Jump to content

አቶም

ከውክፔዲያ
(ከአተም የተዛወረ)
አተም
የሂሊየም አተም
ሂሊየም አተም


ሐምራዊው ኑክሊየስን፣


ጥቁሩ ጭጋግ የኤሌክትሮን ደመናን፣ እና

ጥቁሩ አሞሌ መስመር (10−10 m or 100 pm)ን ይወክላሉ።

ክፍፍሎች
አቶም የኬሚካል ንጥር ታናሹ ክፍልፋይ ነው
ጸባዮች
ግዝፈት: 1.66 x 10(−27) to 4.52 x 10(−25) kg
ኤሌክትሪክ ቻርጅ: ዜሮ

አቶም ወይም አተም ሁሉም ቁስ የተገነባበት መሰረታዊ እኑስ ነው። እንደ ግዝፈታቸው፣ መጠናቸው የተያየ ስም ያላቸው ብዙ አይነት አተሞች አሉ። እነዚህ የተያዩ አይነት አተሞች የኬሚካል ንጥር ይባላሉ። ለምሳሌ ወርቅ አንዱ የንጥር አይነት ነው።

አተሞች ለአይን እማይታዩ፣ በጣም ደቃቅ ቢሆኑም ትክክለኛ መጠናቸው ግን ከንጥር ንጥር ይለያያል። በአጠቃላይ መልኩ አተሞች ከ 0.1 እስከ 0.5 ናኖ ሜትር ስፋት ሊኖራቸው ይችላል

አብላጫውን ጊዜ አተሞች ብቻቸውን አይገኙም። ይልቁኑ አንዱ አቶም ከሌላ አቶም ጋር በመጋጠም ሞልኪዩል የተሰኘውን እኑስ ይፈጥራሉ። ለምሳሌ ሁለት የሃይድሮጅን እና አንድ የኦክሲጅን አተሞች ሲጋጠሙ የውሃ ሞልኪዩልን ይፈጥራሉ።

አተሞች በራሳቸው ከ3 አንስተኛ እኑሶች የተሰሩ ናቸው። እነዚህም ኤሌክትሮንፕሮቶን እና ኒውትሮን ይባላሉ። ፕሮቶኖችና ኒውትሮኖች አንድ ላይ ሆነው በአቶሙ መሃል ተጠጋግተው ሲቀመጡ የአተሙን ኒኩሊየስ ይፈጥራሉ። ኤሌክትሮኖች በበኩላቸው ይህን ኒኩሊየስ በደመና መልክ ከበው ይገኛሉ። ኤሌክትሮኖች ምንም እንኳ ኒኩሊየሱን እየከበቡ ቢሽከረከሩም ከኒኩሊየሱ በረው እንዳይጠፉ የኤሌክትሮመግነጢስ ጉልበት አዋዶ ይይዛቸዋል።

በአተም ውስጥ የሚገኙት የፕሮቶን፣ ኒውትሮንና እና ኤሌክትሮን ብዛቶች ያ አተም ምን ንጥር እንደሆነ ይወስናል። ለምሳሌ አንድ አቶም 1 ፕሮቶን፣ 0 ኒውትሮን እና 1 ኤሌክትሮን ካለው ሃይድሮጅን ይሆናል፣ በአንጻሩ 16 ፕሮቶን፣ 16 ኒውትሮን እና 16 ኤሌክትሮን ካለው ድኝ (ሰልፈር) ይሆናል ማለት ነው።

አተሞች እርስ በርሳቸው ሳይጋፉ ሰፋ ብለው ሲቀመጡ ጋዝ ወይንም አየር ይሆናሉ። በተቃራኒ፣ ጭፍግ ብለው አንድ ቦታ ላይ ሲገኙ እና መንቀሳቀስ እሚችሉ በመንቀጥቀጥ ከሆነ ጠጣር ነገር ይሆናሉ።

እቶን የአቶም እሳት በአቶም ፉዝዮን ወይም አቶምን በመክፈል የሚገኝ እጂ-ትልቅ ኃይል ነው።

ተጨማሪ ንባቦች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]