ ሱቅ ገብተን እንግሊዝኛ እናወራለን። እነቻንግን ጥቁር አሜሪካዊ እንምሰላቸው ይሄ ዉሸት አይደለም። ክርስቶስ ሳይወለድ በፊት የነበረ ቴክኒክ ነው። የእስራኤሉ ንጉስ ዳዊትም ይህችን ዘዴ ተጠቅሞባታል። ታዲያ እኛ ለቻይናዊ ጥቁር አሜሪካዊ ሆነን ብንቀርብ ዉሸት ነው?

አሁን አንዱ ስዕል መሸጫ ገብተናል አሉ።ከዚያ ሊን አገኘንና አንድ ታሪካዊ ስዕል ስጠን ስንለው ምን እንደሚሰጠን ገምቱ! ኮምጣጤ ቀማሾቹን። 

ስዕሉ ላይ ሦሥት ሠዎች ኮምጣጤ የያዘን ማሰሮ ከበው ቆመዋል። ሶስቱም በጣታቸው ኮምጣጤዉን ይቀምሳሉ። የያንዳንዳቸዉ ፊት የኮምጣጤዉን ጣዕም ያሳያል። እነዚህ ሰዎች ሶስቱ ታላላቅ የቻይና መምህራን ኩንግፉ(የኋላው ኮንፊሺየስ) አጎት ቡድሀና የታኦዪዝም መስራች ላኦድሱህ ናቸው።
የመጀመሪያው ተፋው። ሁለተኛው ፊቱን ኮሶ አስመሰለው። ሶስተኛው ከት ብሎ ሳቀ።ፊቱን ኮሶ ያስመሰለው አባት ኩንግፉ ምንጣፉ በትክክል ካልተነጠፈ መምህሩ መቀመጥ የለበትም የሚል ፍልስፍና ይዞ የነበረበትን ዓለም መቃወም ያዘ።ሁለተኛው ሰው አጎት ቡድሀ አለም መራራ ናትና ራቃት ብሎ ቢጫ ቀሚስ ለብሶ ብትውናዉን ተያያዘው።

ሶስተኛው ኮምጣጤ ቀማሽ ከት ብሎ የሳቀው ላኦድሱህ(ታኦ)የዚህን አለም መከራ ውስጧ እየኖሩ መተው ስለማይቻል በፈገግታ መቀበል የመረጠው ነው።

አሁን ደግሞ ከቻይና መንደር ወደ ሠፈራችን እንመለስና ከነዚህ ሶስት መምህራን የሚጠቅመንን የላኦድሱህን ጥበብ እንመርምር። እንደ አባት ኩንግፉ ከማይጥመን ሁሉ እየተጣላን መኖር አያዛልቅም።...... 

ዛሬ በስደት ባለንባቸው ሀገሮች ሁሉ ሀበሻ ወሬኛ፣ሀሜተኛ፣ ምቀኛ እያልን ከወገናችን ርቀን እንደ አጎት ቡድሀ አለም በቃኝ ብለን በአንድ ክፍል ውስጥ ቲቪ እያየን መዋልናማደር ያለብን አይመስለኝም።

ላንዳፍታ በምናብ ሀገር ቤት ሂዱና ያደግንበትን ማህረሰብ ቃኙልኝ። ሙቀጫ የገዛ ጎረቤቱ ባለው ዘነዘና ተማምኖ ዘነዘና ለመዋስ ጎረቤት መሄድ አያሳፍርም ። ስኳርም ሽሮም በርበሬም ቢጎድል ጎረቤት ከሚኬድበት ማህበር ተፈጥረን እዚህ ችግራችንን የምናካፍለው አለመኖሩ ስልጣኔ ነው?አዲስ አመትን በህብረት በችቦ ብርሀን የሚቀበል፣ዳመራን ተጠራርቶ ከሚለኩስ፣በሬን ቅርጫ አርጎ ከሚካፈል ህዝብ መሐል ወጥተን አመት በዓልን ቤት ዘግቶ የሚያስቀምጠን መሻሻል ይሆን?

ባለፈው እትም የኛው አኪለስ ሒል በሚል ርዕስ ስር ሕብረት ማጣታችን ትልቁ ድክመታችን እንደሆነ አንስቼ ነበር። ህብረት ያሳጣንም ወገናችንን መናቃችን፣ አጉል ባህሪዉን መጥላታችን ነው።

የወገናችን ነገር ስላልጣመን እንደ ቡድኀ ባሕታዊ መሆንን መረጥን።ግንኮ ሌላም አማራጭ አለ። እንደ ላኦድሱህ ኮምጣጤ ቀምሶ መሳቅ!!! የጠላነዉን ከማጥፋት ወደ መራቅ ተሻሽለናል። አሁንም እንሻሻልና ከማንወደው፣  ከማይጥመን ጋር የመስራትና የመጠቀም ብልሀትን እንማር።የወገናችንን ያልጣመንን ባሕሪ ስቀን አሳልፈን ጣፋጩን እናጣጥም።በዝቅተኛ ደሞዝ እድሜ ልክ ከመስራት እንደ ታኦ በኮምጣጤው እንሳቅና አብረን እንደግ። በተናጠል የማይቻል፤ በሕብረት መቻሉን እንመን።
አበው አክሱምን ያቆሙት በህብረት ነው።ላሊበላን ካንድ ቋጥኝ የፈለፈሉት በሕብረት ነው።አድዋ ላይ ድል ያደረጉት በሕብረት ነው።

ለመሆኑ አያቶቻችን ያን ሁሉ አብረው ሲሰሩ ሁሌም የሚተቃቀፉ ነበሩ? የአድዋ ዘማቾች ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው። የዐድዋ ጦር ዘማቾች ከክተቱ በፊት በስልጣን ሽኩቻ እርስ በርስ ሲዋጉ የነበሩ ናቸው። አድዋ ላይ ግን ጠላትን በሕብረት ድል አደረጉት። እኛም በሀበሻ ላይ የማንወደው ነገር ቢኖርም አብረን መስራት ግን መማር አለብን።

እንግዲህ የኮምጣጤ ቀማሾቹን ታሪክ ለትምህርት ለተግሳፅና ልብንም ለማቅናት ይጠቅም መስሎኝ ከቤንጃሚን ሆፍ መፅሐፍ ያገኘሁትን ተረኩላችሁ።

እጀ-መንገድ እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

የእንጦሮጦሱ ችሎት

ይህችን ተረት የነገሩን የጎንቸ ቤቴው የሀገር ሽማግሌ ዳሞ ናቸው።የጎንቸ ቤቴ የቸሀዎች መንደር ነው።ተረቲቱ በሰባት ቤት ጉራጊኛ ትነገር እንጂ እኛ በአማርኛ ነው የምንተርታት። ከመልዕክቷ ምጥቀትና ጥልቀት የተነሳ ፅንፈ-ዓለማዊ ይዘት እንዲኖራት መቸቷን ዘላለማዊና ዓለማቀፋዊ አደረግናት፤ እንጂ ተረቲቷ እንዲህ አልነበረችም። የዳሞ ተረት የሕዝብ ሀብት ናትና “ኮፒ ራይት” የለባትም።ስለዚህ ተረቲቷን ቀጣጥለን እንዲህ አራዝመናታል። እንደ ቅዱስ ፅሑፉ ትንቢት ሰይጣንና ጭፍሮቹ ከሚካኤልና ከሰማይ መላዕክት ጋር ተዋጉ።ታዲያ እነሰይጣን ተሸነፉና ከሰማይ ወደ ምድር ተጣሉ።(የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 12 ቁጥር 7-10)

ሰይጣን በእንጦሮጦስ ዘውዱን እንደጫነ ጳላንዛፌርን ጠራና ስለ ኢትዮጲያ አንድም ሳይቀር መረጃ እንዲያመጣለት ላከው። ጳላንዛፌርም በአንድ ሺኛ ካልኢት ተመልሶ መጥቶ ስለሉሲና የዓለም ሕዝብ ሁሉ ከኢትዮጲያ እንደተበተነ ነገረው። የሙሴ የቃልኪዳን ታቦት ኢትዮጲያ እንዳለ፣ ክርስቶስና ነቢዩ ሞሐመድ ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን፣ግማደ መስቀሉ ኢትዮጲያ እንዳለ ሲነግሩት የሰማይ ሽንፈቱን የሚወጣበት ቦታ በማግኘቱ ልቡ ጮቤ ዘለለች።  

እርኩሳን ወዳጆቹን ሰበሰበና ኢትዮጲያን ለማጥፋት ምን እናድርግ ብሎ ምክር ጠየቀ።በተንኮል የተጠበቡት እርኩሳን መላዕክቱ ዕኩይ ሀሳባቸውን አዥጎደጎዱት። ጳጢያሮቢንዳ የተባለው ተንከሲሱ ሽማግሌ ጋኔል “በመጀመሪያ ጥንካሬያቸው ምን እንደሆነ እንወቅ አለ። ሰይጣን ወደ ጳላንዛፌር ዘወር ሲል ታሪክ አዋቂው ጭራቅ ከመቅፅበት የሔሮዶቱስን “ዘ ሂትሪስ” መፅሐፍ ገልጦ ምዕራፍ ሦሥትን በአንድ ቅጭታ ፉት አላትና ኢትዮጲያውያኖች አያርሱም በፈንታው መሬታቸው ራሷ ቀን በቀን የተትረፈረፈ ምግብ ታቀርብላቸዋለች። ከመሬታቸው የሚፈልቀው ዉኃ እጅግ ልዩ ስለሆነ ከዓለም ካሉ ሰዎች በጠቅላላ ዕድሜ ረጅሞች ናቸው። መሬታቸው ዕጅግ ለም፣ ሰዎቻቸውም ድንቅና ማራኪ ዉበት ያላቸው ናቸው። እያለ ሲተነትን ሰይጣን አቋረጠውና ከዛሬ ጀምሮ ሐገሪቱ በበሽታና በረሐብ እንድትማቅቅ፣ የግዮን ወንዝም ለም አፈራቸውን ለባሪያዬ ለፈርዖን እንዲገብር የሚል ዉሳኔውን አሳለፈ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ የአባይ ወንዝ ለሙን አፈር እያጠበ ለግብጥ ይገብራል። ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አቃጣሪ ጭራቅ እያለከለከ ሰይጣን ችሎት ገብቶ ኢትዮጲያውያን አክሱም ላይ ክዋን (ኦብሊክ) አቆሙ ብሎ ተናገረ። ሰይጣንና ጭፍሮቹ ችሎቱን ትተው ወጥተው ሲመለከቱ ከአንድ ድንጋይ የተወቀሩ ብዙ ድንጋዮች ውደ ሰማይ ተቀስተው ቆመው ተመለከቱ። ሰይጣን ተናዶ ዳግም እንዲህ ያለ ነገር እንዳይሰሩና ስማቸው እንዳይገን ዕውቀት ንሷቸው ሲል አዘዘ። በጥልቁ ጨለማ(በእንጦሮጦስ አቆጣጠር)፣ሰይጣን በትረ-መንግሥቱን በያዘ በአምስተኛው ቀን የላሊበላ ቤተ-መቅደስ መታነፁን ነገሩት።ሰይጣን እመር ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ስልጣኔ እንዳይኖራቸው እውቀት ንፈጓቸው አላልኩምን? ብሎ ቢያንባርቅባቸው ሽሜው ጳጢያሮቢንዳ ዝግ ብሎ እነሱኮ በዕውቀት ሳይሆን በጥበብ(ዊዝደም) የተሞሉ ናቸው፤ ጥበባቸውን ካልነጠቅናቸው ልናቆማቸው አንችልም። ቢል ሰይጣን በትዝታ ተመስጦ እውቀታቸውን መውሰድ እችላለሁ ጥበብ ግን በተፈጥሮ ያገኙት ከፈጣሪ የተሰጣቸው ነውና የኔ ያልሆነውን ልወስድ አልችልም ብሎ የርኩሳን መናፍስትን አንጀት በሃዘን አንቦጫቦጨው። ሆኖም ሰይጣንና ምክር ቤቱ ኢትዮጲያን በዘር በሃይማኖት በጎሳ በቋንቋ በድንበር እንድትከፋፈል ተስማምተው ተለያዩ በዚህም የተነሳ የመሳፍን ዘመን ሰፍኖ እረስ በርስ ለ200 አመታት ተፋጀን የእንጦሮጦሱ ችሎትም አረፈ። ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወሬኛ ጋኔል ከኢትዮጲያ ውስጥ አንድ ቴዎድሮስ የተባለ ሰው ተነስቶ ኢትዮጲያን እንደጥንቱ አንድ ሊያደርግ ነው ቢሉት ሰይጣን በቸልተኝነት አንድ የእኛን ጦር ላክና ቴድሮስን አምጣልኝ ብሎ መከላከያ ሚኒስትሩን አዘዘው ሚኒስትሩም እንግሊዝን ላከ አንድ ቀን ስይጣንና መከላከያ ሚኒስትሩ የተንኮል ድር ሲያደሩ ድንገት ሰይጣን ለመከላከያ ሚኒስትሩ ያ ቴዎድሮስ የሚባለውን ሰውዬ ጠፍራችሁ ዐምጡልኝ አላልኩምን? ቢለው ሚኒስትሩ ሲፈራ ሲቸር እሱማኮ ከነፍሱ ኩራቱ በልጦበት እጄን አልሰጥም ብሎ ሞተ ቢለው ሰይጣንን አብዝቶ ገረመው እኚህ አበሾች እንዴት ያሉ ሞገደኞች ናቸው ?ሲል ተናገረ ይህን እያወሩ ሳለ ለሰይጣን የሳተላይት ጥሪ ደረሰው ሚኒሊክ የሚባል ሰው ትነስቶ ኢትዮጲያ አንድ አደረገ ሲሉት ፈረሴን ጫኑለኝ አለና አንድ የጣልያን ጋኔል ላይ ተቀምጦ ወደ ኢትዮጲያ ጋለበና አድዋ ላይ ጦሩን አከማችቶ ቁጭ አድዋ ዘምቶ ጭራውን እግሮቹ ስር ቆልፎ አይዋረዱ ውርደት ተዋርዶ ወደ እንጦሮጦሱ ሲመለስ ጳጢያሮቢንዳ ዬንጦሮጦሱ ችሎት የአንጋፋው እርኩስ መንፈስ ሃሳብ ለማዳመጥ ተገዶ ሽሜው እንዲህ ነበር ያሉት እናንተ ሰይጣኖች ለመሆኑ የአበሻ ሚስጥር አይገባችሁምን ሀበሻ ሀገሩን በጣም ያፈቅራል ድሃ ሆነ ሃብታም ለሃገሩ ያለው ፍቅር ከሚስቱ ይበልጣል እርጉዝ ሚስቱን ከቤት ብቻዋን ትቶ አድዋ እንደዘመተ አላያችሁምን ?እና ለሃገሩ ሊሞት የቆረጠ ሰው ተዋግታችሁ ልታሸንፉ ይቻላችሗልን ?ሲሉ ሰይጣን ጣልቃ ገባና ፍቅር ከፈጣሪው ነው የተሰጠው እና የሃገሩን ፍቅር ልንወስድበት አንችልም የተሻለው ሃሳብህ ምንድን ነው ሲለው ሸበቶው ሰይጣን ህብረትን እንከልክላቸው ጥንካሬአቸው ህብረታቸው ነው ሲል ተፈሪ መኮንን የሚባል ንጉስ አፍሪካን አንድ ሊያደርግ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አቋቋመ የሚል ዜና ሲመጣ ጭፍሮቹን ምን እናድርግ ቢላቸው ሁሉም ባንድ ድምጽ ህብረት እንንሳቸው አሉ እነሆ የዕንጦሮጦሱ ችሎት ኢትዮጲያውያንን ህብረት ነሳቸው። የመጀመሪያው ብስራት ያመጣው ሾካካ ጭራቅ ኢትዮጲያዊያን እነ ገርማሜ ነዋይን አስሮ ሰጠ።ቀጠለ የኢትዮጲያ ህዝብ በላይ ዘለቀን ቆሞ አሰቀለ። ተብሎ ሲነገረው ከሰማይ ከተባረረ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ አለ ከዛማ የምስራች መከታተል ያዘ።ጓደኛ ጓደኛውን አጋልጦ አስገደለ፣ጎረቤት የጎረቤቱን ልጅ አሳልፎ ሰጠ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን አቀለላት፣ ሀገሩን ናቀ።

    ጳጢያሮቢንዳ ኢትዮጲያዊያንን ህብረት እንከልክላቸው በሚለው የጦር ስልቱ ለማሸነፍ በመቻሉ በእንጦሮጦስ ዘላለማዊ የጀግና ሃውልት ቆመለት     
  ከዛን ጊዜ በሁዋላ በፊት ሆኖ የማያውቀው ስደት በጣም በዛ እነሆ እድሜ ለጳጢያሮቢንዳ ኢትዮጲያዊያን በተሰደዱበት ሀገርንኳ መተባበር አቅቷቸው የመጨረሻ ዝቅተኛ ኑሮ መኖር ጀመሩ ኑሮአቸውም ሳህን በማጠብ ቡና በማፍላት መንገድ በመጥረግ መኪና በመጠበቅ መምራት ጀመሩ የእንጦሮጦሱም ችሎት ኢትዮጵያውያንን ሕብረት በማሳጣት ድሉን ተጎናፅፎ በኢትዮጲያውያን ላይ የከፈተውን ፋይል ዘጋ።

ይህችን ታሪክ የተረክንላችሁ እኔና የጎንቸ ቤቴው ዳሞ ነን።

እጀ-መንገድ እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ። ገብረ-ጉንዳን ጉንዳን 52 ሚ.ሜ ናት። እቺ ጥንጥዬ ነገር በምድር ላይ መታየት ከጀመረች 110 ሚሊዮን ዓመት ይጠጋታል።አበቦች መፈጠር ከጀመሩ ወዲህ ከ12000 በላይ የጉንዳን ዝርያዎችም አብረው ተፈጥረዋል።እኒህ ጉንዳኖች ከአንተርክቲካ በቀር በምድር ዙሪያ የሌሉበት ቦታ የለም።ጉንዳን ልቧ ቂጧ ላይ (አብዶሜን)ነው።ለነገሩ እሷ ልብ ትበለው እንጂ የሕብለ-ሰረሰርዋን (Spinal cord) ጫፍ ነው እንደ ልብ የምትገለገልበት።ጉንዳን ጥንጥ ትሁን እንጂ የክብደቷን ሃምሳ እጥፍ ትሸከማለች። ይሁንና በጉልበቷ ተማምና ብቻዋን ከመኖር ከሌሎች ጉንዳኖች ጋር በአንድ መንጋ እስከ ሚሊዮን ሆነው በሕብረት የመኖርን ጥበብ ተክናዋለች።አብረው በመኖራቸው በምድረገፅ ከሚኖሩ ፍጥረታት ጠንካራ ግዛት(Colony) ካላቸው የመጀመሪያዋ ለመሆን ችላለች። እንግዲህ ይህችን ጉንዳን እንዳስብ ያደረገኝ The Ant bully የሚለው Animation ፊልም ነው።የገብረ-ጉንዳን ታሪክ በThe Ant bully ፊልም በጁሊያ ሮበርትስና በኒኮላስ ኬጅ ድምፅ እየተተረከ ጉንዳኖቹ ይናገሩን ጀመር።ታሪኩ አንድ ሉቃስ የተባለ ትንሽ ልጅ የጉንዳን ቤት እያፈረሰ ጉንዳኖችን ያስቸግራል።አትክልት አጠጣ ሲባል የጉንዳኖችን መኖሪያ በጎርፍ ያጥለቀልቃል። በሉቃስ እኩይ ባሕርይ የተቸገሩት ጉንዳኖች ችሎት ተሰይመው ሉቃስን የሚያጠፉበት ዘዴ ሲቀይሱ አንድ ጠቢብ ጉንዳን መላ ይፈጥርና ሉቃስን ጉንዳን ያሳክለዋል።ሉቃስ ጉንዳን አክሎ ችሎት ሲቀርብ ንግስቲቷ ሉቃስ እንዲሆን ፈርዳበት እንደ ጉንዳን መኖር ይጀምራል።ጉንዳኖች በሉቃስ አስመስለው በ The Ant bully ጉንዳንነትን አሳዩን። ከጉንዳኖቹ ነፍሴን የነካቻት ቃለ-ተውኔት እነሁዋት።ሉቃስና ጠቢቡ ጉንዳን በጠፍ ጨረቃ ለጥ ኮረት ድንጋይ ላይ ተኝተው ያወራሉ።ጠቢቡ ወደ ሰው ልጆች መኖሪያ እየተመለከት ጠቢቡ ጉንዳን፡ ”እዛ የሚኖሩት የሰው ልጆች ሁሉ ለሰው ልጅ ሉዓላዊነት በህብረት ትሰራላችሁ አይደል?” ሉቃስ፡ “እንደዛ ሳይሆን ሁሉም ለራሱ በግሉ ነው የሚሮጠው” ጠቢቡ ጉንዳን፡ “ያማ በጣም ሁዋላ ቀርነት ነው።አንድ ሰው፣እንዴት ብቻውን ሁሉን ሰርቶ ሊጨርስ ይችላል?” ሉቃስ፡ “አንዳንድ አብረው የሚሰሩ ሰዎች አሉ።” ጠቢቡ ጉንዳን፡ ”ለምን ሁሉም አብረው አይሰሩም?” ሉቃስ፡ “ብዙ ልዩነት ስላላቸው መሰለኝ” ጠቢቡ ጉንዳን፡ “ልዩነት ነው አንድን ማህበረሰብ ጠንካራ የሚያደርገው፤ ለምሳሌ በኛ ውስጥ ሁላችንም የተለያየን ነን።ግን ሁሉም አስፈላጊያችን ናቸው።ጥንካሬያችንም ያለው ሕብረታችን ላይ ነው::” ሉቃስ፡ “እኛጋ ግን እንዲህ አይደለም፤ ለምን እንደሆነ እንጃ ብቻ ዝም ብለን እርስ በእርስ እንጠላለፋለን።” ጠቢቡ ጉንዳን፡ (በቁዘማ)”እኔም አንዳንዴ እንደሰው ልጅ የማደርገውን አላቅም።”(ፊልሙ ላይ ጓደኛ ሳይሆኑ በፊት ሉቃስን ሊያጠፋ ይፈልግ ነበር) “I am small, we all are small but together we are big” Lucas ከThe Ant bully የተወሰደ በተናጠል ደካሞች ነን። በህብረት ግን ጠንካሮች ነን።

እጀ መንገድ

እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

የማይመች እውነት Jessica፣ ስራ ቦታ ጣፋጭ ታሪክ የምታስወራን ናት። እኔ፣ የካሲዮፒያንና የአንድሮ ሜዳን ታሪክ አወራሁ። ኤድሪያን፣ አባቱ ስራ ሳይሔድ ቤት ከሱጋ እንዲጫወት ሲል አባቱን በሰዓት 20 ዶላር ሊቀጥር ስለፈለገው የ5 ዓመት ሕፃን ታሪክ ነገረን።Jessica፣ራሷ የክርስቶስ ሰምራን አይነት ታሪክ በእንግሊዝኛ ነገረችን። ራሺያዊቷ Monika ስለማይጨልመው የሌሊንግራድ(ፒትስበርግ) ሌሊት አወራች።ሕንዳዊቷ መነኩሴ Tess፣ የሚቀጥለውን ታሪክ ተረከችልን። “ከዕለታት አንድ ቀን በአሜሪካ የሚኖር አንድ አሜሪካዊ ሳይንቲስት ነበረ፣ ይህ ሳይንቲስት ከልጅነቱ ጀምሮ በፈጣሪ አያምንም ነበር። አንድ ጊዜ ከአሜሪካ ለዕረፍትና ለጉብኝት ወደ ሕንድ ሔዶ 8 ወር ቆይቶ ሲመለስ ቤተ ክርስቲያን አዘውታሪና ፀሎተኛ ሆነ። ማንነቱን የሚያውቁት ተገርመው እንዴት በፈጣሪ ለማመን እንደበቃ ሲጠይቁት እንዲህ ብሎ መለሰ።

‘ሕንድን ከላይ እስከታች አየሁዋት።የሀገሬው ሕዝብ ሁሉ የሚያውቀው አንድ ቋንቋ የለም፤ ሒንዱዎችና ሲኮች አይዋደዱም፣ ሙስሊሞችና ሒንዱዎች ጠላት ናቸው፣ሀብታሞቹ መለስተኛ ሀብታሞቹን አይወዷቸውም፤የከተሜው ለማኝ እንኳን ፣የገጠሩን ለማኝ አይወደውም፤ ሕዝቡ እርስ በርሱ ምቀኛ ነው። አንዱ አንዱን አሳልፎ መስጠት ባሕል ነው፣ ባለ መኪናው ባለ ሶስት ጎማ ታክሲዎችን አይወድም፡ ሀገሪቱ በጥላቻ የተሞላች ናት። አስገራሚው ነገር ሀገሪቷ አልፈረሰችም፣ እንዲያውም እያደገች ነው።እስቲ ንገሩኝ ፈጣሪ ባይኖር ኖሮ እቺ ሀገር በጥላቻ በምቀኝነት፣ ብቻ አትፈርስም ነበር ወይ?’ አላቸው ይባላል።”    

የኔዋን ሀገር አሰብኳት። ሙስሊምና ክርስቲያን ተፋቅረው የሚኖሩባትን ወሎን፣ አንዋር መስኪድንና ራጉኤል ቤ/ክርስትያንን አጠገብ ለአጠገብ የያዘችን መርካቶን፣ የመስቀል ደመራ ለመለኮስና አረፋ(ኢድ አልድሐ)ን ለማክበር የጉራጌ ልጆች የሚሔዱባት ቡታጅራንም አሰብኳቸው። ይህም ሆኖ በዓለም ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ ድሆች ነን። ሀብታም ሀገሮች ገብተንም የመጨረሻ ደሀና ዝቅተኛ ኑሮ ነው የምንኖረው።በቶሮንቶ በአንድ ፋብሪካ ብቻ 800 ኢትዮጵያውያን የጉልበት ሥራ ይሰራሉ።በአንድ ሆቴል ውስጥ ብቻ 50 ኢትዮጵያውያን በዝቅተኛ ሥራ መስክ ለረጅም ዓመታት ሰርተዋል።ከDundas በታችና በJarvis ና በSpadina መካከል 30 Tim Horton’s Cafe ሲኖር 21ዱ ኢትዮጵያዊያውያን ይሰሩባቸዋል።የቶሮንቶው Imperial Parking ውስጥ ከሚሰሩት 201 ሰራተኞች ውስጥ 89ኙ ኢትዮጵያውያን ናቸው።በቶሮንቶ ከሚገኙ 1400 Becks ታክሲዎች ውስጥ 507 ኢትዮጵያውያን የBecks ታክሲን እንደሚነዱ መረጃ አግኝተናል። ኮንስትራክሽንና ፅዳት የሚሰሩትን መገመት የሚችልንኳ ጠፋ። እስከ ሀምሳ ሺህ ኢትዮጵያውያን ይኖረባታል ከምትባለው ቶሮንቶ 90 በመቶው በተመሳሳይ ስራ እንደተሰማሩ ይታመናል። ከስልጣኔ አውራነት እንዴት የዓለም ጭራ ሆንን? አባቶቻችን አክሱምን ሲቀርፁ፣ ላሊበላን ሲያንፁ፣አድዋ ላይ ሲመክቱ፣ፋሺስትን ሲረቱ፤ጥንካሬአቸው ሕብረታቸው ነበር። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ብለው የደካሞች ሕብረት ጠንካራውን እንደሚያሸንፈው መንገራቸው ነበር። እውነታውን መካድና፣ እንደለመድነው ከሌላው እንሻላለን ብለን እራሳችንን እያታለልን በባዶ ሜዳ መደገግ እንችላለን። እውነታውን አምኖ መፍትሔ መፈለግ ግን ብልህነት ነው። ካለንበት የድህነት ማጥ ለመውጣት ብቸኛው አማራጭ ሕብረት ነው።ሌላ መፍትሔ የለም። ሌላ መፍትሔ ያለው ካለ ይንገረን።

እጀ መንገድ

እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

ጓጉንቸሮቹ

እቺ ተረት ከጋሽ ስብሐት የተገለበጠች ናት።ጋሽ ስብሐት በግጥም ፃፋት፣ እኔ በስድ ንባብ አስቀመጥኳት።ጋሽ ስብሐት ግጥሚቱን ከየት እንዳመጣት አላውቅም፤ ብቻ አንድ ቀን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለጥፏት ለኔ ተነበበች። በዘመን ርቀት ትርክቷን እንዳለ ለማስቀመጥ ባይቻለኝም፣ ቁምነገሯ ግን ኩላሊት ላይ ተጥፏል።ተረቲቷ እቻትላችሁ። “በአንድ ኩሬ፣ በፈንጠዝያና በደስታ የሚኖሩ ሁለት ጓጉንቸሮች ነበሩ።ከመጨፈርና ከመደነስ በቀር ምንም ችግር ገጥሟቸው የማያውቁ እኒህ ጓጉንቸሮች፤አንድ ምሽት ላይ ያልታሰበ ሁካታና ጫጫታ ይሰማሉ፤ሁካታው ምሽቱን ባደመቀ ብርሀን የታጀበ ነበርና በሁናቴው የተደናገጡትና ግራ የገባቸው ጓጉንቸሮች ከውሀው ወለል ላይ ተለጥፈው የሚሆነውን ሲጠብቁ፣ ጫጫታው እየበረታ፣ ወገግታው እየደመቀ፣ሲመጣ ከውሀው ብቅ ብለው ሲመለከቱ፣ከመንገዱ ማዶ ቤት ተቃጥሎ ሰዎች እሳቱን ሊያጠፉ ሲሯሯጡ ተመለከቱ።እሳቱ ያለው ከመንገዱ ባሻገር፣ በዚህ ላይ እኛ ውኃ ውስጥ ነን ምንም አንሆንም ብለው ኩሬው አናት ላይ ሲፈነጥዙ፣ ሰዎቹ እሳቱን ለማጥፋት ከኩሬው በባልዲ ሲጠልቁ ጓጉንቸሮቹንም ጨልፈው የሚነደው እሳት ውስጥ ጨመሯቸው።” ጋሽ ስብሐት እቺን ተረት ለምን እንደፃፋት እንጃ እኔ ግን ለሆነ ነገር ጠቀመችኝ። ቢሆንልን ሁላችንም ማደግ እንፈልጋለን፣ወይ በትምህርታችን በርትተን የተሻለ ደረጃ ለመድረስ፣ወይ ደግሞ የምናገኛትን አጠራቅመን አገር ቤት ገብተን ኢንቨስት በማድረግ፣ቤት ገዝተንም፣ብቻ በየራሳችን መንገድ ለማደግ እናስባለን።በምንኖርባት ከተማ በቶሮንቶ ኢትዮጵያውያን ለማደግ ሲፍጨረጨሩ እናያለን።ተሳክቶላቸው የከበሩ በዙም ባይሆኑ የሚታገሉትን ግን እያየን ነው። ይህንን ፅሑፍ በምንፅፍበት ሰዓት፣152 በግል ሥራ የሚተዳደሩ እንዳሉ ቆጠርን።ይህም ማለት፣ሬስቶራንቶች፣የሸቀጥ መደብሮች፣ትራቭል ኤጀንሲዎች፣ ሕትመትና ዲዛይነሮች፣ፀጉር ቤቶች፣እንጀራ አቅራቢዎች፣የመX-masኛ ብዙሀን አገልግሎቶች፣የሕክምና መስጫዎች፣የሐዋላ አገልግሎት፣የቴክኒክ ሞያተኞች፣የፎቶግራፍና የቪዲዮ ቀረፃዎች፣የኮምፒውተር ጠጋኞች፣የሙቪንግ ትራክስ ሾፌሮች፣የቤት ጥX-masና ዕድሳት ሞያተኞች፣ድምፃውያንና የሙዚቃ መሳሪያ ሙያተኞች፣.... የእነዚህ እንቅስቃሴዎች በከተማችን መኖር፣በኮሙኒቲ ደረጃ ማደጋችንን የምናይባቸው መንገዶች ናቸው።እነዚህ ድርጅቶች የሚያድጉት ደግሞ እኛ ስንጠቀምባቸው ነው።ለዚህም ነው ሰሞኑን በየአውቶቡስ መጠለያው “support your neighbourhood business” የሚል የኮሙኒቲ ማስታወቂያ የሚታየው ላለፉት 10 ዓመታት 41 የንግድ ድርጀቶች ተዘግተዋል።ለምን እንደተዘጉ ለማወቅ ምሑር ቃለ መጠይቅ ማድረግ አያስፈልገንም። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለነዛ ድርጅቶች መዘጋት አስተዋፆ አርX-masል።አንድ በቅርቡ የተዘጋ ድርጅት ባለቤትን አነጋግረን “... ድርጅቱን በመክፈቴ ተፀፅቻለሁ።እኛ ማኅበረሰብ ውስጥ ማእግ ይቻልም ሲል ተደምጧል። አንድ የመX-masኛ ሚዲያ ከፍቶ የነበረ ኢትዮጲያዊ ከሁለት ዓመታት ግልጋሎት በኋላ ከመዝጋቱ በፊት “አግዙኝ! ብሎ ስብሰባ ጠርቶ የተገኙለት 6 ሰዎች ብቻ ሲሆኑ ከ15 000 ዶላር ኪሳራ ጋር የዜና አውታሩን ሲዘጋ ለሁለት ዓመታት ለሰጠን አገልግሎትንኳ ዕውቅና አልሰጠነውም።” የንግድ እንቅስቃሴ መኖር ሁላችንንም ይጠቅማል።ወጣም ወረደም መX-masኛዎቻችንና አX-masኚዎቻችን ናቸው።አላቂ ዕቃዎችን ያቀርቡልናል።በሥራ የተወጠረ አ ዕምሮአችንን ዘና የሚያረጉልን የመዝናኛ ዝግጀት የሚያዘጋጁልን ናቸው። መረዳዳት ባስፈለገን ጊዜ በመጀመሪያ ለዕርዳታ ዕጃችንን የምንዘረጋው ወደነሱ ነው። አንዳንድ ሬስቶራንቶች፣ በዓመት እስከ 10 000 ዶላር ለኮሙኒቲው ያወጣሉ።(የኮሙኒቲ እንቅስቃሴዎችን ስፖንሰር በማድረግ፣ቀጥተኛ የገንዘብ ልገሳ፣...)፣ ዝግጅቶች፣ወይንም ማስታወቂያዎች ሲኖሩ ፖስተሮች የሚለጥፉትና፣ የመረጃ መቀባበያዎቻችን እነዚሁ ድርጅቶች ናቸው። አንድ ሬጀንት ፓርክ ሠፈር የሚታተም የአካባቢ ጋዜጣ ላይ “support your neighbourhood business”የሚል ፅሑፍ ሳነብ፣ የኮሙኒቲ ንግድ ድርጅቶችን መደገፍ የምንችልባቸውን መንገዶች ሲናገር፣ ከሰው ጋር ቀጠሮ ሲኖረን ወደ ሠፈራችሁ አምጡት፤ አንደኛ እንጋችሁ ሰፈራችሁን ለማወቅ ጥሩ አጋጣሚ ይሆነዋል፣ሁለተኛ፤ የሰፈራችሁ ንግድ ድርጅት ገቢ ያገኛል። መሥሪያ ቤታችሁ አነስተኛ ፓርቲ( የልደት፣ወይንም የሽኝት ግብዣ) ሲኖር፣የሰፈራችሁን ሬስቶራንት አድራሻ ስጡ.... ከሬስቶራንቱ ባለቤትጋ ተነጋግራችሁ የግሩፕ ቅናሽ አስደርጋችሁ መስሪያቤታችሁን አግባቡ። የሠፈራችሁ ሬስቶራንት በምግቡ ጥራት፣ ወይንም በቤቱ ንፅሕና ችግር ካለበት ወጥታችሁ ለጓደኞቻችሁ ከመናገር ለሬስቶራንቱ ባለቤት ንገሩት። ጠንካራ ሠፈር የጠንካራ ጎረቤቶች ውጤት ነው “The great neighbourhood is made up of great neighbours”

አንድ ንግድ ድርጅት ሲዘጋ እኛን አይመለከትም ብለን ነው የምናስበው? እንደዛ ከሆነ ተረቷን ልድገማት። “... በአንድ ኩሬ፣ በፈንጠዝያና በደስታ የሚኖሩ ሁለት ጓጉንቸሮች ነበሩ ...”

1. እጀመንገድ

ዓድዋን በአቫታር

March1, 2010 አቫታርን ለማየት በአይማክስ ስቱዲዮ ተቀምጠን ፊልሙ ጀመረ። የሰው ልጆች ከኢንዱስትሪና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አብዮት በኋላ በ2154 ዓ.ም. እጅግ ኃይለኛና በቴክኖሎጂ የመጠቀ ደረጃ ላይ ደርሰው ፅንፈ አለምን ሲቀራመቱ፣ በአልፋ ሴንቹዋሪ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሀብት፣ በባለቤትነት የያዘው R. D. A. የተባለው ኮርፖሬሽን unobtanium የተባለ ንጥረ ነገር ፍለጋ፣ ከምድር 4.37 የብርሀን ዓመት ርቃ ወደ ምትገኘው አልፋ ሴንቹዋሪ ተጓዘ። በአንድ ኪሎ unobtanium፣ ሀያ ሚሊዮን ዶላር ለማፈስ የቋመጠው R. D. A. ኮርፖሬሽን ፓንዶራ ሲደርስ ችግር ገጠመው። ይህች በአልፋ ሴንቹዋሪ ሥርዐተ ፀሐይ(solar system) የምትገኝ ምድር መሰል ጨረቃ፣ በተፈጥሮ ጥበብና በአካል ብቃት የተካኑ ሰማያዊ የቆዳ ቀለም ያላቸው Na'vi የተባሉ 2ሜትር ከሰባ ሳንቲ ሜትር በላይ የሚረዝሙ ሰው መሰል ፍጡራን መኖሪያ ናት። ኢኒህ ናቪዎች፣ በቴክኖሎጂ የበለፀገ ጦር ሠራዊት በጦርና በፍላፃ ገትረው ያዙ። አርዲኤ የ Na'vi ዎች አይበገሬነት ተልዕኮውን ስለገታው የፓንዶራን ነዋሪዎች ለመሰለል በነዛ የፓንዶራ ፍጡራን ላይ ሰዎችን በናቪዎች አምሳልና አካል የሚያሳድግ አቫታር የተባለ ጥናት የሚያደርግ የሳይንስ ማዕከልን ስፖንሰር አድርጎ የጥናቱን ውጤት ለመካፈል ይስማማል። ማዕከሉ፤ በናቪዎችና በፓንዶራ ፍቅር የተጠመዱ ባለሙያዎችን ያቀፈ ቢሆንም የ Na'vi ዎችን ሚስጢር አስልፎ ለመስጠት ይገደዳል። ኮርፖሬሽኑ ከሰው ልጆች በግዝፍና በሁለት ዕጥፍ የሚበልጡት Omaticaya የተባሉት በሺህ የሚቆጠሩ ነገዶች ይሚኖሩበት የነበረውን እጅግ ግዙፍ የሆነውን የዛፍ ለመገንደስ በ Colonel Quaritch የሚመራው Sec-Ops ጦር ከነመኖሪያ ዛፋቸው ለማጥፋት ሠራዊቱን ይልካል።Omaticayaን በጦርና በፍላፃ የጦር ጀቶችን ይገጥማሉ። ጦርነቱ ምንም የተመጣጠነ አሰላለፍ አልነበረውም።ሆኖም በፓንዶራ የሚኖሩ ጎሳዎች ተጠራርተው፣ የፓንዶራ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥም ረድቷቸው፤ ምድርን አውድመው ፓንዶራንም ሊያወድሙ የመጡትን በፓንዶራ ድል ነሷቸው።ፊልሙ ተጠናቀቀ።የተዋንያኑ ስም መፃፍ ሲጀምር አይኔን ጨፍኜ ማ ማንን ሆኖ እንደሚጫወት ማሰብ ጀመርኩ።

RDA እንደ ፋሺስት ኢጣሊያ;

AVATAR እንደ ሚሽነሪዎች; 

Colonel Quaritch እንደ ጄኔራል አልበርቶኒ Na’vi እንደ አርበኞች;

ፓንዶራ እንደ አድዋ

Neytiri እንደ ጣይቱ ብጡል;

እርግጥ ነው ፊልሙ ላይ ሚኒሊክን ሆኖ የተጫወተው አንድ አሜሪካዊ ነው።የኛም ታሪክ በነሱ ሲፃፍ ስታሮቹ እነሱ ናቸው።እኛ ግን ምናችን ሞኝ ነው? ሳንሱር እያደረግን ፊልሙን እናያለን። The same Quotes from Adwa and Avatar “We will engage the Ethiopians in piecemeal battles” General Oreste Baraterie march 1, 1896 “ ... this mission is not high and tight. I want be home for dinner” Colonel Quaritch The head of Sec-Ops in Avatar “They are not humans, flying beaten savages that living on tree.” RDA Administrator Parker Selfridge in Avatar “... They (Ethiopians) need to learn civilization, they are savages.” brigadier Matteo Albertone. February 1896

የፓንዶራ Na'vi ዎች ፍልስፍናቸው አንድነት፣ውህደት፣ጥምረት ነው።ከተፈጥሮ ጋር መዋሐድ፣ ከወገኖቻቸው ጋር መጣመር፣ በአላማ አንድ መሆን... በአድዋ ደግሞ ሕብረትና ፍቅር፣... አቫታር ለቶሮንቶ ኢትዮጵያውያን ለትምህርት፣ለተግሳጽ፣ልብን ለማቅናትና ለሕብረት ይጠቅማቸው ዘንድ ያየነውን ጣፍ አረግናት።

እጀ መንገድ

ፅንፈ-ዓለማዊው ቋንቋ

      የፅንፈ-አለም ግዝፈቱን ለመረዳት ከመሬት እንጀምር።መሬታችን በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ናት።በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከመሬት ሌላ ስምንቱ ፕላኔቶች (ዘጠነኛዋ ፕላኔት ፑሉቶ አርጅታ በ2006 ሞታለች) ጨረቃዎች፣ ኮሜቶች፣ ሜትዮራቶች፣ ፀሐይ ራሷና ሌሎችም ይገኛሉ።እንግዲህ ፀሐይ አንድ ኮከብ ናት።የኛ ፀሐይ የምትገኝበት ጋላክሲ(የክዋክብት ረጨት)፣እንደ ፀሐይ ያሉ የራሳቸው ሶላር ሲስተም ያላቸው ቢሊዮን ክዋክብት አሉ።የኛ ሶላር ሲስተም (ሥርዐተ ፀሐይ) የምትገኝበት የክዋክብት ረጨት ወተታማ መንገድ(ሚልክ ዌይ) በመባል ይታወቃል እንደኛ አይነት ቢሊዮን ክዋክብትን የያዙ ቢሊዮን ጊዜ ቢሊዮን ጋላክሲዎች አሉ።እነዚህ ሁሉ በፅንፈ አለማችን ውስጥ አሉ።
      አሁን ደሞ እጅግ ግዙፍ ከሆነው ከፅንፈ ዓለማችን እጅግ አነስተኛና ደቃቅ የሆነውን አተም እንመልከት። አተም  ἄτομος/átomos, ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን α-τεμνω, ትርጓሜውም የማይቆረጥ፣ ሊከፈል የማይቻል የመጨረሻ ተካፋይ ማለት ነው። አተም፣ የመጨረሻው ደቃቅም ሆኖ አንድ ነጠላ አተም የሁለት ክፍሎች ውሑድ ወይንም ሕብር ነው።ኑክሊየስና አውተር ሼልስ።ኒኩሊየስ ፕሮቶንስንና ኒውትሮንስን ይይዛል።አንዱን አተም ለሁለት ብንቆርጠውንኳ የራሱ ኒኩሊየስና አውተር ሼልስ ይኖሩታል እንጂ በነጠላ አይቆይም።አስገራሚው ነገር ኤሌክትሮንስ ኒኩሊየስን፣ጨረቃ መሬትን፣መሬት ፀሐይን፣ ፀሐይ ጋላክስዋን፣ ጋላክሲዎች ከሌሎች ጋላክሢዎች ጋር ፅንፈ አለምን፤ በሕብረት ይዞራሉ።

ሕብረት ፅንፈ አለማዊ እንቅስቃሴ ነው። ብቻውን የሚንቀሳቀስ ነገር የለም።ደራሲው ፓውሎስ ምን ይላል? መጀመሪያ ፓውሎን እንወቀው።በትውልድ ብራዚላዊ፣በእምነት ካቶሊካዊ፣ መፅሐፎቹ አለማቀፋዊ፣ አመለካከቱ ፅንፈ-ዓለማዊ ነው።ዘ-አልኬሚስት የሚለው መፅሐፉ 30 ሚሊዮን ቅጂ የተሸጠ ሲሆን፤ በ67 ቋንቋዎችም ተተርጉሟል።አሁን ደግሞ የዘ-አልኬሚስት ደራሲን ፓውሎ ኩዌሊዮን እናመስግንና ፅንፈአለማዊውን ቋንቋ እናጥና።

      ፓውሎ “ዘ-አልኬሚስት” በሚለው መፅሐፉ የቀረፀው ሳንቲያጎ የተባለ በጎቹን የሚያፈቅር የስፓኝ እረኛ፤ አንዲት በደቡባዊ ስፓኝ የምትገኝ፣ አንዳልዱጉ በምትባል የገጠር ምድረበዳ በጎቹን ሲጠብቅ፣ ግብፅ ፒራሚድ ስር ቢቆፍር ሀብት እንደሚያገኝ በሕልሙ ይታየዋል።ይህ በዓመት አንዴ በጎቹን እየሸለተ የሚሸጥ እረኛ፣የበጎቹን ፀጉር ከሚገዛው ነጋዴ ሴት ልጅ በፍቅር ቢሆነልልም፣ የሚወዳቸውን በጎቹንና የነጋዴውን ሴት ልጅ ትቶ ፣ የሜዲትራኒያንን ባሕር አቋርጦ አፍሪካ ሲገባ ያልጠበቀው ነገር ይገጥመዋል። አፍሪካውያኖቹ አረቢኛ እንጂ የእስፓኝ፡ቋንቋ አይናገሩም። 
           አስገራሚው ነገር ሳንቲያጎ ከአንድ አረባዊ ቋሊማ ነጋዴ ጋር ሳይነጋገሩ ተግባብተው ለቋሊማ ነጋዴው ተቀጥሮ ሙሉቀን ሰርቶለት፣ ደሞዙን ቋሊማ ተቀብሎ ሄደ። ወደ ካይሮ የሚወስደውን የስሀራን በርሀ ሲያቋርጥ  አንድ ከፅንፈ ዓለም እየጠፋ ያለውን ፅንፈ-ዓለማዊውን ቋንቋ ከአልኬሚስቶች ለመማር ወደ ካይሮ የሚሄድ አንድ እንግሊዛዊ ፕሮፌሰር ያገኛል። ካይሮ ከመድረሳቸው በፊት በሰሀራ በረሐ በሚገኘው ለምለም ቦታ (oasis of the sahara) አልኬሚስቱ ሳንቲያጎን ፈልጎ መጣ። እኒህ ብረትን ወደ ወርቅነት መቀየር ይችላሉ እየተባለ የሚነገርላቸው ጠቢቦች፤ ከፈላስፎችና ከምሁራን አንድ እረኛን መረጡ። አልኬሚስቱና ሳንቲያጎ በመንገድ ላይ በጎሳ ጦረኞች ተማርከው ከሞት የሚያስጥላቸው ነፋስ ብቻ ነበርና ከበጎቹ ጋር በሚያወራበት፣ ቋሊማ ነጋዴውን ባነጋገረበት ቋንቋ ነፋሱን አነጋገረው፣ ፀሐይም ሰማች፤ መልሳም ተናገረችው። ሳንቲያጎ፣ በምድር ላይ ያለ የሰው ዘር ሁሉ የዘነጋውን፣ ምሁራን የሳቱት፣ ፈላስፎች የዘለሉትን ፅንፈ አለማዊውን ቋንቋ ከግዑዛን ጋር አወራበት። የፓውሎን ዘ-አልኬሚስት የመጨረሻውን ገፅ ስንዘጋ ፅንፈ-ዓእማዊው ቋንቋ ፍቅር መሆኑን ነግረናል።

ከጥንጥዬዋ አተም እና ግዙፉ ፅንፈ አለም ውስጥ ያሉት የከዋክብት ረጨቶች በሕብረት የሚንቀሳቀሱበት ቋንቋ እውነት ፍቅር ይሆን? ቅዱሳት መፅሐፍት 1001 ጊዜ ነግረውን አልገባን ያለውን፣ ፓውሎ ኮሆሊዮ በዘ-አልኬሚስት መፅሐፉ ለ30 ሚሊዮን ሰዎች አስነበበን። እኛ ደሞ ለእናንተ አካፈልናት።

እጀ-መንገድ

እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

ጥቁርና ነጭ ብርድ ልብስ

በ1969 በሞሀመድ ዚያድባሬ የሚመራው የሶማሌ ጦር ምስራቅ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ።ኦጋዴን፣ ደገሀቡር፣ ገላዲን፣ቀብሪደሀር፣ጂጂጋ፣ቀላፎ፣ዋርዴር፣ጎዴ፣... በሶማሌ ጦር እጅ ወደቁ። በመላው ኢትዮጵያ የእናት ሀገር ጥሪ ተደረገ። ለዚህ ጥሪ 300 000 የሚሊሺያ ሠራዊት አባላት ምላሽ ሰጥተው ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ዘመቱ። ይህ ነው ምኞቴ እኔ በሕይወቴ፣ ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ፣ የሚለው መዝሙር የነዚህ ሚሊሺያ ሰራዊት አባላት የጋራ መዝሙር ነበር። ከአዋሽ ወንዝ ጀምሮ የሶማሌን ወራሪ ጦር አባረው፣ ገላዲንን ነፃ አውጥተው፣ በሶማሌ ድንበር ውስጥ ገልደጎብ ላይ ምሽግ ቆፍረው ለ12 ዓመታት ድንበር የጠበቁት እነዚህ የሚሊሻ ሠራዊት አባላት፣ ከመላው ኢትዮጵያ ከሁሉም ብሔረሰቦች የተውጣጡ፣ ሕዝባዊ ሠራዊት ነበሩ።አላማቸውም አንድ ነበር።ሀገራቸውን ከጥቃት መከላከል። እነዚህ ከሀገሪቱ የተለያየ ክፍል፣ከዳር እስከዳር ለአንድ ዓላማ በነቂስ የወጡት የሠራዊቱ አባላት ታጠቅ ማሰልጠኛ ጣቢያ ለስልጠና ሲገቡ በጥቁርና በነጭ ብርድልብስ ምክንያት እርስ በርስ ተጋድለዋል። ዛሬ ካራማራ ተራራ ላይ፣ ያልወለቁ በሺህ የሚቆጠሩ የወታደር ጫማዎች አሉ። እነዛ ጫማዎች ለእናት ሀገር ምድር፣ ለእናት ሀገር ሰማይ ፍቅርና ልዕልና የወደቁ የሕዝባዊ ሠራዊት አባላትን ቅሪት አፅም እንደያዙ ናቸው። እነዚያ ጫማዎች፣ እርጉዝ ሚስቶቻቸውን ከባዶ ቤት ጥለው፣ ያጨዱትን ሳይሰበስቡ፣እንደወጡ የቀሩ የሀገራችን የቁርጥ ቀን ልጆች ቅሪት መቃብር ናቸው። ለአሥራ ስምንት ዓመታት በሐረርጌ ሜዳዎች ተፈንግለው ይታዩ የነበሩት ታንኮች፣ በየሜዳው እንደድንጋይ ይለቀሙ የነበሩ የሞርታር ጥይቶች፣ በየቦታው ይታዩ የነበሩ፤ የወታደር መኪኖች እነዚህን ሠራዊቶች ጭነው ነበር። በ1972 የዋርዴር አዙሪት የዋጣቸው 370 የሚሊሻ አባላት አላማቸው አንድ ነበር።” እናት ሀገር ወይንም ሞት!” ።እነዛ የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት አብዮት የሚለውን ፍልስፍና አያቁም። ማርክስና ሌኒን በመንደራቸው ማንም አይደሉም፤ ደርግን፣ ወይንም ሶሻሊዝምን ለመከላከል አይደለም የዘመቱት፣ የሶማሌ ጥላቻም አይደለም። የሀገር ድንበር ለማስከበር ብቻ ነው። በ4ኛው የአብዮት በዓል በአብዮት አደባባይ ሰልፍ ካሳዩት እነዛ ሁሉ የሠራዊት አባላት፣ ብዙዎቹ በክብር ወደቤታቸው አልተመለሱም።ያን ያህል ሀገራቸውን ይወዱ የነበሩ፣ ለሀገራቸው ያላቸውን ሁሉ የሰጡ እንዴት በብርድ ልብስ ምክንያት እርስ በርስ ተላለቁ?

ከመላው ሀገሪቱ የተመለመሉት የሠራዊቱ አባላት ወደ ታጠቅ ጦር ሠፈር የገቡት በቅደም ተከተል ነበር። ለጦር ሠፈሩ የሚቀርቡት ቀድመው ሲገቡ፣ ራቅ ያሉት ዘግየት ብለው ተከታተሉ። ቀድመው የገቡት ነጭ ብርድልብስ ሲሰጣቸው በኋላ የገቡት ጥቁር ብርድልብስ ታደላቸው። ጠዋት ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ ለቁርስ ሲሰለፉ በብርድ ልብስ ቀለም ተቧድነው አጠገባቸው ባገኙት ነገር ሁሉ ተጨፋጨፉ፣ በዛ ቀን 273 ሬሳ ተለቀመ።በሺህ የሚቆጠሩ ቆስለው ለሆስፒታል ተዳረጉ።ታጠቅ ጦር ሠፈር፣ ለአንድ ዓላማ የወጡ፣ የወንድማማቾችን ደም ጠጣች።

ዛሬም የሀገራችን ድህነት እያሳዘነን ውስጣችን ለእናት ሀገር ሊሞት እየተዘጋጀ፣ ከውጭ በለበስነው አቋም እርስ በርስ ጠላት ሆንን። ጥንካሬአችን ሊሆን የሚገባው የፖለቲካ አቋማችን ጥቁር ብርድልብስ፣ ውበታችን የሆነው ብሔረሰባችን ነጭ ብርድልብስ ሆነው ለግድያ ተፋጠጥን። አላማችን ግን አንድ ነው። የበለፀገች ኢትዮጵያን መፍጠር። ልዩነታችንን አውቀን፣ ልዩነታችንን ካላከበርን፣ ዓላማችን የጠላት ዒላማ ይሆናል፣ ሕልማችንም ቅዠት ሆኖ ይቀራል። በዚሁ ምክንያት በገዛ ድሎቻችን እኳን ተሸነፍን። በበለጥንበት ሜዳ ተሸንፈን ወጣን። ኃያል ሆነን ሳለ ደክመን ወደቅን።

                               ሕብረት ኃይላችን ነው።

EJE MENGED[ኮድ አርም]

እጀ-መንገድ እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

ኮምጣጤ ቀማሾቹ

ጥንታዊ ቻይናዎች የኛ ታሪክ 10ሺ አመት ታሪክ ነው ይላሉ። የነሱ የ10ሺ አመት ታሪክ ከኛ ከ3ሺ መኩሪያችን ጋር ሲነፃፀር አቤት የኛ ማነሷ! እኛ ደግሞ በሉሲ ሚሊዮን ጊዜ እናስከነዳቸዋለን።

እያንዳንዱ የቻይና ገበሬ ቻይና ባትኖር የአለም ስልጣኔ ከጦርና ከፍላፃ አያልፍም ብሎ ያስባል። መድኃኒትን፣ የእርሻ መገልገያን፣ ሥነ-ፅሑፍን ፣ስነ-ሥዕልን፣ ፍልስፍናን፣ ወረቀት ፣ ህትመት ፣ባሩድ ፣ኮምፓስ ... ለአለም ያበረከትን እኛ ነን ይላሉ። እውነትም እኒህ ቻይናዎች ብዙ ነገር ሰርተዋልና! እሱን ለሌላ ጊዜ ላቆየውና አሁን ወደ ኮምጣጤ ቀማሾቹ...

በቻይና ትላልቅ ከተማዎች በሚገኙ ጠባባብ መንገዶች ያሉት ሱቆች አንድ ስዕል ይሸጣሉ ወይንም ይሰቅሉታል። ማስተር ኮፒው ከቻይና ሀብቶች አንዱ ሆኖ በፔኪንግ ሙዚየም የሚገኝ ሀብት ሲሆን ቅጂዉን ግን ብዙ ሠዎች ሠርተዉታል።

እንግዲህ እኔና እናንተ ወደዛ ቻይና መንደር እንሂድ።ለቻይና እኛ ቱሪስት ልንሆን አንችልም። ቻይናውያን ምግብ ያልበላ ሠው ከቤቱ መውጣት የለበትም ይላሉ። እኛ ደግሞ ረሐባችን ፀሐይ የሞቀው ነው።ስለዚህ አንዱ ቻይናዊ ሱቅ ገብተን እንግሊዝኛ እናወራለን። እነቻንግን ጥቁር አሜሪካዊ እንምሰላቸው ይሄ ዉሸት አይደለም። ክርስቶስ ሳይወለድ በፊት የነበረ ቴክኒክ ነው። የእስራኤሉ ንጉስ ዳዊትም ይህችን ዘዴ ተጠቅሞባታል። ታዲያ እኛ ለቻይናዊ ጥቁር አሜሪካዊ ሆነን ብንቀርብ ዉሸት ነው?

አሁን አንዱ ስዕል መሸጫ ገብተናል አሉ።ከዚያ ሊን አገኘንና አንድ ታሪካዊ ስዕል ስጠን ስንለው ምን እንደሚሰጠን ገምቱ! ኮምጣጤ ቀማሾቹን።

ስዕሉ ላይ ሦሥት ሠዎች ኮምጣጤ የያዘን ማሰሮ ከበው ቆመዋል። ሶስቱም በጣታቸው ኮምጣጤዉን ይቀምሳሉ። የያንዳንዳቸዉ ፊት የኮምጣጤዉን ጣዕም ያሳያል። እነዚህ ሰዎች ሶስቱ ታላላቅ የቻይና መምህራን ኩንግፉ(የኋላው ኮንፊሺየስ) አጎት ቡድሀና የታኦዪዝም መስራች ላኦድሱህ ናቸው። የመጀመሪያው ተፋው። ሁለተኛው ፊቱን ኮሶ አስመሰለው። ሶስተኛው ከት ብሎ ሳቀ።ፊቱን ኮሶ ያስመሰለው አባት ኩንግፉ ምንጣፉ በትክክል ካልተነጠፈ መምህሩ መቀመጥ የለበትም የሚል ፍልስፍና ይዞ የነበረበትን ዓለም መቃወም ያዘ።ሁለተኛው ሰው አጎት ቡድሀ አለም መራራ ናትና ራቃት ብሎ ቢጫ ቀሚስ ለብሶ ብትውናዉን ተያያዘው።

ሶስተኛው ኮምጣጤ ቀማሽ ከት ብሎ የሳቀው ላኦድሱህ(ታኦ)የዚህን አለም መከራ ውስጧ እየኖሩ መተው ስለማይቻል በፈገግታ መቀበል የመረጠው ነው።

አሁን ደግሞ ከቻይና መንደር ወደ ሠፈራችን እንመለስና ከነዚህ ሶስት መምህራን የሚጠቅመንን የላኦድሱህን ጥበብ እንመርምር። እንደ አባት ኩንግፉ ከማይጥመን ሁሉ እየተጣላን መኖር አያዛልቅም።...... ዛሬ በስደት ባለንባቸው ሀገሮች ሁሉ ሀበሻ ወሬኛ፣ሀሜተኛ፣ ምቀኛ እያልን ከወገናችን ርቀን እንደ አጎት ቡድሀ አለም በቃኝ ብለን በአንድ ክፍል ውስጥ ቲቪ እያየን መዋልናማደር ያለብን አይመስለኝም።

ላንዳፍታ በምናብ ሀገር ቤት ሂዱና ያደግንበትን ማህረሰብ ቃኙልኝ። ሙቀጫ የገዛ ጎረቤቱ ባለው ዘነዘና ተማምኖ ዘነዘና ለመዋስ ጎረቤት መሄድ አያሳፍርም ። ስኳርም ሽሮም በርበሬም ቢጎድል ጎረቤት ከሚኬድበት ማህበር ተፈጥረን እዚህ ችግራችንን የምናካፍለው አለመኖሩ ስልጣኔ ነው?አዲስ አመትን በህብረት በችቦ ብርሀን የሚቀበል፣ዳመራን ተጠራርቶ ከሚለኩስ፣በሬን ቅርጫ አርጎ ከሚካፈል ህዝብ መሐል ወጥተን አመት በዓልን ቤት ዘግቶ የሚያስቀምጠን መሻሻል ይሆን?

ባለፈው እትም የኛው አኪለስ ሒል በሚል ርዕስ ስር ሕብረት ማጣታችን ትልቁ ድክመታችን እንደሆነ አንስቼ ነበር። ህብረት ያሳጣንም ወገናችንን መናቃችን፣ አጉል ባህሪዉን መጥላታችን ነው።

የወገናችን ነገር ስላልጣመን እንደ ቡድኀ ባሕታዊ መሆንን መረጥን።ግንኮ ሌላም አማራጭ አለ። እንደ ላኦድሱህ ኮምጣጤ ቀምሶ መሳቅ!!! የጠላነዉን ከማጥፋት ወደ መራቅ ተሻሽለናል። አሁንም እንሻሻልና ከማንወደው፣ ከማይጥመን ጋር የመስራትና የመጠቀም ብልሀትን እንማር።የወገናችንን ያልጣመንን ባሕሪ ስቀን አሳልፈን ጣፋጩን እናጣጥም።በዝቅተኛ ደሞዝ እድሜ ልክ ከመስራት እንደ ታኦ በኮምጣጤው እንሳቅና አብረን እንደግ። በተናጠል የማይቻል፤ በሕብረት መቻሉን እንመን። አበው አክሱምን ያቆሙት በህብረት ነው።ላሊበላን ካንድ ቋጥኝ የፈለፈሉት በሕብረት ነው።አድዋ ላይ ድል ያደረጉት በሕብረት ነው።

ለመሆኑ አያቶቻችን ያን ሁሉ አብረው ሲሰሩ ሁሌም የሚተቃቀፉ ነበሩ? የአድዋ ዘማቾች ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው። የዐድዋ ጦር ዘማቾች ከክተቱ በፊት በስልጣን ሽኩቻ እርስ በርስ ሲዋጉ የነበሩ ናቸው። አድዋ ላይ ግን ጠላትን በሕብረት ድል አደረጉት። እኛም በሀበሻ ላይ የማንወደው ነገር ቢኖርም አብረን መስራት ግን መማር አለብን።

እንግዲህ የኮምጣጤ ቀማሾቹን ታሪክ ለትምህርት ለተግሳፅና ልብንም ለማቅናት ይጠቅም መስሎኝ ከቤንጃሚን ሆፍ መፅሐፍ ያገኘሁትን ተረኩላችሁ። እጀ-መንገድ እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

የእንጦሮጦሱ ችሎት

ይህችን ተረት የነገሩን የጎንቸ ቤቴው የሀገር ሽማግሌ ዳሞ ናቸው።የጎንቸ ቤቴ የቸሀዎች መንደር ነው።ተረቲቱ በሰባት ቤት ጉራጊኛ ትነገር እንጂ እኛ በአማርኛ ነው የምንተርታት። ከመልዕክቷ ምጥቀትና ጥልቀት የተነሳ ፅንፈ-ዓለማዊ ይዘት እንዲኖራት መቸቷን ዘላለማዊና ዓለማቀፋዊ አደረግናት፤ እንጂ ተረቲቷ እንዲህ አልነበረችም። የዳሞ ተረት የሕዝብ ሀብት ናትና “ኮፒ ራይት” የለባትም።ስለዚህ ተረቲቷን ቀጣጥለን እንዲህ አራዝመናታል። እንደ ቅዱስ ፅሑፉ ትንቢት ሰይጣንና ጭፍሮቹ ከሚካኤልና ከሰማይ መላዕክት ጋር ተዋጉ።ታዲያ እነሰይጣን ተሸነፉና ከሰማይ ወደ ምድር ተጣሉ።(የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 12 ቁጥር 7-10)

ሰይጣን በእንጦሮጦስ ዘውዱን እንደጫነ ጳላንዛፌርን ጠራና ስለ ኢትዮጲያ አንድም ሳይቀር መረጃ እንዲያመጣለት ላከው። ጳላንዛፌርም በአንድ ሺኛ ካልኢት ተመልሶ መጥቶ ስለሉሲና የዓለም ሕዝብ ሁሉ ከኢትዮጲያ እንደተበተነ ነገረው። የሙሴ የቃልኪዳን ታቦት ኢትዮጲያ እንዳለ፣ ክርስቶስና ነቢዩ ሞሐመድ ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን፣ግማደ መስቀሉ ኢትዮጲያ እንዳለ ሲነግሩት የሰማይ ሽንፈቱን የሚወጣበት ቦታ በማግኘቱ ልቡ ጮቤ ዘለለች። እርኩሳን ወዳጆቹን ሰበሰበና ኢትዮጲያን ለማጥፋት ምን እናድርግ ብሎ ምክር ጠየቀ።በተንኮል የተጠበቡት እርኩሳን መላዕክቱ ዕኩይ ሀሳባቸውን አዥጎደጎዱት። ጳጢያሮቢንዳ የተባለው ተንከሲሱ ሽማግሌ ጋኔል “በመጀመሪያ ጥንካሬያቸው ምን እንደሆነ እንወቅ አለ። ሰይጣን ወደ ጳላንዛፌር ዘወር ሲል ታሪክ አዋቂው ጭራቅ ከመቅፅበት የሔሮዶቱስን “ዘ ሂትሪስ” መፅሐፍ ገልጦ ምዕራፍ ሦሥትን በአንድ ቅጭታ ፉት አላትና ኢትዮጲያውያኖች አያርሱም በፈንታው መሬታቸው ራሷ ቀን በቀን የተትረፈረፈ ምግብ ታቀርብላቸዋለች። ከመሬታቸው የሚፈልቀው ዉኃ እጅግ ልዩ ስለሆነ ከዓለም ካሉ ሰዎች በጠቅላላ ዕድሜ ረጅሞች ናቸው። መሬታቸው ዕጅግ ለም፣ ሰዎቻቸውም ድንቅና ማራኪ ዉበት ያላቸው ናቸው። እያለ ሲተነትን ሰይጣን አቋረጠውና ከዛሬ ጀምሮ ሐገሪቱ በበሽታና በረሐብ እንድትማቅቅ፣ የግዮን ወንዝም ለም አፈራቸውን ለባሪያዬ ለፈርዖን እንዲገብር የሚል ዉሳኔውን አሳለፈ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ የአባይ ወንዝ ለሙን አፈር እያጠበ ለግብጥ ይገብራል። ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አቃጣሪ ጭራቅ እያለከለከ ሰይጣን ችሎት ገብቶ ኢትዮጲያውያን አክሱም ላይ ክዋን (ኦብሊክ) አቆሙ ብሎ ተናገረ። ሰይጣንና ጭፍሮቹ ችሎቱን ትተው ወጥተው ሲመለከቱ ከአንድ ድንጋይ የተወቀሩ ብዙ ድንጋዮች ውደ ሰማይ ተቀስተው ቆመው ተመለከቱ። ሰይጣን ተናዶ ዳግም እንዲህ ያለ ነገር እንዳይሰሩና ስማቸው እንዳይገን ዕውቀት ንሷቸው ሲል አዘዘ። በጥልቁ ጨለማ(በእንጦሮጦስ አቆጣጠር)፣ሰይጣን በትረ-መንግሥቱን በያዘ በአምስተኛው ቀን የላሊበላ ቤተ-መቅደስ መታነፁን ነገሩት።ሰይጣን እመር ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ስልጣኔ እንዳይኖራቸው እውቀት ንፈጓቸው አላልኩምን? ብሎ ቢያንባርቅባቸው ሽሜው ጳጢያሮቢንዳ ዝግ ብሎ እነሱኮ በዕውቀት ሳይሆን በጥበብ(ዊዝደም) የተሞሉ ናቸው፤ ጥበባቸውን ካልነጠቅናቸው ልናቆማቸው አንችልም። ቢል ሰይጣን በትዝታ ተመስጦ እውቀታቸውን መውሰድ እችላለሁ ጥበብ ግን በተፈጥሮ ያገኙት ከፈጣሪ የተሰጣቸው ነውና የኔ ያልሆነውን ልወስድ አልችልም ብሎ የርኩሳን መናፍስትን አንጀት በሃዘን አንቦጫቦጨው። ሆኖም ሰይጣንና ምክር ቤቱ ኢትዮጲያን በዘር በሃይማኖት በጎሳ በቋንቋ በድንበር እንድትከፋፈል ተስማምተው ተለያዩ በዚህም የተነሳ የመሳፍን ዘመን ሰፍኖ እረስ በርስ ለ200 አመታት ተፋጀን የእንጦሮጦሱ ችሎትም አረፈ። ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወሬኛ ጋኔል ከኢትዮጲያ ውስጥ አንድ ቴዎድሮስ የተባለ ሰው ተነስቶ ኢትዮጲያን እንደጥንቱ አንድ ሊያደርግ ነው ቢሉት ሰይጣን በቸልተኝነት አንድ የእኛን ጦር ላክና ቴድሮስን አምጣልኝ ብሎ መከላከያ ሚኒስትሩን አዘዘው ሚኒስትሩም እንግሊዝን ላከ አንድ ቀን ስይጣንና መከላከያ ሚኒስትሩ የተንኮል ድር ሲያደሩ ድንገት ሰይጣን ለመከላከያ ሚኒስትሩ ያ ቴዎድሮስ የሚባለውን ሰውዬ ጠፍራችሁ ዐምጡልኝ አላልኩምን? ቢለው ሚኒስትሩ ሲፈራ ሲቸር እሱማኮ ከነፍሱ ኩራቱ በልጦበት እጄን አልሰጥም ብሎ ሞተ ቢለው ሰይጣንን አብዝቶ ገረመው እኚህ አበሾች እንዴት ያሉ ሞገደኞች ናቸው ?ሲል ተናገረ ይህን እያወሩ ሳለ ለሰይጣን የሳተላይት ጥሪ ደረሰው ሚኒሊክ የሚባል ሰው ትነስቶ ኢትዮጲያ አንድ አደረገ ሲሉት ፈረሴን ጫኑለኝ አለና አንድ የጣልያን ጋኔል ላይ ተቀምጦ ወደ ኢትዮጲያ ጋለበና አድዋ ላይ ጦሩን አከማችቶ ቁጭ አድዋ ዘምቶ ጭራውን እግሮቹ ስር ቆልፎ አይዋረዱ ውርደት ተዋርዶ ወደ እንጦሮጦሱ ሲመለስ ጳጢያሮቢንዳ ዬንጦሮጦሱ ችሎት የአንጋፋው እርኩስ መንፈስ ሃሳብ ለማዳመጥ ተገዶ ሽሜው እንዲህ ነበር ያሉት እናንተ ሰይጣኖች ለመሆኑ የአበሻ ሚስጥር አይገባችሁምን ሀበሻ ሀገሩን በጣም ያፈቅራል ድሃ ሆነ ሃብታም ለሃገሩ ያለው ፍቅር ከሚስቱ ይበልጣል እርጉዝ ሚስቱን ከቤት ብቻዋን ትቶ አድዋ እንደዘመተ አላያችሁምን ?እና ለሃገሩ ሊሞት የቆረጠ ሰው ተዋግታችሁ ልታሸንፉ ይቻላችሗልን ?ሲሉ ሰይጣን ጣልቃ ገባና ፍቅር ከፈጣሪው ነው የተሰጠው እና የሃገሩን ፍቅር ልንወስድበት አንችልም የተሻለው ሃሳብህ ምንድን ነው ሲለው ሸበቶው ሰይጣን ህብረትን እንከልክላቸው ጥንካሬአቸው ህብረታቸው ነው ሲል ተፈሪ መኮንን የሚባል ንጉስ አፍሪካን አንድ ሊያደርግ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አቋቋመ የሚል ዜና ሲመጣ ጭፍሮቹን ምን እናድርግ ቢላቸው ሁሉም ባንድ ድምጽ ህብረት እንንሳቸው አሉ እነሆ የዕንጦሮጦሱ ችሎት ኢትዮጲያውያንን ህብረት ነሳቸው። የመጀመሪያው ብስራት ያመጣው ሾካካ ጭራቅ ኢትዮጲያዊያን እነ ገርማሜ ነዋይን አስሮ ሰጠ።ቀጠለ የኢትዮጲያ ህዝብ በላይ ዘለቀን ቆሞ አሰቀለ። ተብሎ ሲነገረው ከሰማይ ከተባረረ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ አለ ከዛማ የምስራች መከታተል ያዘ።ጓደኛ ጓደኛውን አጋልጦ አስገደለ፣ጎረቤት የጎረቤቱን ልጅ አሳልፎ ሰጠ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን አቀለላት፣ ሀገሩን ናቀ።

   ጳጢያሮቢንዳ ኢትዮጲያዊያንን ህብረት እንከልክላቸው በሚለው የጦር ስልቱ ለማሸነፍ በመቻሉ በእንጦሮጦስ ዘላለማዊ የጀግና ሃውልት ቆመለት     
 ከዛን ጊዜ በሁዋላ በፊት ሆኖ የማያውቀው ስደት በጣም በዛ እነሆ እድሜ ለጳጢያሮቢንዳ ኢትዮጲያዊያን በተሰደዱበት ሀገርንኳ መተባበር አቅቷቸው የመጨረሻ ዝቅተኛ ኑሮ መኖር ጀመሩ ኑሮአቸውም ሳህን በማጠብ ቡና በማፍላት መንገድ በመጥረግ መኪና በመጠበቅ መምራት ጀመሩ የእንጦሮጦሱም ችሎት ኢትዮጵያውያንን ሕብረት በማሳጣት ድሉን ተጎናፅፎ በኢትዮጲያውያን ላይ የከፈተውን ፋይል ዘጋ።

ይህችን ታሪክ የተረክንላችሁ እኔና የጎንቸ ቤቴው ዳሞ ነን።

እጀ-መንገድ እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ። ገብረ-ጉንዳን ጉንዳን 52 ሚ.ሜ ናት። እቺ ጥንጥዬ ነገር በምድር ላይ መታየት ከጀመረች 110 ሚሊዮን ዓመት ይጠጋታል።አበቦች መፈጠር ከጀመሩ ወዲህ ከ12000 በላይ የጉንዳን ዝርያዎችም አብረው ተፈጥረዋል።እኒህ ጉንዳኖች ከአንተርክቲካ በቀር በምድር ዙሪያ የሌሉበት ቦታ የለም።ጉንዳን ልቧ ቂጧ ላይ (አብዶሜን)ነው።ለነገሩ እሷ ልብ ትበለው እንጂ የሕብለ-ሰረሰርዋን (Spinal cord) ጫፍ ነው እንደ ልብ የምትገለገልበት።ጉንዳን ጥንጥ ትሁን እንጂ የክብደቷን ሃምሳ እጥፍ ትሸከማለች። ይሁንና በጉልበቷ ተማምና ብቻዋን ከመኖር ከሌሎች ጉንዳኖች ጋር በአንድ መንጋ እስከ ሚሊዮን ሆነው በሕብረት የመኖርን ጥበብ ተክናዋለች።አብረው በመኖራቸው በምድረገፅ ከሚኖሩ ፍጥረታት ጠንካራ ግዛት(Colony) ካላቸው የመጀመሪያዋ ለመሆን ችላለች። እንግዲህ ይህችን ጉንዳን እንዳስብ ያደረገኝ The Ant bully የሚለው Animation ፊልም ነው።የገብረ-ጉንዳን ታሪክ በThe Ant bully ፊልም በጁሊያ ሮበርትስና በኒኮላስ ኬጅ ድምፅ እየተተረከ ጉንዳኖቹ ይናገሩን ጀመር።ታሪኩ አንድ ሉቃስ የተባለ ትንሽ ልጅ የጉንዳን ቤት እያፈረሰ ጉንዳኖችን ያስቸግራል።አትክልት አጠጣ ሲባል የጉንዳኖችን መኖሪያ በጎርፍ ያጥለቀልቃል። በሉቃስ እኩይ ባሕርይ የተቸገሩት ጉንዳኖች ችሎት ተሰይመው ሉቃስን የሚያጠፉበት ዘዴ ሲቀይሱ አንድ ጠቢብ ጉንዳን መላ ይፈጥርና ሉቃስን ጉንዳን ያሳክለዋል።ሉቃስ ጉንዳን አክሎ ችሎት ሲቀርብ ንግስቲቷ ሉቃስ እንዲሆን ፈርዳበት እንደ ጉንዳን መኖር ይጀምራል።ጉንዳኖች በሉቃስ አስመስለው በ The Ant bully ጉንዳንነትን አሳዩን። ከጉንዳኖቹ ነፍሴን የነካቻት ቃለ-ተውኔት እነሁዋት።ሉቃስና ጠቢቡ ጉንዳን በጠፍ ጨረቃ ለጥ ኮረት ድንጋይ ላይ ተኝተው ያወራሉ።ጠቢቡ ወደ ሰው ልጆች መኖሪያ እየተመለከት ጠቢቡ ጉንዳን፡ ”እዛ የሚኖሩት የሰው ልጆች ሁሉ ለሰው ልጅ ሉዓላዊነት በህብረት ትሰራላችሁ አይደል?” ሉቃስ፡ “እንደዛ ሳይሆን ሁሉም ለራሱ በግሉ ነው የሚሮጠው” ጠቢቡ ጉንዳን፡ “ያማ በጣም ሁዋላ ቀርነት ነው።አንድ ሰው፣እንዴት ብቻውን ሁሉን ሰርቶ ሊጨርስ ይችላል?” ሉቃስ፡ “አንዳንድ አብረው የሚሰሩ ሰዎች አሉ።” ጠቢቡ ጉንዳን፡ ”ለምን ሁሉም አብረው አይሰሩም?” ሉቃስ፡ “ብዙ ልዩነት ስላላቸው መሰለኝ” ጠቢቡ ጉንዳን፡ “ልዩነት ነው አንድን ማህበረሰብ ጠንካራ የሚያደርገው፤ ለምሳሌ በኛ ውስጥ ሁላችንም የተለያየን ነን።ግን ሁሉም አስፈላጊያችን ናቸው።ጥንካሬያችንም ያለው ሕብረታችን ላይ ነው::” ሉቃስ፡ “እኛጋ ግን እንዲህ አይደለም፤ ለምን እንደሆነ እንጃ ብቻ ዝም ብለን እርስ በእርስ እንጠላለፋለን።” ጠቢቡ ጉንዳን፡ (በቁዘማ)”እኔም አንዳንዴ እንደሰው ልጅ የማደርገውን አላቅም።”(ፊልሙ ላይ ጓደኛ ሳይሆኑ በፊት ሉቃስን ሊያጠፋ ይፈልግ ነበር) “I am small, we all are small but together we are big” Lucas ከThe Ant bully የተወሰደ በተናጠል ደካሞች ነን። በህብረት ግን ጠንካሮች ነን።

እጀ መንገድ

እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

የማይመች እውነት Jessica፣ ስራ ቦታ ጣፋጭ ታሪክ የምታስወራን ናት። እኔ፣ የካሲዮፒያንና የአንድሮ ሜዳን ታሪክ አወራሁ። ኤድሪያን፣ አባቱ ስራ ሳይሔድ ቤት ከሱጋ እንዲጫወት ሲል አባቱን በሰዓት 20 ዶላር ሊቀጥር ስለፈለገው የ5 ዓመት ሕፃን ታሪክ ነገረን።Jessica፣ራሷ የክርስቶስ ሰምራን አይነት ታሪክ በእንግሊዝኛ ነገረችን። ራሺያዊቷ Monika ስለማይጨልመው የሌሊንግራድ(ፒትስበርግ) ሌሊት አወራች።ሕንዳዊቷ መነኩሴ Tess፣ የሚቀጥለውን ታሪክ ተረከችልን። “ከዕለታት አንድ ቀን በአሜሪካ የሚኖር አንድ አሜሪካዊ ሳይንቲስት ነበረ፣ ይህ ሳይንቲስት ከልጅነቱ ጀምሮ በፈጣሪ አያምንም ነበር። አንድ ጊዜ ከአሜሪካ ለዕረፍትና ለጉብኝት ወደ ሕንድ ሔዶ 8 ወር ቆይቶ ሲመለስ ቤተ ክርስቲያን አዘውታሪና ፀሎተኛ ሆነ። ማንነቱን የሚያውቁት ተገርመው እንዴት በፈጣሪ ለማመን እንደበቃ ሲጠይቁት እንዲህ ብሎ መለሰ።

‘ሕንድን ከላይ እስከታች አየሁዋት።የሀገሬው ሕዝብ ሁሉ የሚያውቀው አንድ ቋንቋ የለም፤ ሒንዱዎችና ሲኮች አይዋደዱም፣ ሙስሊሞችና ሒንዱዎች ጠላት ናቸው፣ሀብታሞቹ መለስተኛ ሀብታሞቹን አይወዷቸውም፤የከተሜው ለማኝ እንኳን ፣የገጠሩን ለማኝ አይወደውም፤ ሕዝቡ እርስ በርሱ ምቀኛ ነው። አንዱ አንዱን አሳልፎ መስጠት ባሕል ነው፣ ባለ መኪናው ባለ ሶስት ጎማ ታክሲዎችን አይወድም፡ ሀገሪቱ በጥላቻ የተሞላች ናት። አስገራሚው ነገር ሀገሪቷ አልፈረሰችም፣ እንዲያውም እያደገች ነው።እስቲ ንገሩኝ ፈጣሪ ባይኖር ኖሮ እቺ ሀገር በጥላቻ በምቀኝነት፣ ብቻ አትፈርስም ነበር ወይ?’ አላቸው ይባላል።” የኔዋን ሀገር አሰብኳት። ሙስሊምና ክርስቲያን ተፋቅረው የሚኖሩባትን ወሎን፣ አንዋር መስኪድንና ራጉኤል ቤ/ክርስትያንን አጠገብ ለአጠገብ የያዘችን መርካቶን፣ የመስቀል ደመራ ለመለኮስና አረፋ(ኢድ አልድሐ)ን ለማክበር የጉራጌ ልጆች የሚሔዱባት ቡታጅራንም አሰብኳቸው። ይህም ሆኖ በዓለም ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ ድሆች ነን። ሀብታም ሀገሮች ገብተንም የመጨረሻ ደሀና ዝቅተኛ ኑሮ ነው የምንኖረው።በቶሮንቶ በአንድ ፋብሪካ ብቻ 800 ኢትዮጵያውያን የጉልበት ሥራ ይሰራሉ።በአንድ ሆቴል ውስጥ ብቻ 50 ኢትዮጵያውያን በዝቅተኛ ሥራ መስክ ለረጅም ዓመታት ሰርተዋል።ከDundas በታችና በJarvis ና በSpadina መካከል 30 Tim Horton’s Cafe ሲኖር 21ዱ ኢትዮጵያዊያውያን ይሰሩባቸዋል።የቶሮንቶው Imperial Parking ውስጥ ከሚሰሩት 201 ሰራተኞች ውስጥ 89ኙ ኢትዮጵያውያን ናቸው።በቶሮንቶ ከሚገኙ 1400 Becks ታክሲዎች ውስጥ 507 ኢትዮጵያውያን የBecks ታክሲን እንደሚነዱ መረጃ አግኝተናል። ኮንስትራክሽንና ፅዳት የሚሰሩትን መገመት የሚችልንኳ ጠፋ። እስከ ሀምሳ ሺህ ኢትዮጵያውያን ይኖረባታል ከምትባለው ቶሮንቶ 90 በመቶው በተመሳሳይ ስራ እንደተሰማሩ ይታመናል። ከስልጣኔ አውራነት እንዴት የዓለም ጭራ ሆንን? አባቶቻችን አክሱምን ሲቀርፁ፣ ላሊበላን ሲያንፁ፣አድዋ ላይ ሲመክቱ፣ፋሺስትን ሲረቱ፤ጥንካሬአቸው ሕብረታቸው ነበር። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ብለው የደካሞች ሕብረት ጠንካራውን እንደሚያሸንፈው መንገራቸው ነበር። እውነታውን መካድና፣ እንደለመድነው ከሌላው እንሻላለን ብለን እራሳችንን እያታለልን በባዶ ሜዳ መደገግ እንችላለን። እውነታውን አምኖ መፍትሔ መፈለግ ግን ብልህነት ነው። ካለንበት የድህነት ማጥ ለመውጣት ብቸኛው አማራጭ ሕብረት ነው።ሌላ መፍትሔ የለም። ሌላ መፍትሔ ያለው ካለ ይንገረን።

እጀ መንገድ

እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

ጓጉንቸሮቹ

እቺ ተረት ከጋሽ ስብሐት የተገለበጠች ናት።ጋሽ ስብሐት በግጥም ፃፋት፣ እኔ በስድ ንባብ አስቀመጥኳት።ጋሽ ስብሐት ግጥሚቱን ከየት እንዳመጣት አላውቅም፤ ብቻ አንድ ቀን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለጥፏት ለኔ ተነበበች። በዘመን ርቀት ትርክቷን እንዳለ ለማስቀመጥ ባይቻለኝም፣ ቁምነገሯ ግን ኩላሊት ላይ ተጥፏል።ተረቲቷ እቻትላችሁ። “በአንድ ኩሬ፣ በፈንጠዝያና በደስታ የሚኖሩ ሁለት ጓጉንቸሮች ነበሩ።ከመጨፈርና ከመደነስ በቀር ምንም ችግር ገጥሟቸው የማያውቁ እኒህ ጓጉንቸሮች፤አንድ ምሽት ላይ ያልታሰበ ሁካታና ጫጫታ ይሰማሉ፤ሁካታው ምሽቱን ባደመቀ ብርሀን የታጀበ ነበርና በሁናቴው የተደናገጡትና ግራ የገባቸው ጓጉንቸሮች ከውሀው ወለል ላይ ተለጥፈው የሚሆነውን ሲጠብቁ፣ ጫጫታው እየበረታ፣ ወገግታው እየደመቀ፣ሲመጣ ከውሀው ብቅ ብለው ሲመለከቱ፣ከመንገዱ ማዶ ቤት ተቃጥሎ ሰዎች እሳቱን ሊያጠፉ ሲሯሯጡ ተመለከቱ።እሳቱ ያለው ከመንገዱ ባሻገር፣ በዚህ ላይ እኛ ውኃ ውስጥ ነን ምንም አንሆንም ብለው ኩሬው አናት ላይ ሲፈነጥዙ፣ ሰዎቹ እሳቱን ለማጥፋት ከኩሬው በባልዲ ሲጠልቁ ጓጉንቸሮቹንም ጨልፈው የሚነደው እሳት ውስጥ ጨመሯቸው።” ጋሽ ስብሐት እቺን ተረት ለምን እንደፃፋት እንጃ እኔ ግን ለሆነ ነገር ጠቀመችኝ። ቢሆንልን ሁላችንም ማደግ እንፈልጋለን፣ወይ በትምህርታችን በርትተን የተሻለ ደረጃ ለመድረስ፣ወይ ደግሞ የምናገኛትን አጠራቅመን አገር ቤት ገብተን ኢንቨስት በማድረግ፣ቤት ገዝተንም፣ብቻ በየራሳችን መንገድ ለማደግ እናስባለን።በምንኖርባት ከተማ በቶሮንቶ ኢትዮጵያውያን ለማደግ ሲፍጨረጨሩ እናያለን።ተሳክቶላቸው የከበሩ በዙም ባይሆኑ የሚታገሉትን ግን እያየን ነው። ይህንን ፅሑፍ በምንፅፍበት ሰዓት፣152 በግል ሥራ የሚተዳደሩ እንዳሉ ቆጠርን።ይህም ማለት፣ሬስቶራንቶች፣የሸቀጥ መደብሮች፣ትራቭል ኤጀንሲዎች፣ ሕትመትና ዲዛይነሮች፣ፀጉር ቤቶች፣እንጀራ አቅራቢዎች፣የመX-masኛ ብዙሀን አገልግሎቶች፣የሕክምና መስጫዎች፣የሐዋላ አገልግሎት፣የቴክኒክ ሞያተኞች፣የፎቶግራፍና የቪዲዮ ቀረፃዎች፣የኮምፒውተር ጠጋኞች፣የሙቪንግ ትራክስ ሾፌሮች፣የቤት ጥX-masና ዕድሳት ሞያተኞች፣ድምፃውያንና የሙዚቃ መሳሪያ ሙያተኞች፣.... የእነዚህ እንቅስቃሴዎች በከተማችን መኖር፣በኮሙኒቲ ደረጃ ማደጋችንን የምናይባቸው መንገዶች ናቸው።እነዚህ ድርጅቶች የሚያድጉት ደግሞ እኛ ስንጠቀምባቸው ነው።ለዚህም ነው ሰሞኑን በየአውቶቡስ መጠለያው “support your neighbourhood business” የሚል የኮሙኒቲ ማስታወቂያ የሚታየው ላለፉት 10 ዓመታት 41 የንግድ ድርጀቶች ተዘግተዋል።ለምን እንደተዘጉ ለማወቅ ምሑር ቃለ መጠይቅ ማድረግ አያስፈልገንም። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለነዛ ድርጅቶች መዘጋት አስተዋፆ አርX-masል።አንድ በቅርቡ የተዘጋ ድርጅት ባለቤትን አነጋግረን “... ድርጅቱን በመክፈቴ ተፀፅቻለሁ።እኛ ማኅበረሰብ ውስጥ ማእግ ይቻልም ሲል ተደምጧል። አንድ የመX-masኛ ሚዲያ ከፍቶ የነበረ ኢትዮጲያዊ ከሁለት ዓመታት ግልጋሎት በኋላ ከመዝጋቱ በፊት “አግዙኝ! ብሎ ስብሰባ ጠርቶ የተገኙለት 6 ሰዎች ብቻ ሲሆኑ ከ15 000 ዶላር ኪሳራ ጋር የዜና አውታሩን ሲዘጋ ለሁለት ዓመታት ለሰጠን አገልግሎትንኳ ዕውቅና አልሰጠነውም።” የንግድ እንቅስቃሴ መኖር ሁላችንንም ይጠቅማል።ወጣም ወረደም መX-masኛዎቻችንና አX-masኚዎቻችን ናቸው።አላቂ ዕቃዎችን ያቀርቡልናል።በሥራ የተወጠረ አ ዕምሮአችንን ዘና የሚያረጉልን የመዝናኛ ዝግጀት የሚያዘጋጁልን ናቸው። መረዳዳት ባስፈለገን ጊዜ በመጀመሪያ ለዕርዳታ ዕጃችንን የምንዘረጋው ወደነሱ ነው። አንዳንድ ሬስቶራንቶች፣ በዓመት እስከ 10 000 ዶላር ለኮሙኒቲው ያወጣሉ።(የኮሙኒቲ እንቅስቃሴዎችን ስፖንሰር በማድረግ፣ቀጥተኛ የገንዘብ ልገሳ፣...)፣ ዝግጅቶች፣ወይንም ማስታወቂያዎች ሲኖሩ ፖስተሮች የሚለጥፉትና፣ የመረጃ መቀባበያዎቻችን እነዚሁ ድርጅቶች ናቸው። አንድ ሬጀንት ፓርክ ሠፈር የሚታተም የአካባቢ ጋዜጣ ላይ “support your neighbourhood business”የሚል ፅሑፍ ሳነብ፣ የኮሙኒቲ ንግድ ድርጅቶችን መደገፍ የምንችልባቸውን መንገዶች ሲናገር፣ ከሰው ጋር ቀጠሮ ሲኖረን ወደ ሠፈራችሁ አምጡት፤ አንደኛ እንጋችሁ ሰፈራችሁን ለማወቅ ጥሩ አጋጣሚ ይሆነዋል፣ሁለተኛ፤ የሰፈራችሁ ንግድ ድርጅት ገቢ ያገኛል። መሥሪያ ቤታችሁ አነስተኛ ፓርቲ( የልደት፣ወይንም የሽኝት ግብዣ) ሲኖር፣የሰፈራችሁን ሬስቶራንት አድራሻ ስጡ.... ከሬስቶራንቱ ባለቤትጋ ተነጋግራችሁ የግሩፕ ቅናሽ አስደርጋችሁ መስሪያቤታችሁን አግባቡ። የሠፈራችሁ ሬስቶራንት በምግቡ ጥራት፣ ወይንም በቤቱ ንፅሕና ችግር ካለበት ወጥታችሁ ለጓደኞቻችሁ ከመናገር ለሬስቶራንቱ ባለቤት ንገሩት። ጠንካራ ሠፈር የጠንካራ ጎረቤቶች ውጤት ነው “The great neighbourhood is made up of great neighbours”

አንድ ንግድ ድርጅት ሲዘጋ እኛን አይመለከትም ብለን ነው የምናስበው? እንደዛ ከሆነ ተረቷን ልድገማት። “... በአንድ ኩሬ፣ በፈንጠዝያና በደስታ የሚኖሩ ሁለት ጓጉንቸሮች ነበሩ ...”

1. እጀመንገድ

እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

ዓድዋን በአቫታር

March1, 2010 አቫታርን ለማየት በአይማክስ ስቱዲዮ ተቀምጠን ፊልሙ ጀመረ። የሰው ልጆች ከኢንዱስትሪና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አብዮት በኋላ በ2154 ዓ.ም. እጅግ ኃይለኛና በቴክኖሎጂ የመጠቀ ደረጃ ላይ ደርሰው ፅንፈ አለምን ሲቀራመቱ፣ በአልፋ ሴንቹዋሪ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሀብት፣ በባለቤትነት የያዘው R. D. A. የተባለው ኮርፖሬሽን unobtanium የተባለ ንጥረ ነገር ፍለጋ፣ ከምድር 4.37 የብርሀን ዓመት ርቃ ወደ ምትገኘው አልፋ ሴንቹዋሪ ተጓዘ። በአንድ ኪሎ unobtanium፣ ሀያ ሚሊዮን ዶላር ለማፈስ የቋመጠው R. D. A. ኮርፖሬሽን ፓንዶራ ሲደርስ ችግር ገጠመው። ይህች በአልፋ ሴንቹዋሪ ሥርዐተ ፀሐይ(solar system) የምትገኝ ምድር መሰል ጨረቃ፣ በተፈጥሮ ጥበብና በአካል ብቃት የተካኑ ሰማያዊ የቆዳ ቀለም ያላቸው Na'vi የተባሉ 2ሜትር ከሰባ ሳንቲ ሜትር በላይ የሚረዝሙ ሰው መሰል ፍጡራን መኖሪያ ናት። ኢኒህ ናቪዎች፣ በቴክኖሎጂ የበለፀገ ጦር ሠራዊት በጦርና በፍላፃ ገትረው ያዙ። አርዲኤ የ Na'vi ዎች አይበገሬነት ተልዕኮውን ስለገታው የፓንዶራን ነዋሪዎች ለመሰለል በነዛ የፓንዶራ ፍጡራን ላይ ሰዎችን በናቪዎች አምሳልና አካል የሚያሳድግ አቫታር የተባለ ጥናት የሚያደርግ የሳይንስ ማዕከልን ስፖንሰር አድርጎ የጥናቱን ውጤት ለመካፈል ይስማማል። ማዕከሉ፤ በናቪዎችና በፓንዶራ ፍቅር የተጠመዱ ባለሙያዎችን ያቀፈ ቢሆንም የ Na'vi ዎችን ሚስጢር አስልፎ ለመስጠት ይገደዳል። ኮርፖሬሽኑ ከሰው ልጆች በግዝፍና በሁለት ዕጥፍ የሚበልጡት Omaticaya የተባሉት በሺህ የሚቆጠሩ ነገዶች ይሚኖሩበት የነበረውን እጅግ ግዙፍ የሆነውን የዛፍ ለመገንደስ በ Colonel Quaritch የሚመራው Sec-Ops ጦር ከነመኖሪያ ዛፋቸው ለማጥፋት ሠራዊቱን ይልካል።Omaticayaን በጦርና በፍላፃ የጦር ጀቶችን ይገጥማሉ። ጦርነቱ ምንም የተመጣጠነ አሰላለፍ አልነበረውም።ሆኖም በፓንዶራ የሚኖሩ ጎሳዎች ተጠራርተው፣ የፓንዶራ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥም ረድቷቸው፤ ምድርን አውድመው ፓንዶራንም ሊያወድሙ የመጡትን በፓንዶራ ድል ነሷቸው።ፊልሙ ተጠናቀቀ።የተዋንያኑ ስም መፃፍ ሲጀምር አይኔን ጨፍኜ ማ ማንን ሆኖ እንደሚጫወት ማሰብ ጀመርኩ።

RDA እንደ ፋሺስት ኢጣሊያ;

AVATAR እንደ ሚሽነሪዎች; Colonel Quaritch እንደ ጄኔራል አልበርቶኒ Na’vi እንደ አርበኞች;

ፓንዶራ እንደ አድዋ Neytiri እንደ ጣይቱ ብጡል;

እርግጥ ነው ፊልሙ ላይ ሚኒሊክን ሆኖ የተጫወተው አንድ አሜሪካዊ ነው።የኛም ታሪክ በነሱ ሲፃፍ ስታሮቹ እነሱ ናቸው።እኛ ግን ምናችን ሞኝ ነው? ሳንሱር እያደረግን ፊልሙን እናያለን። The same Quotes from Adwa and Avatar “We will engage the Ethiopians in piecemeal battles” General Oreste Baraterie march 1, 1896 “ ... this mission is not high and tight. I want be home for dinner” Colonel Quaritch The head of Sec-Ops in Avatar “They are not humans, flying beaten savages that living on tree.” RDA Administrator Parker Selfridge in Avatar “... They (Ethiopians) need to learn civilization, they are savages.” brigadier Matteo Albertone. February 1896

የፓንዶራ Na'vi ዎች ፍልስፍናቸው አንድነት፣ውህደት፣ጥምረት ነው።ከተፈጥሮ ጋር መዋሐድ፣ ከወገኖቻቸው ጋር መጣመር፣ በአላማ አንድ መሆን... በአድዋ ደግሞ ሕብረትና ፍቅር፣... አቫታር ለቶሮንቶ ኢትዮጵያውያን ለትምህርት፣ለተግሳጽ፣ልብን ለማቅናትና ለሕብረት ይጠቅማቸው ዘንድ ያየነውን ጣፍ አረግናት።

እጀ መንገድ

ፅንፈ-ዓለማዊው ቋንቋ

     የፅንፈ-አለም ግዝፈቱን ለመረዳት ከመሬት እንጀምር።መሬታችን በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ናት።በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከመሬት ሌላ ስምንቱ ፕላኔቶች (ዘጠነኛዋ ፕላኔት ፑሉቶ አርጅታ በ2006 ሞታለች) ጨረቃዎች፣ ኮሜቶች፣ ሜትዮራቶች፣ ፀሐይ ራሷና ሌሎችም ይገኛሉ።እንግዲህ ፀሐይ አንድ ኮከብ ናት።የኛ ፀሐይ የምትገኝበት ጋላክሲ(የክዋክብት ረጨት)፣እንደ ፀሐይ ያሉ የራሳቸው ሶላር ሲስተም ያላቸው ቢሊዮን ክዋክብት አሉ።የኛ ሶላር ሲስተም (ሥርዐተ ፀሐይ) የምትገኝበት የክዋክብት ረጨት ወተታማ መንገድ(ሚልክ ዌይ) በመባል ይታወቃል እንደኛ አይነት ቢሊዮን ክዋክብትን የያዙ ቢሊዮን ጊዜ ቢሊዮን ጋላክሲዎች አሉ።እነዚህ ሁሉ በፅንፈ አለማችን ውስጥ አሉ።
     አሁን ደሞ እጅግ ግዙፍ ከሆነው ከፅንፈ ዓለማችን እጅግ አነስተኛና ደቃቅ የሆነውን አተም እንመልከት። አተም  ἄτομος/átomos, ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን α-τεμνω, ትርጓሜውም የማይቆረጥ፣ ሊከፈል የማይቻል የመጨረሻ ተካፋይ ማለት ነው። አተም፣ የመጨረሻው ደቃቅም ሆኖ አንድ ነጠላ አተም የሁለት ክፍሎች ውሑድ ወይንም ሕብር ነው።ኑክሊየስና አውተር ሼልስ።ኒኩሊየስ ፕሮቶንስንና ኒውትሮንስን ይይዛል።አንዱን አተም ለሁለት ብንቆርጠውንኳ የራሱ ኒኩሊየስና አውተር ሼልስ ይኖሩታል እንጂ በነጠላ አይቆይም።አስገራሚው ነገር ኤሌክትሮንስ ኒኩሊየስን፣ጨረቃ መሬትን፣መሬት ፀሐይን፣ ፀሐይ ጋላክስዋን፣ ጋላክሲዎች ከሌሎች ጋላክሢዎች ጋር ፅንፈ አለምን፤ በሕብረት ይዞራሉ።

ሕብረት ፅንፈ አለማዊ እንቅስቃሴ ነው። ብቻውን የሚንቀሳቀስ ነገር የለም።ደራሲው ፓውሎስ ምን ይላል? መጀመሪያ ፓውሎን እንወቀው።በትውልድ ብራዚላዊ፣በእምነት ካቶሊካዊ፣ መፅሐፎቹ አለማቀፋዊ፣ አመለካከቱ ፅንፈ-ዓለማዊ ነው።ዘ-አልኬሚስት የሚለው መፅሐፉ 30 ሚሊዮን ቅጂ የተሸጠ ሲሆን፤ በ67 ቋንቋዎችም ተተርጉሟል።አሁን ደግሞ የዘ-አልኬሚስት ደራሲን ፓውሎ ኩዌሊዮን እናመስግንና ፅንፈአለማዊውን ቋንቋ እናጥና።

     ፓውሎ “ዘ-አልኬሚስት” በሚለው መፅሐፉ የቀረፀው ሳንቲያጎ የተባለ በጎቹን የሚያፈቅር የስፓኝ እረኛ፤ አንዲት በደቡባዊ ስፓኝ የምትገኝ፣ አንዳልዱጉ በምትባል የገጠር ምድረበዳ በጎቹን ሲጠብቅ፣ ግብፅ ፒራሚድ ስር ቢቆፍር ሀብት እንደሚያገኝ በሕልሙ ይታየዋል።ይህ በዓመት አንዴ በጎቹን እየሸለተ የሚሸጥ እረኛ፣የበጎቹን ፀጉር ከሚገዛው ነጋዴ ሴት ልጅ በፍቅር ቢሆነልልም፣ የሚወዳቸውን በጎቹንና የነጋዴውን ሴት ልጅ ትቶ ፣ የሜዲትራኒያንን ባሕር አቋርጦ አፍሪካ ሲገባ ያልጠበቀው ነገር ይገጥመዋል። አፍሪካውያኖቹ አረቢኛ እንጂ የእስፓኝ፡ቋንቋ አይናገሩም። 
          አስገራሚው ነገር ሳንቲያጎ ከአንድ አረባዊ ቋሊማ ነጋዴ ጋር ሳይነጋገሩ ተግባብተው ለቋሊማ ነጋዴው ተቀጥሮ ሙሉቀን ሰርቶለት፣ ደሞዙን ቋሊማ ተቀብሎ ሄደ። ወደ ካይሮ የሚወስደውን የስሀራን በርሀ ሲያቋርጥ  አንድ ከፅንፈ ዓለም እየጠፋ ያለውን ፅንፈ-ዓለማዊውን ቋንቋ ከአልኬሚስቶች ለመማር ወደ ካይሮ የሚሄድ አንድ እንግሊዛዊ ፕሮፌሰር ያገኛል። ካይሮ ከመድረሳቸው በፊት በሰሀራ በረሐ በሚገኘው ለምለም ቦታ (oasis of the sahara) አልኬሚስቱ ሳንቲያጎን ፈልጎ መጣ። እኒህ ብረትን ወደ ወርቅነት መቀየር ይችላሉ እየተባለ የሚነገርላቸው ጠቢቦች፤ ከፈላስፎችና ከምሁራን አንድ እረኛን መረጡ። አልኬሚስቱና ሳንቲያጎ በመንገድ ላይ በጎሳ ጦረኞች ተማርከው ከሞት የሚያስጥላቸው ነፋስ ብቻ ነበርና ከበጎቹ ጋር በሚያወራበት፣ ቋሊማ ነጋዴውን ባነጋገረበት ቋንቋ ነፋሱን አነጋገረው፣ ፀሐይም ሰማች፤ መልሳም ተናገረችው። ሳንቲያጎ፣ በምድር ላይ ያለ የሰው ዘር ሁሉ የዘነጋውን፣ ምሁራን የሳቱት፣ ፈላስፎች የዘለሉትን ፅንፈ አለማዊውን ቋንቋ ከግዑዛን ጋር አወራበት። የፓውሎን ዘ-አልኬሚስት የመጨረሻውን ገፅ ስንዘጋ ፅንፈ-ዓእማዊው ቋንቋ ፍቅር መሆኑን ነግረናል።

ከጥንጥዬዋ አተም እና ግዙፉ ፅንፈ አለም ውስጥ ያሉት የከዋክብት ረጨቶች በሕብረት የሚንቀሳቀሱበት ቋንቋ እውነት ፍቅር ይሆን? ቅዱሳት መፅሐፍት 1001 ጊዜ ነግረውን አልገባን ያለውን፣ ፓውሎ ኮሆሊዮ በዘ-አልኬሚስት መፅሐፉ ለ30 ሚሊዮን ሰዎች አስነበበን። እኛ ደሞ ለእናንተ አካፈልናት።

     የፅንፈ-አለም ግዝፈቱን ለመረዳት ከመሬት እንጀምር።መሬታችን በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ናት።በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከመሬት ሌላ ስምንቱ ፕላኔቶች (ዘጠነኛዋ ፕላኔት ፑሉቶ አርጅታ በ2006 ሞታለች) ጨረቃዎች፣ ኮሜቶች፣ ሜትዮራቶች፣ ፀሐይ ራሷና ሌሎችም ይገኛሉ።እንግዲህ ፀሐይ አንድ ኮከብ ናት።የኛ ፀሐይ የምትገኝበት ጋላክሲ(የክዋክብት ረጨት)፣እንደ ፀሐይ ያሉ የራሳቸው ሶላር ሲስተም ያላቸው ቢሊዮን ክዋክብት አሉ።የኛ ሶላር ሲስተም (ሥርዐተ ፀሐይ) የምትገኝበት የክዋክብት ረጨት ወተታማ መንገድ(ሚልክ ዌይ) በመባል ይታወቃል እንደኛ አይነት ቢሊዮን ክዋክብትን የያዙ ቢሊዮን ጊዜ ቢሊዮን ጋላክሲዎች አሉ።እነዚህ ሁሉ በፅንፈ አለማችን ውስጥ አሉ።
     አሁን ደሞ እጅግ ግዙፍ ከሆነው ከፅንፈ ዓለማችን እጅግ አነስተኛና ደቃቅ የሆነውን አተም እንመልከት። አተም  ἄτομος/átomos, ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን α-τεμνω, ትርጓሜውም የማይቆረጥ፣ ሊከፈል የማይቻል የመጨረሻ ተካፋይ ማለት ነው። አተም፣ የመጨረሻው ደቃቅም ሆኖ አንድ ነጠላ አተም የሁለት ክፍሎች ውሑድ ወይንም ሕብር ነው።ኑክሊየስና አውተር ሼልስ።ኒኩሊየስ ፕሮቶንስንና ኒውትሮንስን ይይዛል።አንዱን አተም ለሁለት ብንቆርጠውንኳ የራሱ ኒኩሊየስና አውተር ሼልስ ይኖሩታል እንጂ በነጠላ አይቆይም።አስገራሚው ነገር ኤሌክትሮንስ ኒኩሊየስን፣ጨረቃ መሬትን፣መሬት ፀሐይን፣ ፀሐይ ጋላክስዋን፣ ጋላክሲዎች ከሌሎች ጋላክሢዎች ጋር ፅንፈ አለምን፤ በሕብረት ይዞራሉ።

ሕብረት ፅንፈ አለማዊ እንቅስቃሴ ነው። ብቻውን የሚንቀሳቀስ ነገር የለም።ደራሲው ፓውሎስ ምን ይላል? መጀመሪያ ፓውሎን እንወቀው።በትውልድ ብራዚላዊ፣በእምነት ካቶሊካዊ፣ መፅሐፎቹ አለማቀፋዊ፣ አመለካከቱ ፅንፈ-ዓለማዊ ነው።ዘ-አልኬሚስት የሚለው መፅሐፉ 30 ሚሊዮን ቅጂ የተሸጠ ሲሆን፤ በ67 ቋንቋዎችም ተተርጉሟል።አሁን ደግሞ የዘ-አልኬሚስት ደራሲን ፓውሎ ኩዌሊዮን እናመስግንና ፅንፈአለማዊውን ቋንቋ እናጥና።

     ፓውሎ “ዘ-አልኬሚስት” በሚለው መፅሐፉ የቀረፀው ሳንቲያጎ የተባለ በጎቹን የሚያፈቅር የስፓኝ እረኛ፤ አንዲት በደቡባዊ ስፓኝ የምትገኝ፣ አንዳልዱጉ በምትባል የገጠር ምድረበዳ በጎቹን ሲጠብቅ፣ ግብፅ ፒራሚድ ስር ቢቆፍር ሀብት እንደሚያገኝ በሕልሙ ይታየዋል።ይህ በዓመት አንዴ በጎቹን እየሸለተ የሚሸጥ እረኛ፣የበጎቹን ፀጉር ከሚገዛው ነጋዴ ሴት ልጅ በፍቅር ቢሆነልልም፣ የሚወዳቸውን በጎቹንና የነጋዴውን ሴት ልጅ ትቶ ፣ የሜዲትራኒያንን ባሕር አቋርጦ አፍሪካ ሲገባ ያልጠበቀው ነገር ይገጥመዋል። አፍሪካውያኖቹ አረቢኛ እንጂ የእስፓኝ፡ቋንቋ አይናገሩም። 
          አስገራሚው ነገር ሳንቲያጎ ከአንድ አረባዊ ቋሊማ ነጋዴ ጋር ሳይነጋገሩ ተግባብተው ለቋሊማ ነጋዴው ተቀጥሮ ሙሉቀን ሰርቶለት፣ ደሞዙን ቋሊማ ተቀብሎ ሄደ። ወደ ካይሮ የሚወስደውን የስሀራን በርሀ ሲያቋርጥ  አንድ ከፅንፈ ዓለም እየጠፋ ያለውን ፅንፈ-ዓለማዊውን ቋንቋ ከአልኬሚስቶች ለመማር ወደ ካይሮ የሚሄድ አንድ እንግሊዛዊ ፕሮፌሰር ያገኛል። ካይሮ ከመድረሳቸው በፊት በሰሀራ በረሐ በሚገኘው ለምለም ቦታ (oasis of the sahara) አልኬሚስቱ ሳንቲያጎን ፈልጎ መጣ። እኒህ ብረትን ወደ ወርቅነት መቀየር ይችላሉ እየተባለ የሚነገርላቸው ጠቢቦች፤ ከፈላስፎችና ከምሁራን አንድ እረኛን መረጡ። አልኬሚስቱና ሳንቲያጎ በመንገድ ላይ በጎሳ ጦረኞች ተማርከው ከሞት የሚያስጥላቸው ነፋስ ብቻ ነበርና ከበጎቹ ጋር በሚያወራበት፣ ቋሊማ ነጋዴውን ባነጋገረበት ቋንቋ ነፋሱን አነጋገረው፣ ፀሐይም ሰማች፤ መልሳም ተናገረችው። ሳንቲያጎ፣ በምድር ላይ ያለ የሰው ዘር ሁሉ የዘነጋውን፣ ምሁራን የሳቱት፣ ፈላስፎች የዘለሉትን ፅንፈ አለማዊውን ቋንቋ ከግዑዛን ጋር አወራበት። የፓውሎን ዘ-አልኬሚስት የመጨረሻውን ገፅ ስንዘጋ ፅንፈ-ዓእማዊው ቋንቋ ፍቅር መሆኑን ነግረናል።

ከጥንጥዬዋ አተም እና ግዙፉ ፅንፈ አለም ውስጥ ያሉት የከዋክብት ረጨቶች በሕብረት የሚንቀሳቀሱበት ቋንቋ እውነት ፍቅር ይሆን? ቅዱሳት መፅሐፍት 1001 ጊዜ ነግረውን አልገባን ያለውን፣ ፓውሎ ኮሆሊዮ በዘ-አልኬሚስት መፅሐፉ ለ30 ሚሊዮን ሰዎች አስነበበን። እኛ ደሞ ለእናንተ አካፈልናት።

እጀ-መንገድ

እጂቱ የኔ፣ መንገዲቱ ደሞ የጋሽ ስብሐት ናት።ጋሽ ስብሐትን “መንገድህን አውሰኝ፣” ብለው፤ “የሰው መንገድ ምን ያደርግልሀል?” ብሎ መንገዱን ከለከለኝ። እኔ ደግሞ ባንተ መንገድ መሄድ ነው ያማረኝ አልኩና መንገዱን ወሰድኩበት።ሀገርና መንገድ የጋራ አይደል? እነሆ እጀ-መንገድ።

ጥቁርና ነጭ ብርድ ልብስ

በ1969 በሞሀመድ ዚያድባሬ የሚመራው የሶማሌ ጦር ምስራቅ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ።ኦጋዴን፣ ደገሀቡር፣ ገላዲን፣ቀብሪደሀር፣ጂጂጋ፣ቀላፎ፣ዋርዴር፣ጎዴ፣... በሶማሌ ጦር እጅ ወደቁ። በመላው ኢትዮጵያ የእናት ሀገር ጥሪ ተደረገ። ለዚህ ጥሪ 300 000 የሚሊሺያ ሠራዊት አባላት ምላሽ ሰጥተው ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ዘመቱ። ይህ ነው ምኞቴ እኔ በሕይወቴ፣ ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ፣ የሚለው መዝሙር የነዚህ ሚሊሺያ ሰራዊት አባላት የጋራ መዝሙር ነበር። ከአዋሽ ወንዝ ጀምሮ የሶማሌን ወራሪ ጦር አባረው፣ ገላዲንን ነፃ አውጥተው፣ በሶማሌ ድንበር ውስጥ ገልደጎብ ላይ ምሽግ ቆፍረው ለ12 ዓመታት ድንበር የጠበቁት እነዚህ የሚሊሻ ሠራዊት አባላት፣ ከመላው ኢትዮጵያ ከሁሉም ብሔረሰቦች የተውጣጡ፣ ሕዝባዊ ሠራዊት ነበሩ።አላማቸውም አንድ ነበር።ሀገራቸውን ከጥቃት መከላከል። እነዚህ ከሀገሪቱ የተለያየ ክፍል፣ከዳር እስከዳር ለአንድ ዓላማ በነቂስ የወጡት የሠራዊቱ አባላት ታጠቅ ማሰልጠኛ ጣቢያ ለስልጠና ሲገቡ በጥቁርና በነጭ ብርድልብስ ምክንያት እርስ በርስ ተጋድለዋል። ዛሬ ካራማራ ተራራ ላይ፣ ያልወለቁ በሺህ የሚቆጠሩ የወታደር ጫማዎች አሉ። እነዛ ጫማዎች ለእናት ሀገር ምድር፣ ለእናት ሀገር ሰማይ ፍቅርና ልዕልና የወደቁ የሕዝባዊ ሠራዊት አባላትን ቅሪት አፅም እንደያዙ ናቸው። እነዚያ ጫማዎች፣ እርጉዝ ሚስቶቻቸውን ከባዶ ቤት ጥለው፣ ያጨዱትን ሳይሰበስቡ፣እንደወጡ የቀሩ የሀገራችን የቁርጥ ቀን ልጆች ቅሪት መቃብር ናቸው። ለአሥራ ስምንት ዓመታት በሐረርጌ ሜዳዎች ተፈንግለው ይታዩ የነበሩት ታንኮች፣ በየሜዳው እንደድንጋይ ይለቀሙ የነበሩ የሞርታር ጥይቶች፣ በየቦታው ይታዩ የነበሩ፤ የወታደር መኪኖች እነዚህን ሠራዊቶች ጭነው ነበር። በ1972 የዋርዴር አዙሪት የዋጣቸው 370 የሚሊሻ አባላት አላማቸው አንድ ነበር።” እናት ሀገር ወይንም ሞት!” ።እነዛ የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት አብዮት የሚለውን ፍልስፍና አያቁም። ማርክስና ሌኒን በመንደራቸው ማንም አይደሉም፤ ደርግን፣ ወይንም ሶሻሊዝምን ለመከላከል አይደለም የዘመቱት፣ የሶማሌ ጥላቻም አይደለም። የሀገር ድንበር ለማስከበር ብቻ ነው። በ4ኛው የአብዮት በዓል በአብዮት አደባባይ ሰልፍ ካሳዩት እነዛ ሁሉ የሠራዊት አባላት፣ ብዙዎቹ በክብር ወደቤታቸው አልተመለሱም።ያን ያህል ሀገራቸውን ይወዱ የነበሩ፣ ለሀገራቸው ያላቸውን ሁሉ የሰጡ እንዴት በብርድ ልብስ ምክንያት እርስ በርስ ተላለቁ?

ከመላው ሀገሪቱ የተመለመሉት የሠራዊቱ አባላት ወደ ታጠቅ ጦር ሠፈር የገቡት በቅደም ተከተል ነበር። ለጦር ሠፈሩ የሚቀርቡት ቀድመው ሲገቡ፣ ራቅ ያሉት ዘግየት ብለው ተከታተሉ። ቀድመው የገቡት ነጭ ብርድልብስ ሲሰጣቸው በኋላ የገቡት ጥቁር ብርድልብስ ታደላቸው። ጠዋት ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ ለቁርስ ሲሰለፉ በብርድ ልብስ ቀለም ተቧድነው አጠገባቸው ባገኙት ነገር ሁሉ ተጨፋጨፉ፣ በዛ ቀን 273 ሬሳ ተለቀመ።በሺህ የሚቆጠሩ ቆስለው ለሆስፒታል ተዳረጉ።ታጠቅ ጦር ሠፈር፣ ለአንድ ዓላማ የወጡ፣ የወንድማማቾችን ደም ጠጣች። ዛሬም የሀገራችን ድህነት እያሳዘነን ውስጣችን ለእናት ሀገር ሊሞት እየተዘጋጀ፣ ከውጭ በለበስነው አቋም እርስ በርስ ጠላት ሆንን። ጥንካሬአችን ሊሆን የሚገባው የፖለቲካ አቋማችን ጥቁር ብርድልብስ፣ ውበታችን የሆነው ብሔረሰባችን ነጭ ብርድልብስ ሆነው ለግድያ ተፋጠጥን። አላማችን ግን አንድ ነው። የበለፀገች ኢትዮጵያን መፍጠር። ልዩነታችንን አውቀን፣ ልዩነታችንን ካላከበርን፣ ዓላማችን የጠላት ዒላማ ይሆናል፣ ሕልማችንም ቅዠት ሆኖ ይቀራል። በዚሁ ምክንያት በገዛ ድሎቻችን እኳን ተሸነፍን። በበለጥንበት ሜዳ ተሸንፈን ወጣን። ኃያል ሆነን ሳለ ደክመን ወደቅን።

                              ሕብረት ኃይላችን ነው።