Jump to content

አዘዞ

ከውክፔዲያ

ስለ አዘዞ ከተማ የሚያመለክት ትንሽ ሃተታ

አዘዞ የተባለችው ከተማ በሽማግሌዎችና ሊቃውንት አንደበት ሲነገር የነበረው አፈ ታሪክ የስሟ ትርጓሜ አንዲህ ነው፡፡ ይህች አዘዞ የተባለች ከተማ የጎንደር ነገስታት በሞቱ ጊዜ ይቀበሩባት ነበር፡፡ የን ግዜም ሲሞቱ የትዕዛዛቸውና የኑዛዜአቸው ቃል ከመቃብረ መንግስት መዝገብ ውስጥ እንዲገኝ እያሉ ከሞቱ በኋላ የሚሆነውን የኑዛዜአቸውንና የትዕዛዛቸውን ቃል ስለሚያስቀምጡበት ያዘዙበት ወይም የተናዘዙበት ቦታ በማለት ፈንታ ከዘመን ብዛት አዘዞ ተባለች እንጂ ጥን ስሟ አዝዞ ወይም ተናዝዞ ሞተ ማለት ነው፡፡

ምንጭ፡ አባ ጋስፖሪኒ ጉማ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ከረጅሙ ባጭሩ የተውጣጣ፡፡