አባል ውይይት:Lovezeida

Page contents not supported in other languages.
ከውክፔዲያ

ኩታበር[ኮድ አርም]

የኩታበር ወረዳ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን መሰተዳዳር ከሚገኙ 24 ወረዳዎች አንዱ ነው በወረዳው ውስጥ 20 የገጠር እና 1 ከተማ ቀበሌ በጠቅላላ 21 ቀበሌዎች አሉ::ወረዳው ከደቡብ ወሎ ዞን ዋና ከተማ ደሴ በ20 ኪሜ ከክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር በ500 ኪ.ሜ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በ420 ኪ.ሜ እርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ወረዳው፡- በምሰራቅ ከተሁለደሬ በምዕራብ ከተንታ ከሰሜን አምባሰል ከደቡብ ከደሴ ዙሪያ ትዋሰናለች ፡፡ የወረዳው ቆዳ ስፋት 70071 ሔ/ር ሲሆን አየር ንብረቱም ቆላማ 4% ደጋ 42 % ወይና ደጋ 54% ሲሆና የወረዳው ዋና ከተማ የተቆረቆረቸው 1938 ጀምሮ በወቅቱ የአካባቢዊ ገዥ በነበሩት በአቶ ብርሃነ ስላሴና በደጅ አዝማች በላይ አሊ አማካኝነት እንደተቆረቆረ የከተማዋ የእድሜ ባለጸጋዎች ይናገራሉ የኩታበር ከተማ የዱሮ ስያሜዋ መታሎ በር ሲሆን ይህ ስያሜ የተሰጣት በአካባቢው መታሎ ተብሎ የሚጠራ ወንዝ በመኖሩ ከወንዙ ስም የተወሰደ ነበረ የአሁኑ ስያሜዋን ያገኘችበት ምክንያት የአገር ሽማሌዎች ሲናገሩ የደጃ አዝማች በላይ አሊ ዘመድ የሆኑት ሴት እሳቸውን ለመጠየቅ ወደ መታሎ በር መጥተው እንደነበረና አካባቢዊ ንፋሳማ በመሆኑ የለበሱትን ኩታ የንፋሱ ኃይል እያውለበለበ ሊውስደባቸው ሲሆን ኩታየን ያገርህ ንፋስ ሊቀማኝ ነው ብለው በመቀለዳቸው በዚህ አጋጣሚ ከሴትዮዋ ኩታ ጋር በማያያዝ ኩታበር እንደተባለች ያስረዳሉ ፡፡