አውቶስቴሮግራም
Appearance
አውቶስቴሮግራም ማለቱ ያለ መነጽር ከሁለት ቅጥ ገጽታ ላይ የተሳለን ስዕል ሦስት ቅጥ እንዳለው ሆኖ በሰው ልጅ አንጎል መታየቱ።
አውቶስቴሪዮግራምን ለማየት 3 ስልቶች መከተል ይቻላል።
አንድ፣ አፍንጫ የስዕሉን ገጽ እንዲነካ አድርጎ መጠጋት። ከዚያ አይንን ሳያንቀሳቅሱ ቀስ ብሎ ራቅ ማለት። በዚህ ወቅት አይን ስዕሉ ላይ ለማተኮር ስለሚፈልግ እንዳያታኩር፣ እንዲያውም ድሮ በነበረበት ሁኔታ እንዲቀጥል ማድረግ። ቀስ ብሎ ወደኋላ ሲኬድ የሆነ ቦታ ላይ 3 ቅጡ ምስል ይገለጣል።
ሁለተኛው ዘዴ ስዕሉን እየተመለከቱ ግን ከስዕሉ በስተጀርባ ላይ ባለ እቃ ላይ አይንን ማተኮር (በእርግጥ ሳይሆን፣ በምናብ)። ወይም በስዕሉ ውስጥ የራስን ነጸብራቅ ለማየት መሞከር።
ሦስተኛው እና የበለጠ አስተማማኙ መንገድ፣ አንድ ጣትን በአይንመካከል በማስቀመጥ፣ እዚያ ጣት ላይ በማተኮር፣ ቀስ በቀስ ጣቱን ወደስዕሉ በማስጠጋትና ጣቱ ላይ ምንጊዜም ትኩረት በማድረግ፣ ልክ 3 ቅጥ የሆነውን የአውቶ ስቴሪዮግራም ምስል ሲያዩ በማቆም ነው።