አባል ውይይት:Medre Genet Arba minch ethiopia

Page contents not supported in other languages.
ከውክፔዲያ
    አርባ ምንጭ ከተማ ከታደለቻቸውና የፈጣሪዋን ስም ከምታነሳባቸው መልካም ገጽታዎች መካከል ሌላው ቅርስ የእግዜር ድልድይ ነው። ከከተማዋ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው በተለምዶ “የእግዜር ድልድይ” ተብሎ የሚጠራው ይህ ድልድይ ትልቅ የመሬት አካል ሲሆን ሁለት የተለያዩ ይዘትና ቀለም ያላቸው /አባያና ጫሞ/ ሐይቆች  ተገናኝተው ፀብ እንዳይፈጥሩ ለመገላገል በዳኝነት የቆመ የሚመስል አስገራሚ የመሬት ከፍታ ነው። የእግዜር ድልድይ አፈጣጠር በእጅጉ ይገርማል። የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስብ የተፈጥሮ ስጦታ ነው። አርባ ምንጭ ከተማን እንዲሁም የአባያና ጫሞ ሃይቆችን ሙሉ ገጸታ፣ በቅርብ ርቀት ለማየትና ለመዝናናት ምቹ በመሆኑ በተለይም የውጪ አገር ቱሪስቶች ከዚህ ስፍራ ሆነው አካባቢውን ለማየት ስፍራውን ይመርጡታል።  እግዜር ድልድይ ላይ ሆነው አባያና ጫሞን ከነሞገሳቸው በመመልከት የሃይቆቹን ውሃ መልክ ልዩነት ማወቅ ይችላሉ። ንፁህና የመጠጥ ውሃ መልክ ይዞ የተኛው  የጫሞ ሐይቅ ነው፤ መልኩ ወርቅ የሚመስለው ግዙፍ ሐይቅ ደግሞ አባያ ይህንን ውበት እየተመለከቱበት ያለው ድልድይ ደግሞ የእግዜር ድልድይ።
   [[1]]